ሱረቱ Ibrahim ابراهيم
52 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 72
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓر كِتَٰبٌ أَنزَلْنَٰهُ إِلَيْكَ لِتُخْرِجَ ٱلنَّاسَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ بِإِذْنِ رَبِّهِمْ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَمِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ቁርኣን ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ፤ ምስጉን ወደ ሆነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወደ አንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهِ ٱلَّذِى لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَوَيْلٌ لِّلْكَٰفِرِينَ مِنْ عَذَابٍ شَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy2. ወደ እዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ወደ ሆነው ጌታ ወደ አላህ መንገድ (ታወጣ ዘንድ ):: ለከሓዲያን ሁሉ ከብርቱ ቅጣት ወዮላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَسْتَحِبُّونَ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا عَلَى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍۭ بَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy3. እነዚያ የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ህይወት ይበልጥ የሚወዱና ከአላህ መንገድ ሰዎችን የሚያግዱ፤ መጥመሟንም (ደካማ ጎኗን) የሚፈልጓት ናቸው:: እነዚያ በሩቅ ስህተት ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا بِلِسَانِ قَوْمِهِۦ لِيُبَيِّنَ لَهُمْ فَيُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِى مَن يَشَآءُ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy4. ከመልዕክተኞች ማንኛውንም ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም:: አላህ የሚፈልገውንም ያጠምማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ أَنْ أَخْرِجْ قَوْمَكَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَذَكِّرْهُم بِأَيَّىٰمِ ٱللَّهِ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy5. ሙሳን ወገኖችህን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ:: የአላህንም ቀናት አስገንዝባቸው በማለት በተዓምራታችን አጠናክረን በእርግጥ ላክነው:: በዚህ ውስጥ በብዙ ታጋሽና በብዙ አመስጋኝ ለሆኑት ሁሉ በእርግጥ ብዙ ተዓምራት አሉበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ أَنجَىٰكُم مِّنْ ءَالِ فِرْعَوْنَ يَسُومُونَكُمْ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ وَيُذَبِّحُونَ أَبْنَآءَكُمْ وَيَسْتَحْيُونَ نِسَآءَكُمْ وَفِى ذَٰلِكُم بَلَآءٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ «ከፈርዖን ቤተሰቦች መጥፎን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆን በአዳናችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለላችሁን የአላህን ጸጋ አስታውሱ:: በዚሃችሁ ከጌታችሁ የሆነ ታላቅ ፈተና አለበት።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِى لَشَدِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. ጌታችሁም፦ «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ:: ብትክዱም እቀጣችኋለሁ:: ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነው።» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ مُوسَىٰٓ إِن تَكْفُرُوٓا۟ أَنتُمْ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا فَإِنَّ ٱللَّهَ لَغَنِىٌّ حَمِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy8. ሙሳ፡- «እናንተም በምድር ያለዉም ሁሉ በመላ ብትክዱ አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነው።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ يَأْتِكُمْ نَبَؤُا۟ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعْدِهِمْ لَا يَعْلَمُهُمْ إِلَّا ٱللَّهُ جَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَرَدُّوٓا۟ أَيْدِيَهُمْ فِىٓ أَفْوَٰهِهِمْ وَقَالُوٓا۟ إِنَّا كَفَرْنَا بِمَآ أُرْسِلْتُم بِهِۦ وَإِنَّا لَفِى شَكٍّ مِّمَّا تَدْعُونَنَآ إِلَيْهِ مُرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy9. (ሙስሊሞች ሆይ!) የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑህ ህዝቦች፤ የዓድ፣ የሠሙድም የእነዚያም ከእነርሱ በኋላ የነበሩት ከአላህ በስተቀር ሌላ የማያውቃቸው ህዝቦች ወሬ (ታሪክ) አልመጣላችሁምን? መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች መጡላቸውና እጆቻቸውን በቁጭት ሊነክሱ ወደ አፎቻቸው መለሱ: «በተላካችሁበት ነገር ካድን እኛም ወደ እርሱ ከምትጠሩን ነገር አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ነን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَتْ رُسُلُهُمْ أَفِى ٱللَّهِ شَكٌّ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يَدْعُوكُمْ لِيَغْفِرَ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُؤَخِّرَكُمْ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى قَالُوٓا۟ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُنَا تُرِيدُونَ أَن تَصُدُّونَا عَمَّا كَانَ يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأْتُونَا بِسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy10. መልዕክተኞቻቸው «ከኃጢአቶቻችሁ እንዲሚራችሁ ወደ ተወሰነ ጊዜም ያለ ቅጣት እንዲያቆያችሁ የሚጠራችሁ ሲሆን ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ በሆነው አላህ በመኖሩ ጥርጣሬ አለን?» አሏቸው:: ህዝቦቹም፡ «እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ (ሌላ ፍጡር) አይደላችሁም:: አባቶቻችን ይገዙት ከነበሩት ልትከለክሉን ትሻላችሁን? ግልጽን አስረጅ ካመጣችሁት ሌላ እስቲ አምጡልን።» አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَتْ لَهُمْ رُسُلُهُمْ إِن نَّحْنُ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَمُنُّ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ وَمَا كَانَ لَنَآ أَن نَّأْتِيَكُم بِسُلْطَٰنٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. መልዕክተኞቻቸውም ለእነርሱ አሉ: «እኛ ብጤያችሁ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለንም:: ግን አላህ ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ ይለግሳል:: እኛም በአላህ ፈቃድ እንጂ ማስረጃን ልናመጣላችሁ አይገባንም:: በአላህ ላይ ብቻ ምእመናን ይጠጉ (ይመኩ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا لَنَآ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدْ هَدَىٰنَا سُبُلَنَا وَلَنَصْبِرَنَّ عَلَىٰ مَآ ءَاذَيْتُمُونَا وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُتَوَكِّلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. «መንገዳችንን በእርግጥ የመራን ሲሆን በአላህ ላይ የማንመካበት ምን አለን? በማሰቃየታችሁም ላይ እንታገሳለን:: በአላህ ላይ ብቻ ተመኪዎች ሁሉ ይመኩ።» (አሉ)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِرُسُلِهِمْ لَنُخْرِجَنَّكُم مِّنْ أَرْضِنَآ أَوْ لَتَعُودُنَّ فِى مِلَّتِنَا فَأَوْحَىٰٓ إِلَيْهِمْ رَبُّهُمْ لَنُهْلِكَنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. እነዚያ በአላህ የካዱት ለመልእክተኞቻቸው: «ከምድራችን በእርግጥ እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን ትመለሳላችሁ።» አሉ:: ወደ እነርሱም ጌታቸው እንዲህ ሲል ላከ: «(ከሓዲያን) በዳዮችን እናጠፋለን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَنُسْكِنَنَّكُمُ ٱلْأَرْضَ مِنۢ بَعْدِهِمْ ذَٰلِكَ لِمَنْ خَافَ مَقَامِى وَخَافَ وَعِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy14. «ከእነርሱ በኋላም በምድሪቱ በእርግጥ እናስቀምጣችኋለን:: ይህ በፊቴ መቆሙን ለሚፈራና ዛቻዬን ለሚፈራ ነው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱسْتَفْتَحُوا۟ وَخَابَ كُلُّ جَبَّارٍ عَنِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy15. እርዳታንም ከአላህ ፈለጉ፤ ተረዱም። ጨካኝ ሞገደኛ የሆነም ሁሉ አፈረ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِّن وَرَآئِهِۦ جَهَنَّمُ وَيُسْقَىٰ مِن مَّآءٍ صَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy16. ከስተፊቱ ገሀነም አለበት:: እዥ ከሆነም ውሃ ይጋታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَتَجَرَّعُهُۥ وَلَا يَكَادُ يُسِيغُهُۥ وَيَأْتِيهِ ٱلْمَوْتُ مِن كُلِّ مَكَانٍ وَمَا هُوَ بِمَيِّتٍ وَمِن وَرَآئِهِۦ عَذَابٌ غَلِيظٌ
