caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nahl النحل

128 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 70

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ أَتَىٰٓ أَمْرُ ٱللَّهِ فَلَا تَسْتَعْجِلُوهُ سُبْحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy1. (ከሓዲያን ሆይ!)፤ የአላህ ትዕዛዝ መጣ ስለዚህ አታጣድፉት:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ:: ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ

Amharic Translation - Africa Academy2. ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ መላዕክትን ከራዕይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል:: «ከሓዲያንን በቅጣት አስጠንቅቁ:: እነሆ ከእኔ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ፍሩኝም።» ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِٱلْحَقِّ تَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ :: ከፍም አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ مِن نُّطْفَةٍ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy4.ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው:: ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ ትንሣኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْأَنْعَٰمَ خَلَقَهَا لَكُمْ فِيهَا دِفْءٌ وَمَنَٰفِعُ وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. (ሰዎች ሆይ!) ግመልን፤ ከብትን፤ ፍየልንም፤ በእርሷ ብርድ መከላከያ ሙቀትና ሌሎች ጥቅሞችም ያሉባት ስትሆን ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ (ትመገባላችሁ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَكُمْ فِيهَا جَمَالٌ حِينَ تُرِيحُونَ وَحِينَ تَسْرَحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. በእርሷም ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜና ጧት ወደ ግጦሽ ቦታዋ በምታሰማሯት ወቅት ለእናንተ ውበት አለላችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَحْمِلُ أَثْقَالَكُمْ إِلَىٰ بَلَدٍ لَّمْ تَكُونُوا۟ بَٰلِغِيهِ إِلَّا بِشِقِّ ٱلْأَنفُسِ إِنَّ رَبَّكُمْ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy7. ጓዞቻችሁንም ነፍሶቻችሁን በማስቸገር እንጂ ወደ ማትደርሱበት አገር ትሸከማለች:: ጌታችሁ በእርግጥ ሩህሩህ እና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْخَيْلَ وَٱلْبِغَالَ وَٱلْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. ፈረሶችን፤ በቅሎዎችንና አህዮችን ልትጋልቧቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ:: የማታውቁትን ድንቅ ነገርም ወደ ፊት ይፈጥራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَلَى ٱللَّهِ قَصْدُ ٱلسَّبِيلِ وَمِنْهَا جَآئِرٌ وَلَوْ شَآءَ لَهَدَىٰكُمْ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy9. በአላህም ላይ በችሮታው ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት:: ከእርሷም ጠማማ አለ:: በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً لَّكُم مِّنْهُ شَرَابٌ وَمِنْهُ شَجَرٌ فِيهِ تُسِيمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው:: ከእርሱም ለእናንተ መጠጥ አለላችሁ:: ከእርሱም እንስሳዎችን በእርሱ ውስጥ የምታሰማሩበት ዛፍ ይበቅልበታል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُنۢبِتُ لَكُم بِهِ ٱلزَّرْعَ وَٱلزَّيْتُونَ وَٱلنَّخِيلَ وَٱلْأَعْنَٰبَ وَمِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. በእርሱ አዝመራን፣ የዘይት ወይራን፣ ዘምባባዎችን፣ ወይኖችንና ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ ትልቅ ተዓምር አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ وَٱلنُّجُومُ مُسَخَّرَٰتٌۢ بِأَمْرِهِۦٓ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ:: ከዋክብትም በሙሉ በፈቃዱ ብቻ የተገሩ ናቸው:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ አያሌ ተዓምራት አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا ذَرَأَ لَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مُخْتَلِفًا أَلْوَٰنُهُۥٓ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّقَوْمٍ يَذَّكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ሆኖ የፈጠረላችሁን ሁሉ ገራላችሁ:: በዚህ ውስጥ ለሚገሠጹ ሕዝቦች ሁሉ ግልጽ ተዐምር አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى سَخَّرَ ٱلْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا۟ مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا۟ مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا وَتَرَى ٱلْفُلْكَ مَوَاخِرَ فِيهِ وَلِتَبْتَغُوا۟ مِن فَضْلِهِۦ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. እርሱ ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው:: መርከቦችንም በውስጡ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ:: ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም ገራላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَلْقَىٰ فِى ٱلْأَرْضِ رَوَٰسِىَ أَن تَمِيدَ بِكُمْ وَأَنْهَٰرًا وَسُبُلًا لَّعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. በምድር ውስጥ በናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት። ትመሩም ዘንድ ጅረቶችንና መንገዶችን አደረገ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَلَٰمَٰتٍ وَبِٱلنَّجْمِ هُمْ يَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy16. ምልክቶችንም አደረገ:: በከዋክብትም እነርሱ ይመራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَمَن يَخْلُقُ كَمَن لَّا يَخْلُقُ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. (ሰዎች ሆይ!) የሚፈጥር ልክ እንደማይፈጥር ነውን? አትገሠጹምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن تَعُدُّوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحْصُوهَآ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy18. የአላህን ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ يَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. አላህ የምትደብቁትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ያውቃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَخْلُقُونَ شَيْـًٔا وَهُمْ يُخْلَقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው አማልክት ሁሉ ምንንም አይፈጥሩም:: እንዲያዉም