Amharic Translation - Africa Academy17. ይጎነጨዋል፤ ሊውጠዉም አይቀርብም:: ሞትም ከየስፍራው ሁሉ ይመጣበታል:: እርሱም የሚሞት አይደለም:: ከበስተፊቱም ከባድ ቅጣት አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّثَلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِرَبِّهِمْ أَعْمَٰلُهُمْ كَرَمَادٍ ٱشْتَدَّتْ بِهِ ٱلرِّيحُ فِى يَوْمٍ عَاصِفٍ لَّا يَقْدِرُونَ مِمَّا كَسَبُوا۟ عَلَىٰ شَىْءٍ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلضَّلَٰلُ ٱلْبَعِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy18. የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው ምሳሌ በነፋሻ ቀን ነፋስ እንደ በረታችበት አመድ ነው:: በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም። ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِٱلْحَقِّ إِن يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَأْتِ بِخَلْقٍ جَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy19. (የሰው ልጅ ሆይ!) አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ መሆኑን አታይምን? ቢሻ ያጠፋችኋል:: አዲስ ፍጡርንም ያመጣል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٍ
Amharic Translation - Africa Academy20. ይህም እናንተን አጥፍቶ አዲስ ፍጥረትን ማምጣት በአላህ ላይ አስቸጋሪ ጉዳይ አይደለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبَرَزُوا۟ لِلَّهِ جَمِيعًا فَقَالَ ٱلضُّعَفَٰٓؤُا۟ لِلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوٓا۟ إِنَّا كُنَّا لَكُمْ تَبَعًا فَهَلْ أَنتُم مُّغْنُونَ عَنَّا مِنْ عَذَابِ ٱللَّهِ مِن شَىْءٍ قَالُوا۟ لَوْ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ لَهَدَيْنَٰكُمْ سَوَآءٌ عَلَيْنَآ أَجَزِعْنَآ أَمْ صَبَرْنَا مَا لَنَا مِن مَّحِيصٍ
Amharic Translation - Africa Academy21. የተሰበሰቡ ሆነው ለአላህ ይገለጻሉ። ሐሳበ ደካማዎቹም ተከታዮች ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርን እናንተ ከአላህ ቅጣት ከእኛ ላይ አንዳችን ነገር ተከላካዮች ናችሁን?» ይሏቸዋል። አስከታዮቹም። «አላህ ባቀናን ኖሮ በመራናችሁ ነበር።» ይሏቸዋል:: «ብንበሳጭ ወይም ብንታገሥም በእኛ ላይ ሁሉም እኩል ነው:: ለእኛ ምንም መጠጊያ የለንም።» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلشَّيْطَٰنُ لَمَّا قُضِىَ ٱلْأَمْرُ إِنَّ ٱللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ ٱلْحَقِّ وَوَعَدتُّكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ وَمَا كَانَ لِىَ عَلَيْكُم مِّن سُلْطَٰنٍ إِلَّآ أَن دَعَوْتُكُمْ فَٱسْتَجَبْتُمْ لِى فَلَا تَلُومُونِى وَلُومُوٓا۟ أَنفُسَكُم مَّآ أَنَا۠ بِمُصْرِخِكُمْ وَمَآ أَنتُم بِمُصْرِخِىَّ إِنِّى كَفَرْتُ بِمَآ أَشْرَكْتُمُونِ مِن قَبْلُ إِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy22. ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል: «አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ እኔም ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ:: አፈረስኩባችሁም:: ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ሥልጣን አልነበረኝም:: ግና ጠራኋችሁና ታዘዛችሁኝ:: ስለዚህ አትውቀሱኝ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ:: እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም። እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ሁሉ ካድኩ በዳዮቹ ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُدْخِلَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِمْ تَحِيَّتُهُمْ فِيهَا سَلَٰمٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. እነዚያ በትክክል ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በጌታቸው ፈቃድ እንዲገቡ ይደረጋሉ:: በውስጣቸው መከባበሪያቸው ሰላምታቸው «ሰላም ለእናንተ ይሁን መባባል» ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ كَيْفَ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا كَلِمَةً طَيِّبَةً كَشَجَرَةٍ طَيِّبَةٍ أَصْلُهَا ثَابِتٌ وَفَرْعُهَا فِى ٱلسَّمَآءِ