እነርሱ ራሳቸው ይፈጠራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْوَٰتٌ غَيْرُ أَحْيَآءٍ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. እነርሱ ሕያው ያልሆኑ ሙታን ናቸው:: እራሳቸው እንኳን መቼ እንደሚቀሰቀሱ አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ فَٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ قُلُوبُهُم مُّنكِرَةٌ وَهُم مُّسْتَكْبِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22. አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲያን ናቸው:: እነርሱም የኮሩ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا جَرَمَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْمُسْتَكْبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy23. አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለበትም:: እርሱ ኩሩዎችን አይወድም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا قِيلَ لَهُم مَّاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمْ قَالُوٓا۟ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy24. ጌታችሁ በሙሐመድ ላይ ምን አወረደ በተባሉ ጊዜም: «የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶችን ነው።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيَحْمِلُوٓا۟ أَوْزَارَهُمْ كَامِلَةً يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَمِنْ أَوْزَارِ ٱلَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيْرِ عِلْمٍ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. ይህንን የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉና ከነዚያም ያለ ዕውቀት ሆነው ከሚያጣምሟቸው ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው:: ንቁ የሚሸከሙት ኃጢአት ምንኛ ከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَدْ مَكَرَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَأَتَى ٱللَّهُ بُنْيَٰنَهُم مِّنَ ٱلْقَوَاعِدِ فَخَرَّ عَلَيْهِمُ ٱلسَّقْفُ مِن فَوْقِهِمْ وَأَتَىٰهُمُ ٱلْعَذَابُ مِنْ حَيْثُ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. እነዚያ ከእነርሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት ከሓዲያን አሴሩ:: ከዚያም አላህ ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ:: እናም ጣሪያው በላያቸው ላይ ወደቀባቸው:: ቅጣቱም ከማያውቁት ስፍራ መጣባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يُخْزِيهِمْ وَيَقُولُ أَيْنَ شُرَكَآءِىَ ٱلَّذِينَ كُنتُمْ تُشَٰٓقُّونَ فِيهِمْ قَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ إِنَّ ٱلْخِزْىَ ٱلْيَوْمَ وَٱلسُّوٓءَ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy27. ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል:: «እነዚያም በእነርሱ ጉዳይ ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» ይላቸዋል። እነዚያ እውቀትን የተሰጡት ክፍሎች «ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በከሓዲያን ላይ ነው።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ ظَالِمِىٓ أَنفُسِهِمْ فَأَلْقَوُا۟ ٱلسَّلَمَ مَا كُنَّا نَعْمَلُ مِن سُوٓءٍۭ بَلَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. እነዚያ ነፍሶቻችውን በዳይ ሆነው መላዕክት የሚገድሏቸው «ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርንም» ሲሉ ታዛዥነታቸውን ይገልፃሉ:: «በእውነት አላህ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር አዋቂ ነው።» ይባላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱدْخُلُوٓا۟ أَبْوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَا فَلَبِئْسَ مَثْوَى ٱلْمُتَكَبِّرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. «የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» ይባላሉ:: የኩሩ ሰዎች ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም በእርግጥ ከፋች!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقِيلَ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ مَاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمْ قَالُوا۟ خَيْرًا لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ فِى هَٰذِهِ ٱلدُّنْيَا حَسَنَةٌ وَلَدَارُ ٱلْـَٔاخِرَةِ خَيْرٌ وَلَنِعْمَ دَارُ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy30. ለእነዚያም ለተጠነቀቁት ሰዎች «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ?» ተባሉ:: «መልካምን ነገር አወረደ» አሉ:: ለእነዚያ ደግ ለሠሩት ህዝቦች ሁሉ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አለላቸው:: የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት:: የጥንቁቆቹም አገር ገነት ምን ታምር!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

جَنَّٰتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ لَهُمْ فِيهَا مَا يَشَآءُونَ كَذَٰلِكَ يَجْزِى ٱللَّهُ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. እርሷም የሚገቧትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትሆን የመኖሪያ አትክልቶች (ጀነት) ናት:: ለእነርሱም በውስጧ የሚሹት ነገር ሁሉ አለላቸው:: ልክ እንደዚሁም አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ طَيِّبِينَ يَقُولُونَ سَلَٰمٌ عَلَيْكُمُ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. እነዚያ ጥሩ ሆነው መላዕክት «ሰላም ለእናንተ ይሁን" እያሉ የሚገድሏቸው "ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ምክንያትም ወደ ገነት ግቡ።» ይባላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأْتِيَهُمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ يَأْتِىَ أَمْرُ رَبِّكَ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَمَا ظَلَمَهُمُ ٱللَّهُ وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. ከሓዲያን የመላዕክትን ወደ እነርሱ መምጣት ወይም የጌታህ ትዕዛዝ መምጣቱን እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚህ ሠርተዋል:: አላህም አልበደላቸዉም:: ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَصَابَهُمْ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُوا۟ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. እናም የሠሯቸዉም ኃጢአቶች ቅጣት አገኛቸው:: ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይ ወረደባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ لَوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا عَبَدْنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَىْءٍ نَّحْنُ وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمْنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَىْءٍ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَهَلْ عَلَى ٱلرُّسُلِ إِلَّا ٱلْبَلَٰغُ ٱلْمُبِينُ

Amharic Translation - Africa Academy35. እነዚያም ጣዖታትን በአላህ ያጋሩ ህዝቦች «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም ሆንን አባቶቻችን ምንንም ባልተገዛን ነበር:: ያለ እርሱም ትዕዛዝ ምንንም እርም ባላደረግን ነበር።» አሉ:: እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ልክ እንደዚሁ ሠሩ:: በመልዕክተኞቹም ላይ ግልጽ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوتَ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى ٱللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ ٱلضَّلَٰلَةُ فَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُكَذِّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy36. በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትን ራቁ በማለት የሚያስተምር መልዕክተኛን ልከናል:: ከእነርሱም ውስጥ አላህ ያቀናው አለ:: ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት አለ:: እናም በምድር ላይ ሂዱ:: የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር ተመልከቱ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن تَحْرِصْ عَلَىٰ هُدَىٰهُمْ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى مَن يُضِلُّ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመቅናታቸው ላይ ብትጓጓ (ምንም ልታደርግ አትችልም):: ምክንያቱም አላህ የሚያጠመውን አያቀናዉምና:: ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَقْسَمُوا۟ بِٱللَّهِ جَهْدَ أَيْمَٰنِهِمْ لَا يَبْعَثُ ٱللَّهُ مَن يَمُوتُ بَلَىٰ وَعْدًا عَلَيْهِ حَقًّا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy38. ጥብቅ መሐሎቻቸውንም «አላህ የሚሞትን ሰው አያስነሳም።» ሲሉ በአላህ ስም ማሉ:: አባባላቸው ሐሰት ነው። ያስነሳቸዋል:: በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል:: አረጋግጧልም:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيُبَيِّنَ لَهُمُ ٱلَّذِى يَخْتَلِفُونَ فِيهِ وَلِيَعْلَمَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰذِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy39. የሚቀሰቅሳቸዉም ለእነርሱ ያንን የሚለያዩበትን ሊገልጽላቸውና እነዚያ የካዱትም እነርሱ ውሸታሞች የነበሩ መሆናቸውን እንዲያውቁ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَىْءٍ إِذَآ أَرَدْنَٰهُ أَن نَّقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

Amharic Translation - Africa Academy40. ለማንኛዉም ነገር መሆኑን በፈለግን ጊዜ ቃላችን ለእርሱ "ሁን" ማለት ብቻ ነው:: ወዲያዉም ይሆናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هَاجَرُوا۟ فِى ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مَا ظُلِمُوا۟ لَنُبَوِّئَنَّهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا حَسَنَةً وَلَأَجْرُ ٱلْـَٔاخِرَةِ أَكْبَرُ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy41. እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ መንገድ ላይ የተሰደዱ በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) እናሰፍራቸዋለን:: የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው:: (ከሓዲያን) ቢያውቁ ኖሮ (በተከተሏቸው ነበር)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ صَبَرُوا۟ وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy42. እነርሱ እነዚያ የታገሡና በጌታቸዉም ላይ የሚጠጉ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም:: (ሰዎች ሆይ! ) የማታውቁም ከሆናችሁ የዕውቀትን ባለቤቶችን ጠይቁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44. በግልጽ ማስረጃዎችና በመጽሐፍ ላክናቸው። ለሰዎችም ወደ እነርሱ የተወረደላቸውን ፍች ትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ወደ አንተ ቁርኣንን አወረድን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَأَمِنَ ٱلَّذِينَ مَكَرُوا۟ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن يَخْسِفَ ٱللَّهُ بِهِمُ ٱلْأَرْضَ أَوْ يَأْتِيَهُمُ ٱلْعَذَابُ مِنْ حَيْثُ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy45. እነዚያን መጥፎዎችን የዶለቱ ሰዎች አላህ በእነርሱ ምድርን የሚያስዉጣቸው ወይም ከማያውቁት ሥፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يَأْخُذَهُمْ فِى تَقَلُّبِهِمْ فَمَا هُم بِمُعْجِزِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. ወይም ከአገር ወደ አገር በሚዛወሩበት ጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ የሚይዛቸው መሆኑን አይፈሩምን? እነርሱም አሸናፊዎች አይደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يَأْخُذَهُمْ عَلَىٰ تَخَوُّفٍ فَإِنَّ رَبَّكُمْ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy47. ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን? ጌታችሁም ሩሕሩህና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَرَوْا۟ إِلَىٰ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ مِن شَىْءٍ يَتَفَيَّؤُا۟ ظِلَٰلُهُۥ عَنِ ٱلْيَمِينِ وَٱلشَّمَآئِلِ سُجَّدًا لِّلَّهِ وَهُمْ دَٰخِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. ወደዚያ ከማንኛዉም ነገር አላህ ወደ ፈጠረው ጥላዎቹ እነርሱም የተዋረዱ ሲሆኑ ለአላህ ሰጋጆች ሆነው ከቀኝ እና ከግራዎች ወደ ሚዛወሩት አላዩምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ مِن دَآبَّةٍ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. በሰማያትና በምድር ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መላዕክትም ለአላህ ብቻ ይሰግዳሉ:: እነርሱም አይኮሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَخَافُونَ رَبَّهُم مِّن فَوْقِهِمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50. ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል:: የታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ (ይፈጽማሉ):: {1}

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