Amharic Translation - Africa Academy24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ መልካምን ቃል ሥሯ በምድር ውስጥ የተደላደለች ቅርንጫፏም ወደ ሰማይ የረዘመች እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየህምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تُؤْتِىٓ أُكُلَهَا كُلَّ حِينٍۭ بِإِذْنِ رَبِّهَا وَيَضْرِبُ ٱللَّهُ ٱلْأَمْثَالَ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. ፍሬዋን (ምግቧን) በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች:: አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَثَلُ كَلِمَةٍ خَبِيثَةٍ كَشَجَرَةٍ خَبِيثَةٍ ٱجْتُثَّتْ مِن فَوْقِ ٱلْأَرْضِ مَا لَهَا مِن قَرَارٍ
Amharic Translation - Africa Academy26. የመጥፎ ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተገረሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደ ሆነች መጥፎ ዛፍ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُثَبِّتُ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱلْقَوْلِ ٱلثَّابِتِ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَفِى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَيُضِلُّ ٱللَّهُ ٱلظَّٰلِمِينَ وَيَفْعَلُ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُ
Amharic Translation - Africa Academy27. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት ሆነ በመጨረሻይቱም በመቃብር በተረጋገጠው ቃል (በሸሀዳ) ላይ ያደርጋቸዋል (ያጸናቸዋል):: ከሓዲያንንም አላህ ያሳስታቸዋል፤ አላህም የሚሻውን ይሰራልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ بَدَّلُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ كُفْرًا وَأَحَلُّوا۟ قَوْمَهُمْ دَارَ ٱلْبَوَارِ
Amharic Translation - Africa Academy28. ወደ እነዚያ የአላህን ጸጋ በክህደት ወደ ለወጡትና ህዝቦቻቸውን በጥፋት ሀገር ወዳሰፈሩት (ወደ ቁረይሾች) አላየህምን? (አልተመለከትክምን?)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
جَهَنَّمَ يَصْلَوْنَهَا وَبِئْسَ ٱلْقَرَارُ
Amharic Translation - Africa Academy29. ሀገሪቱም የሚገቡባት ስትሆን ገሀነም ናት:: መርጊያነቷ ምንኛ ትከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلُوا۟ لِلَّهِ أَندَادًا لِّيُضِلُّوا۟ عَن سَبِيلِهِۦ قُلْ تَمَتَّعُوا۟ فَإِنَّ مَصِيرَكُمْ إِلَى ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአላህ ከመንገዱ ያሳስቱ ዘንድ ባላንጣዎችን አደረጉለት:: (ሙሐመድ ሆይ!) «ጥቂትን ተጠቀሙ መመለሻችሁም ወደ እሳት ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لِّعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ يُقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُنفِقُوا۟ مِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِىَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خِلَٰلٌ
Amharic Translation - Africa Academy31. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለእነዚያ ላመኑት ባሮቼ ሽያጭና ወዳጅነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ሶላትን በደንቡ እንዲሰግዱ፤ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም ሆነ በግልጽ እንዲለግሱም ንገራቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَخْرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزْقًا لَّكُمْ وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلْفُلْكَ لِتَجْرِىَ فِى ٱلْبَحْرِ بِأَمْرِهِۦ وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلْأَنْهَٰرَ
Amharic Translation - Africa Academy32. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ከሰማይ ዳመናም ውሃን ያወረደ፤ በእርሱም ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ፤ መርከቦችንም በፈቃዱ በባህር ላይ ይንሳፈፉ ዘንድ ለእናንተ ያገራ፤ ወንዞችንም ለናንተ ያገራ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ دَآئِبَيْنِ وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ
Amharic Translation - Africa Academy33. ጸሓይንና ጨረቃንም ዘወትር ሒያጆች ሲሆኑ ለእናንተ የገራ፤ ሌሊትንና ቀንንም ለእናንተ የገራላችሁ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَءَاتَىٰكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ وَإِن تَعُدُّوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ لَا تُحْصُوهَآ إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ لَظَلُومٌ كَفَّارٌ
Amharic Translation - Africa Academy34. ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው:: የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ እንኳ አትዘልቁትም:: ሰው በጣም በደለኛና ከሓዲ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِيمُ رَبِّ ٱجْعَلْ هَٰذَا ٱلْبَلَدَ ءَامِنًا وَٱجْنُبْنِى وَبَنِىَّ أَن نَّعْبُدَ ٱلْأَصْنَامَ
Amharic Translation - Africa Academy35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ባለ ጊዜ አስታውስ: «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር መካን ጸጥተኛ አድርገው:: እኔንና ልጆቼንም ጣኦታትን ከመገዛት አርቀን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبِّ إِنَّهُنَّ أَضْلَلْنَ كَثِيرًا مِّنَ ٱلنَّاسِ فَمَن تَبِعَنِى فَإِنَّهُۥ مِنِّى وَمَنْ عَصَانِى فَإِنَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy36. «ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣኦታቱ) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና:: የተከተለኝም ሰው እርሱ ከእኔ ነው:: ትዕዛዜን የጣሰ ሰው ግን አንተ መሓሪና አዛኝ ነህ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَّبَّنَآ إِنِّىٓ أَسْكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِى بِوَادٍ غَيْرِ ذِى زَرْعٍ عِندَ بَيْتِكَ ٱلْمُحَرَّمِ رَبَّنَا لِيُقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ فَٱجْعَلْ أَفْـِٔدَةً مِّنَ ٱلنَّاسِ تَهْوِىٓ إِلَيْهِمْ وَٱرْزُقْهُم مِّنَ ٱلثَّمَرَٰتِ لَعَلَّهُمْ يَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy37. «ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትህ በካዕባ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ:: ጌታችን ሆይ! ሶላትን ደንቡን ጠብቀው ይሰግዱ ዘንድ አስቀመጥኳቸው:: ከሰዎችም ልቦችን ወደ እነርሱ የሚናፍቁ አድርግ:: ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبَّنَآ إِنَّكَ تَعْلَمُ مَا نُخْفِى وَمَا نُعْلِنُ وَمَا يَخْفَىٰ عَلَى ٱللَّهِ مِن شَىْءٍ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا فِى ٱلسَّمَآءِ
Amharic Translation - Africa Academy38. «ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ:: በአላህ ላይ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር አይደበቅም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى وَهَبَ لِى عَلَى ٱلْكِبَرِ إِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ إِنَّ رَبِّى لَسَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ
Amharic Translation - Africa Academy39. «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማኢልንና ኢስሐቅን ለሰጠኝ አላህ ምስጋና ሁሉ ይገባው። ጌታዬ ልመናን ሰሚ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبِّ ٱجْعَلْنِى مُقِيمَ ٱلصَّلَوٰةِ وَمِن ذُرِّيَّتِى رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَآءِ
Amharic Translation - Africa Academy40. «ጌታዬ ሆይ! ሶላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ:: ከዘሮቼም አድርግ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبَّنَا ٱغْفِرْ لِى وَلِوَٰلِدَىَّ وَلِلْمُؤْمِنِينَ يَوْمَ يَقُومُ ٱلْحِسَابُ
Amharic Translation - Africa Academy41. «ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለአማኞችም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማረን።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَحْسَبَنَّ ٱللَّهَ غَٰفِلًا عَمَّا يَعْمَلُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ ٱلْأَبْصَٰرُ
Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ። የሚያቆያቸው ዓይኖች እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مُهْطِعِينَ مُقْنِعِى رُءُوسِهِمْ لَا يَرْتَدُّ إِلَيْهِمْ طَرْفُهُمْ وَأَفْـِٔدَتُهُمْ هَوَآءٌ
Amharic Translation - Africa Academy43. ወደ ጠሪው መልአክ ቸኳዮች ራሶቻቸውንም አንጋጣጮች ሆነው ዓይኖቻቸው ይፈጣሉ። ዓይኖቻቸው ወደ እነርሱ አይመለሱም:: ልቦቻቸው ባዶዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنذِرِ ٱلنَّاسَ يَوْمَ يَأْتِيهِمُ ٱلْعَذَابُ فَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ رَبَّنَآ أَخِّرْنَآ إِلَىٰٓ أَجَلٍ قَرِيبٍ نُّجِبْ دَعْوَتَكَ وَنَتَّبِعِ ٱلرُّسُلَ أَوَلَمْ تَكُونُوٓا۟ أَقْسَمْتُم مِّن قَبْلُ مَا لَكُم مِّن زَوَالٍ
Amharic Translation - Africa Academy44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎችንም ቅጣቱ የሚመጣባቸውን ቀን አስፈራራቸው:: እነዚያም የበደሉትማ «ጌታችን ሆይ! እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አቆየን:: ጥሪህንም እንቀበላለንና መልዕክተኞቹንም እንከተላለንና።» ይላሉ። ይባላሉም: «ከአሁን በፊት በምድረ ዓለም ለእናንተ ምንም መወገድ የላችሁም በማለት የማላችሁ አልነበራችሁምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَسَكَنتُمْ فِى مَسَٰكِنِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ وَتَبَيَّنَ لَكُمْ كَيْفَ فَعَلْنَا بِهِمْ وَضَرَبْنَا لَكُمُ ٱلْأَمْثَالَ
Amharic Translation - Africa Academy45. «በእነዚያም ነፍሶቻቸውን በበደሉት ሰዎች መኖሪያ ውስጥ ተቀመጣችሁ:: በእነርሱም እንዴት እንደሠራንባቸው ለእናንተም ተገለጸላችሁ፤ ለእናንተ ምሳሌዎችንም ገለጽንላችሁ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَدْ مَكَرُوا۟ مَكْرَهُمْ وَعِندَ ٱللَّهِ مَكْرُهُمْ وَإِن كَانَ مَكْرُهُمْ لِتَزُولَ مِنْهُ ٱلْجِبَالُ
Amharic Translation - Africa Academy46. በነብዩ ላይ ሴራቸውንም በእርግጥ አሴሩ:: ሴራቸዉም ቅጣቱ አላህ ዘንድ ነው:: ሴራቸዉም ኮረብታዎች በእርሱ የሚወገዱበት አልነበረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَا تَحْسَبَنَّ ٱللَّهَ مُخْلِفَ وَعْدِهِۦ رُسُلَهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ ذُو ٱنتِقَامٍ
Amharic Translation - Africa Academy47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህንም ለመልዕክተኞቹ የገባላቸውን ቃል ኪዳኑን አፍራሽ አድርገህ አታስብ:: አላህ ሁሉን አሸናፊና የመበቀል ባለቤት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ تُبَدَّلُ ٱلْأَرْضُ غَيْرَ ٱلْأَرْضِ وَٱلسَّمَٰوَٰتُ وَبَرَزُوا۟ لِلَّهِ ٱلْوَٰحِدِ ٱلْقَهَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy48. ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ በሌላ ሰማያት የሚለወጥበትን እና አንድ ብቸኛና አሸናፊ ለሆነው አላህ ፍጡራን ሁሉ የሚገለጹበትን ቀን የሚሆነውን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَرَى ٱلْمُجْرِمِينَ يَوْمَئِذٍ مُّقَرَّنِينَ فِى ٱلْأَصْفَادِ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አመጸኞችንም በዚያ ቀን በሰንሰለቶች ተቆራኝተው ታያቸዋለህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَرَابِيلُهُم مِّن قَطِرَانٍ وَتَغْشَىٰ وُجُوهَهُمُ ٱلنَّارُ
Amharic Translation - Africa Academy50. ቀሚሶቻቸው ከካትራሜ የተሰሩ ናቸው:: ፊቶቻቸውንም እሳት ትሸፍናቸዋለች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِيَجْزِىَ ٱللَّهُ كُلَّ نَفْسٍ مَّا كَسَبَتْ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ
Amharic Translation - Africa Academy51. አላህ ይህንን ያደረገው ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ትመነዳ ዘንድ ነው:: አላህ ምርመራው ፈጣን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا بَلَٰغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا۟ بِهِۦ وَلِيَعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገሳጭና መድረስ ያለበት ነው:: ሊመከሩበት በእርሱም ሊስፈራሩበት፤ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን ሊያውቁበት፤ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰጹበት የተወረደ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→