Amharic Translation - Africa Academy51. አላህም አለ: «ሁለት አማልክት አትያዙ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔን ብቻ ፍሩኝ።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَلَهُ ٱلدِّينُ وَاصِبًا أَفَغَيْرَ ٱللَّهِ تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy52. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: አምልኮም ዘወትር ለርሱ ብቻ ነው:: ከአላህ ሌላ ያለን ትፈራላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ ٱللَّهِ ثُمَّ إِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فَإِلَيْهِ تَجْـَٔرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. ማንኛዉም በናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ብቻ ነው። ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደ እርሱ ብቻ ትጮሀላችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِذَا كَشَفَ ٱلضُّرَّ عَنكُمْ إِذَا فَرِيقٌ مِّنكُم بِرَبِّهِمْ يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy54. ከዚያም ከናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከናንተ የሆኑ ቡድኖች ወዲያውኑ በጌታችሁ ጣዖትን ያጋራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيَكْفُرُوا۟ بِمَآ ءَاتَيْنَٰهُمْ فَتَمَتَّعُوا۟ فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy55. የሚያጋሩትም በሰጠናቸው ሊክዱ ነው:: ተጠቀሙም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ታውቃላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَجْعَلُونَ لِمَا لَا يَعْلَمُونَ نَصِيبًا مِّمَّا رَزَقْنَٰهُمْ تَٱللَّهِ لَتُسْـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَفْتَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy56. ለማያውቁት ጣዖታትም ከሰጠናቸው ሲሳይ ድርሻን ያደርጋሉ:: በአላህ እምላለሁ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَجْعَلُونَ لِلَّهِ ٱلْبَنَٰتِ سُبْحَٰنَهُۥ وَلَهُم مَّا يَشْتَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. ለአላህ ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ። ጥራት ይገባው። ለእነርሱ ግን የሚፈልጉትን ያደርጋሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِٱلْأُنثَىٰ ظَلَّ وَجْهُهُۥ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy58. ከመሀከላቸው አንዱ በሴት ልጅ (መወለድ) በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ሆኖ ፊቱ ጠቁሮ ቅስሙ ይሰበራል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَتَوَٰرَىٰ مِنَ ٱلْقَوْمِ مِن سُوٓءِ مَا بُشِّرَ بِهِۦٓ أَيُمْسِكُهُۥ عَلَىٰ هُونٍ أَمْ يَدُسُّهُۥ فِى ٱلتُّرَابِ أَلَا سَآءَ مَا يَحْكُمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59. ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ሆኖም ቢሆን ይያዘውን? ወይስ በአፈር ውስጥ ይደብቀውን? በማለት እያምታታ ከሰዎች ይደበቃል:: የሚፈርዱት ፍርድ ምንኛ ከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ مَثَلُ ٱلسَّوْءِ وَلِلَّهِ ٱلْمَثَلُ ٱلْأَعْلَىٰ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy60. ለእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት ሰዎች ሁሉ መጥፎ መገለጫ አላቸው:: ለአላህ ግን ታላቅ መገለጫ አለው:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ يُؤَاخِذُ ٱللَّهُ ٱلنَّاسَ بِظُلْمِهِم مَّا تَرَكَ عَلَيْهَا مِن دَآبَّةٍ وَلَٰكِن يُؤَخِّرُهُمْ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَـْٔخِرُونَ سَاعَةً وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. አላህም ሰዎችን በበደላቸው ሁሉ በቀጣቸው ኖሮ በምድር ላይ ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባላስቀረ ነበር:: ግን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል:: ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይዘገዩም፤ አይቀድሙም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَجْعَلُونَ لِلَّهِ مَا يَكْرَهُونَ وَتَصِفُ أَلْسِنَتُهُمُ ٱلْكَذِبَ أَنَّ لَهُمُ ٱلْحُسْنَىٰ لَا جَرَمَ أَنَّ لَهُمُ ٱلنَّارَ وَأَنَّهُم مُّفْرَطُونَ

Amharic Translation - Africa Academy62. ለአላህም የሚጠሉትን ነገር ያደርጋሉ:: ለእነርሱም መልካሚቱ (ሀገር) እንዳለቻቸው በምላሶቻቸው ውሸትን ይናገራሉ:: ለእነርሱም እሳት ያለቻቸው መሆናቸውና እነርሱም ወደ እርሷ በቅድሚያ የሚነዱ መሆናቸው ጥርጥር የለበትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَٱللَّهِ لَقَدْ أَرْسَلْنَآ إِلَىٰٓ أُمَمٍ مِّن قَبْلِكَ فَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ أَعْمَٰلَهُمْ فَهُوَ وَلِيُّهُمُ ٱلْيَوْمَ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እንምላለን ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ ብዙ መልዕክተኞችን ልከናል:: ሰይጣንም ለእነርሱ ስራዎቻቸውን ሸለመላቸው:: ረዳታቸው ዛሬም እርሱ ነው:: ለእነርሱም ኋላ አሳማሚ ቅጣት አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَنزَلْنَا عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ إِلَّا لِتُبَيِّنَ لَهُمُ ٱلَّذِى ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ وَهُدًى وَرَحْمَةً لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በእርሱ የተለያዩበትን ለእነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ህዝቦች መሪና እዝነት ሊሆን እንጂ ባንተ ላይ መፅሀፉን አላወረድንም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَحْيَا بِهِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَآ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّقَوْمٍ يَسْمَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. አላህ ከሰማይ ውሃን አወረደ:: በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው አደረገ:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ لَكُمْ فِى ٱلْأَنْعَٰمِ لَعِبْرَةً نُّسْقِيكُم مِّمَّا فِى بُطُونِهِۦ مِنۢ بَيْنِ فَرْثٍ وَدَمٍ لَّبَنًا خَالِصًا سَآئِغًا لِّلشَّٰرِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy66. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ በግመል በከብት በፍየል አፈጣጠር አያሌ ምክር ሰጪ ትምህርት አለላችሁ:: በሆዶች ውስጥ ካለው ከፈርስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ጣፋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِن ثَمَرَٰتِ ٱلنَّخِيلِ وَٱلْأَعْنَٰبِ تَتَّخِذُونَ مِنْهُ سَكَرًا وَرِزْقًا حَسَنًا إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. ከዘንባባዎች ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፤ ከእርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሰራላችሁ (ታዘጋጃላችሁ):: በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى ٱلنَّحْلِ أَنِ ٱتَّخِذِى مِنَ ٱلْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ ٱلشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል (አስታወቀ) አስተማረ፡ «ከተራራዎች ከዛፍና ሰዎች ከሚሠሩት ቀፎ ቤቶችን ያዢ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ كُلِى مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ فَٱسْلُكِى سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا يَخْرُجُ مِنۢ بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَٰنُهُۥ فِيهِ شِفَآءٌ لِّلنَّاسِ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69. «ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ የጌታሽንም መንገዶች ለአንቺ የተገሩ ሲሆኑ ግቢ።» ከሆዶቿ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል:: በእርሱ ውስጥ ለሰዎች ፍቱን መድሀኒት አለበት። በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ተዓምር አለበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ خَلَقَكُمْ ثُمَّ يَتَوَفَّىٰكُمْ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرْذَلِ ٱلْعُمُرِ لِكَىْ لَا يَعْلَمَ بَعْدَ عِلْمٍ شَيْـًٔا إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy70. አላህም ፈጠራችሁ ከዚያ ይገድላችኋል:: ከናንተም መካከል ከእውቀት በኋላ ምንንም ነገር የማያውቅ ወደሚሆንበት የጃጀ እድሜ የሚመለስም ሰው አለ:: አላህ ሁሉን አዋቂ፤ በሁሉም ነገር ላይ ቻይም ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ فَضَّلَ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ فِى ٱلرِّزْقِ فَمَا ٱلَّذِينَ فُضِّلُوا۟ بِرَآدِّى رِزْقِهِمْ عَلَىٰ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُهُمْ فَهُمْ فِيهِ سَوَآءٌ أَفَبِنِعْمَةِ ٱللَّهِ يَجْحَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ:: እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዟቸው ባሮች ላይ እነርሱ በእርሱ ይስተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም:: ታዲያ በአላህ ጸጋ ለእርሱ ተጋሪ በማድረግ ይክዳሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا وَجَعَلَ لَكُم مِّنْ أَزْوَٰجِكُم بَنِينَ وَحَفَدَةً وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ أَفَبِٱلْبَٰطِلِ يُؤْمِنُونَ وَبِنِعْمَتِ ٱللَّهِ هُمْ يَكْفُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. አላህ ከነፍሶቻችሁ (ከጎሳዎቻችሁ) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ (የትዳር አጋሮችን ፈጠረ)፤ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ:: ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ:: ታዲያ በውሸት በጣኦት አምነው በአላህ ጸጋ ይክዳሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَمْلِكُ لَهُمْ رِزْقًا مِّنَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ شَيْـًٔا وَلَا يَسْتَطِيعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy73. ከአላህም ሌላ ከሰማያትና ከምድር ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውንና ምንንም የማይችሉትን እነርሱ ያመልካሉን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا تَضْرِبُوا۟ لِلَّهِ ٱلْأَمْثَالَ إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአላህ አምሳያዎችን አታድርጉ:: አላህ ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا عَبْدًا مَّمْلُوكًا لَّا يَقْدِرُ عَلَىٰ شَىْءٍ وَمَن رَّزَقْنَٰهُ مِنَّا رِزْقًا حَسَنًا فَهُوَ يُنفِقُ مِنْهُ سِرًّا وَجَهْرًا هَلْ يَسْتَوُۥنَ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy75. በምንም ላይ የማይችል ሆኖ በይዞታ (አለቃ ያለበት) የሆነውን ባሪያና መልካም ሲሳይን ሰጥተነው እርሱም ከእርሱ ከሰጠነው በሚስጥርና በግልጽ የሚለግሰውን ነፃ ሰው አላህ ለጣኦትና ለእርሱ ምሳሌ አደረገ:: ሁለቱ ይስተካከላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይሁን:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا رَّجُلَيْنِ أَحَدُهُمَآ أَبْكَمُ لَا يَقْدِرُ عَلَىٰ شَىْءٍ وَهُوَ كَلٌّ عَلَىٰ مَوْلَىٰهُ أَيْنَمَا يُوَجِّههُّ لَا يَأْتِ بِخَيْرٍ هَلْ يَسْتَوِى هُوَ وَمَن يَأْمُرُ بِٱلْعَدْلِ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy76. አላህ ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲያንና ለአማኞች) ምሳሌ አደረገ:: አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው:: እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው:: ወደ የትም ቢያዞረው ደግ ነገር አያመጣም:: እርሱና ያ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆኖ በማስተካከል (ፍትህ) የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ غَيْبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَآ أَمْرُ ٱلسَّاعَةِ إِلَّا كَلَمْحِ ٱلْبَصَرِ أَوْ هُوَ أَقْرَبُ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy77. በሰማያትና በምድር ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ብቻ ነው:: የሰዓቲቱም ነገር መምጣቷ እንደ ዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም:: ወይም ይበልጥ የቀረበ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّنۢ بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْـًٔا وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَٱلْأَفْـِٔدَةَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy78. አላህ ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ:: ታመሰግኑ ዘንድም ለእናንተ መስሚያንና ማያዎችን ልቦችንም አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَرَوْا۟ إِلَى ٱلطَّيْرِ مُسَخَّرَٰتٍ فِى جَوِّ ٱلسَّمَآءِ مَا يُمْسِكُهُنَّ إِلَّا ٱللَّهُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy79. ወደ በራሪዎችም በሰማይ አየር ውስጥ ለመብረር የተገሩ ሲሆኑ ከመውደቅ አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው መሆናቸውን አይመለከቱምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنۢ بُيُوتِكُمْ سَكَنًا وَجَعَلَ لَكُم مِّن جُلُودِ ٱلْأَنْعَٰمِ بُيُوتًا تَسْتَخِفُّونَهَا يَوْمَ ظَعْنِكُمْ وَيَوْمَ إِقَامَتِكُمْ وَمِنْ أَصْوَافِهَا وَأَوْبَارِهَا وَأَشْعَارِهَآ أَثَٰثًا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy80. አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን (ማረፊያን) አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ):: ከእንስሳዎችም ቆዳዎችን በጉዟችሁ ቀንም ሆነ በመቀመጫችሁ ቀን የምታቀሏቸውን ቤቶች (ዳሶች) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከበጓ ሱፎች፣ ከግመሏም ጠጉሮች፣ ከፍየሏም ጠጉሮች የቤት እቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን አደረገላችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّمَّا خَلَقَ ظِلَٰلًا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلْجِبَالِ أَكْنَٰنًا وَجَعَلَ لَكُمْ سَرَٰبِيلَ تَقِيكُمُ ٱلْحَرَّ وَسَرَٰبِيلَ تَقِيكُم بَأْسَكُمْ كَذَٰلِكَ يُتِمُّ نِعْمَتَهُۥ عَلَيْكُمْ لَعَلَّكُمْ تُسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy81. አላህ ከፈጠረው ነገር ለእናንተ ጥላዎችን ፈጠረላችሁ:: ከጋራዎችም መከለያዎችን ፈጠረላችሁ:: ሐሩርንም ብርድንም የሚጠብቋችሁን ልብሶች፤ የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች ፈጠረላችሁ:: ልክ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በእናንተ ላይ ይሞላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنَّمَا عَلَيْكَ ٱلْبَلَٰغُ ٱلْمُبِينُ

Amharic Translation - Africa Academy82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስላም ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَعْرِفُونَ نِعْمَتَ ٱللَّهِ ثُمَّ يُنكِرُونَهَا وَأَكْثَرُهُمُ ٱلْكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy83. የአላህን ጸጋ ያውቃሉ:: ሆኖም ከዚያ ይክዷታል:: አብዛኞቻቸዉም ከሓዲያን ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ نَبْعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا ثُمَّ لَا يُؤْذَنُ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَلَا هُمْ يُسْتَعْتَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy84. ከየህዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ:: ከዚያ ለእነዚያ ለካዱት ንግግር አይፈቀድላቸዉም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ ٱلْعَذَابَ فَلَا يُخَفَّفُ عَنْهُمْ وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy85. እነዚያ የበደሉ ሰዎች ቅጣትን ባዩ ጊዜ ለእነርሱ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጣቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ شُرَكَآءَهُمْ قَالُوا۟ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ شُرَكَآؤُنَا ٱلَّذِينَ كُنَّا نَدْعُوا۟ مِن دُونِكَ فَأَلْقَوْا۟ إِلَيْهِمُ ٱلْقَوْلَ إِنَّكُمْ لَكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy86. እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች ተጋሪዎቻቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ ካንተ ሌላ እናመልካቸው የነበሩ ተጋሪዎቻችን ናቸው።» ይላሉ። አማልክቶችም «ውሸታሞች ናችሁ።» በማለት ቃሉን ወደ እነርሱው መልሰው ይወረውራሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَلْقَوْا۟ إِلَى ٱللَّهِ يَوْمَئِذٍ ٱلسَّلَمَ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy87. አጋሪዎቹ በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَصَدُّوا۟ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ زِدْنَٰهُمْ عَذَابًا فَوْقَ ٱلْعَذَابِ بِمَا كَانُوا۟ يُفْسِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy88. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ نَبْعَثُ فِى كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا عَلَيْهِم مِّنْ أَنفُسِهِمْ وَجِئْنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ تِبْيَٰنًا لِّكُلِّ شَىْءٍ وَهُدًى وَرَحْمَةً وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየህዝቡ ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በራሳቸው ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትንና አንተንም በእነዚህ ሕዝቦች ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣብህን ቀን አስታውስ:: መጽሐፉንም ለሁሉም ነገር አብራሪ፤ መመሪያ፣ እዝነትና ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ يَأْمُرُ بِٱلْعَدْلِ وَٱلْإِحْسَٰنِ وَإِيتَآئِ ذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ ٱلْفَحْشَآءِ وَٱلْمُنكَرِ وَٱلْبَغْىِ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy90. አላህ በማስተካከል (በፍትህ) ፤ በማሳመር (በመልካም ሥራ) እና ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል። ከአስከፊ (ጸያፍ ነገር) ከማመንዘር፤ ከሚጠላ ነገር ሁሉ ከመበደልም ይከለክላል:: ትገነዘቡ ዘንድ ይገሥጻችኋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَوْفُوا۟ بِعَهْدِ ٱللَّهِ إِذَا عَٰهَدتُّمْ وَلَا تَنقُضُوا۟ ٱلْأَيْمَٰنَ بَعْدَ تَوْكِيدِهَا وَقَدْ جَعَلْتُمُ ٱللَّهَ عَلَيْكُمْ كَفِيلًا إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy91. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ:: መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላና አላህን በእናንተ ላይ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትሆኑ አታፍርሱ:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّتِى نَقَضَتْ غَزْلَهَا مِنۢ بَعْدِ قُوَّةٍ أَنكَٰثًا تَتَّخِذُونَ أَيْمَٰنَكُمْ دَخَلًۢا بَيْنَكُمْ أَن تَكُونَ أُمَّةٌ هِىَ أَرْبَىٰ مِنْ أُمَّةٍ إِنَّمَا يَبْلُوكُمُ ٱللَّهُ بِهِۦ وَلَيُبَيِّنَنَّ لَكُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ مَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy92. ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ ሕዝብ ከሌላይቱ ሕዝብ የበዛች ለመሆንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትሆኑ እንደዚያች ፈትሏን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው ሴት አትሁኑ:: አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር በእርግጥ ያብራራላችኋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمْ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَلَٰكِن يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِى مَن يَشَآءُ وَلَتُسْـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy93. አላህ በፈለገ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የሚሻውን ሰው ያቀናል:: ትሠሩት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَتَّخِذُوٓا۟ أَيْمَٰنَكُمْ دَخَلًۢا بَيْنَكُمْ فَتَزِلَّ قَدَمٌۢ بَعْدَ ثُبُوتِهَا وَتَذُوقُوا۟ ٱلسُّوٓءَ بِمَا صَدَدتُّمْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَكُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy94. ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳያንዳልጡ ከአላህ መንገድ በመከልከላችሁ ምክንያት ቅጣትንም እንዳትቀምሱ መሓሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አታድርጉት:: ለእናንተም ያን ጊዜ ታላቅ ቅጣት አላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَشْتَرُوا۟ بِعَهْدِ ٱللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا إِنَّمَا عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy95. በአላህ ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ። የምታውቁ ብትሆኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا عِندَكُمْ يَنفَدُ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ بَاقٍ وَلَنَجْزِيَنَّ ٱلَّذِينَ صَبَرُوٓا۟ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy96. እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል:: አላህ ዘንድ ያለው ግን ለዘለዓለም ቀሪ ነው (አያልቅም):: እነዚያንም የታገሡትን ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَنْ عَمِلَ صَٰلِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةً طَيِّبَةً وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy97. ከወንድም ይሁን ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ ሁሉ መልካም ኑሮን እናኖረዋለን:: ይሠሩት ከነበሩት ነገር በመልካሙም ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا قَرَأْتَ ٱلْقُرْءَانَ فَٱسْتَعِذْ بِٱللَّهِ مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy98. ቁርኣንንም ለማንበብ ባሰብክ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ لَيْسَ لَهُۥ سُلْطَٰنٌ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy99. እርሱ በእነዚያ በትክክል ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ሥልጣን የለዉምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا سُلْطَٰنُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَوَلَّوْنَهُۥ وَٱلَّذِينَ هُم بِهِۦ مُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy100. ሥልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ ምክንያት አጋሪዎች በሆኑት ላይ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا بَدَّلْنَآ ءَايَةً مَّكَانَ ءَايَةٍ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوٓا۟ إِنَّمَآ أَنتَ مُفْتَرٍۭ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአንቀጽም ስፍራ ሌላ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው:: «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም።» ይላሉ:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلْحَقِّ لِيُثَبِّتَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር ቁርኣንን ጂብሪል እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّهُمْ يَقُولُونَ إِنَّمَا يُعَلِّمُهُۥ بَشَرٌ لِّسَانُ ٱلَّذِى يُلْحِدُونَ إِلَيْهِ أَعْجَمِىٌّ وَهَٰذَا لِسَانٌ عَرَبِىٌّ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy103. እነርሱም «እርሱን ቁርኣንን የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው።» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን:: የዚያ ወደ እርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐረበኛ ያልሆነ ዐጀምኛ ነው:: ይህ ቁርኣን ግን በግልጽ በዐረብኛ ቋንቋ የተነገረ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ لَا يَهْدِيهِمُ ٱللَّهُ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy104. እነዚያን በአላህ አናቅጽ የማያምኑትን አላህ አይመራቸዉም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا يَفْتَرِى ٱلْكَذِبَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy105. ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አናቅጽ የማያምኑት ብቻ ናቸው:: እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَن كَفَرَ بِٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ إِيمَٰنِهِۦٓ إِلَّا مَنْ أُكْرِهَ وَقَلْبُهُۥ مُطْمَئِنٌّۢ بِٱلْإِيمَٰنِ وَلَٰكِن مَّن شَرَحَ بِٱلْكُفْرِ صَدْرًا فَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy106. ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው ብርቱ ቅጣት አለው። ልቡ በእምነት የረካ ሆኖ በክሕደት ቃል ለመናገር የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር:: ግን ልባቸውን በክሕደት የከፈቱ ሰዎች ከአላህ ቁጣ አለባቸው:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ ٱسْتَحَبُّوا۟ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا عَلَى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy107. ይህ ቅጣት እነርሱ ቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሓዲያንን ሕዝቦች የማያቀና በመሆኑ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَسَمْعِهِمْ وَأَبْصَٰرِهِمْ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْغَٰفِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy108. እነዚያ እነርሱ በልቦቻቸው፤ በዓይኖቻቸውና በጆሮቻቸዉም ላይ አላህ ያተመባቸው ናቸው:: እነዚያም ዝንጉዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا جَرَمَ أَنَّهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy109. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከሳሪዎቹ እነርሱ ለመሆናቸው ጥርጥር የለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ هَاجَرُوا۟ مِنۢ بَعْدِ مَا فُتِنُوا۟ ثُمَّ جَٰهَدُوا۟ وَصَبَرُوٓا۟ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ ከተፈተኑ በኋላ ለተሰደዱት ከዚያም ለታገሉትና ለታገሡት ሁሉ ጌታህም ከፈተናዋ በኋላ በእርግጥ መሐሪና አዛኝ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ تَأْتِى كُلُّ نَفْسٍ تُجَٰدِلُ عَن نَّفْسِهَا وَتُوَفَّىٰ كُلُّ نَفْسٍ مَّا عَمِلَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ሆና የምትመጣበትን ነፍስም ሁሉ የሠራችውን ዋጋ የምትቀበልበትን ቀን (አስታውስ):: እነርሱም ፈጹሞ አይበደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا قَرْيَةً كَانَتْ ءَامِنَةً مُّطْمَئِنَّةً يَأْتِيهَا رِزْقُهَا رَغَدًا مِّن كُلِّ مَكَانٍ فَكَفَرَتْ بِأَنْعُمِ ٱللَّهِ فَأَذَٰقَهَا ٱللَّهُ لِبَاسَ ٱلْجُوعِ وَٱلْخَوْفِ بِمَا كَانُوا۟ يَصْنَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy112. አላህ ጸጥተኛ የረካች ሲሳይዋ ሰፊ ሆኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና ከዚያም በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት የረሀብንና የፍርሀትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ ምሳሌ አደረገ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ جَآءَهُمْ رَسُولٌ مِّنْهُمْ فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمُ ٱلْعَذَابُ وَهُمْ ظَٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy113. ከእነርሱም ውስጥ የሆነ መልዕክተኛም በእርግጥ መጣላቸው:: አስተባበሉትም እነርሱም በዳዬች ሆነው ቅጣቱ ያዛቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكُلُوا۟ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ حَلَٰلًا طَيِّبًا وَٱشْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy114. አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደና ንጹሕ ሲሆን ብሉ:: የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትገዙት ከሆናችሁ አመስግኑት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ ٱلْمَيْتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحْمَ ٱلْخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ لِغَيْرِ ٱللَّهِ بِهِۦ فَمَنِ ٱضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy115. በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋ፣ ያንንም በሚታረድ ጊዜ በእርሱ ላይ ከአላህ ስም ሌላ የተወሳበትን ብቻ ነው:: አመጸኛና ወሰን አላፊም ሳይሆን ከእነዚህ አንዱን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَقُولُوا۟ لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ ٱلْكَذِبَ هَٰذَا حَلَٰلٌ وَهَٰذَا حَرَامٌ لِّتَفْتَرُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ لَا يُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy116. (ሰዎች ሆይ) በአላህ ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህ ደግሞ እርም ነው» አትበሉ:: እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ክፍሎች በፍጹም አይድኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَتَٰعٌ قَلِيلٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy117. ጥቂት መጣቀም ብቻ አለላቸው:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَلَى ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ حَرَّمْنَا مَا قَصَصْنَا عَلَيْكَ مِن قَبْلُ وَمَا ظَلَمْنَٰهُمْ وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ አይሁድ በሆኑት ሰዎች ላይ ከአሁን በፊት ባንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል:: እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ራሳቸው ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا۟ ٱلسُّوٓءَ بِجَهَٰلَةٍ ثُمَّ تَابُوا۟ مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوٓا۟ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy119. ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ በስህተት መጥፎን ለሠሩትና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ إِبْرَٰهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy120. ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ፤ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ህዝብ ነበር:: ከአጋሪዎችም አልነበረም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

شَاكِرًا لِّأَنْعُمِهِ ٱجْتَبَىٰهُ وَهَدَىٰهُ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy121. ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር:: መረጠው:: ወደ ቀጥተኛዉም መንገድ መራው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَاتَيْنَٰهُ فِى ٱلدُّنْيَا حَسَنَةً وَإِنَّهُۥ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ لَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy122. በቅርቢቱም ዓለም በጎ ነገርን ሰጠነው:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም በእርግጥ ከመልካሞቹ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ أَنِ ٱتَّبِعْ مِلَّةَ إِبْرَٰهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy123. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን ተከተል:: ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለትን ወደ አንተ አወረድን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا جُعِلَ ٱلسَّبْتُ عَلَى ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُوا۟ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቅዳሜ ቀን መስራት ክልክል የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በትንሳኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy125. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ በለዘብተኛ ቃልም ሰዎችን ጥራ:: በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው ዘዴ ተከራከራቸው:: ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው:: እንደዚሁም እርሱ ቅን የሆኑትን ሰዎች አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنْ عَاقَبْتُمْ فَعَاقِبُوا۟ بِمِثْلِ مَا عُوقِبْتُم بِهِۦ وَلَئِن صَبَرْتُمْ لَهُوَ خَيْرٌ لِّلصَّٰبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy126. (ሙስሊሞች ሆይ!) ብትበቀሉም በእርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ:: ብትታገሱ ግን እርሱ ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱصْبِرْ وَمَا صَبْرُكَ إِلَّا بِٱللَّهِ وَلَا تَحْزَنْ عَلَيْهِمْ وَلَا تَكُ فِى ضَيْقٍ مِّمَّا يَمْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስ:: መታገስህ በአላህ ማስቻል ብቻ እንጂ አይደለም:: በእነርሱም ላይ ባያምኑ አትተክዝ:: ባንተ ላይ በሚመክሩት ተንኮልም በጭንቀት ውስጥ አትሁን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوا۟ وَّٱلَّذِينَ هُم مُّحْسِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy128. አላህ ከእነዚያ እነርሱ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነርሱ ከመልካም ሠሪ ከሆኑት ሰዎች ጋር ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70