ሱረቱ Al-A'raaf الأعراف
206 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓصٓ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤ ሷድ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كِتَٰبٌ أُنزِلَ إِلَيْكَ فَلَا يَكُن فِى صَدْرِكَ حَرَجٌ مِّنْهُ لِتُنذِرَ بِهِۦ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ልታስጠነቅቅበትና ለምእመናንም መገሰጫ እንዲሆን ወደ አንተ የተወረደ ቁርኣን ነው:: ስለዚህ ልብህ ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. (ሰዎች ሆይ! ) ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደላችሁን መልዕክት ተከተሉ:: ከአላህ ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ:: ጥቂትን ብቻ ትገሰፃላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَم مِّن قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَٰهَا فَجَآءَهَا بَأْسُنَا بَيَٰتًا أَوْ هُمْ قَآئِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. ከከተማ (ሰዎች) መካከል ልናጠፋቸው የፈለግነውንና ወዲያውኑ ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ህዝቦች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَا كَانَ دَعْوَىٰهُمْ إِذْ جَآءَهُم بَأْسُنَآ إِلَّآ أَن قَالُوٓا۟ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy5. ቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ ጸሎታቸው «እኛ በደለኞች ነበርን።» ከማለት በስተቀር ሌላ አልነበረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَنَسْـَٔلَنَّ ٱلَّذِينَ أُرْسِلَ إِلَيْهِمْ وَلَنَسْـَٔلَنَّ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy6. ከዚያ ወደ እነርሱ የተላከባቸውን ህዝቦችና መልዕክተኞቹንም እንጠይቃቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَنَقُصَّنَّ عَلَيْهِم بِعِلْمٍ وَمَا كُنَّا غَآئِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy7. ከዚያም በእነርሱ ላይ የነበሩትን ሁሉ ከእውቀት ጋር እንተርክላቸዋለን:: ከእነርሱ የራቅን አልነበርንምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْوَزْنُ يَوْمَئِذٍ ٱلْحَقُّ فَمَن ثَقُلَتْ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. የዚያን ቀኑ ሚዛን ትክክለኛ ነው:: እናም እነዚያ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸውም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ እነርሱ ብቻ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنْ خَفَّتْ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُم بِمَا كَانُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9. እነዚያ ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸውም በአናቅጻችን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ مَكَّنَّٰكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ وَجَعَلْنَا لَكُمْ فِيهَا مَعَٰيِشَ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy10. (ሰዎች ሆይ! ) በምድር ላይ በእርግጥም አስመቸናችሁ:: በእርሷም ላይ ለእናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ። ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ خَلَقْنَٰكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَٰكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَٰٓئِكَةِ ٱسْجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوٓا۟ إِلَّآ إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ ٱلسَّٰجِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy11. በእርግጥም ፈጠርናችሁ:: ከዚያም ቀረጽናችሁ:: ከዚያም ለመላዕክት « ለአደም ስገዱ።» አልን:: ወዲያዉም ሁሉም ሰገዱ:: ኢብሊስ ብቻ ሲቀር:: እሱማ ከሰጋጆቹ አልሆነም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ قَالَ أَنَا۠ خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِى مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُۥ مِن طِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy12. አላህም «ዲያብሎስ ሆይ! ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው:: ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ:: እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَٱهْبِطْ مِنْهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَٱخْرُجْ إِنَّكَ مِنَ ٱلصَّٰغِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. (አላህም) «ከእርሷ ውረድ:: በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና:: ውጣም:: አንተ ከወራዶቹ ነህና።» አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَنظِرْنِىٓ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. (ኢብሊስም): «እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّكَ مِنَ ٱلْمُنظَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy15. አላህ «አንተ ከሚቆዩት ነህ።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَبِمَآ أَغْوَيْتَنِى لَأَقْعُدَنَّ لَهُمْ صِرَٰطَكَ ٱلْمُسْتَقِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy16. (ኢብሊስም) አለ: «ስላጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ لَـَٔاتِيَنَّهُم مِّنۢ بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَٰنِهِمْ وَعَن شَمَآئِلِهِمْ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy17. «ከዚያም ከበስተፊቶቻቸው፤ ከየኋላቸዉም፤ ከየቀኞቻቸውና ከየግራዎቻቸዉም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ:: አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ሆነው አታገኛቸዉም።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱخْرُجْ مِنْهَا مَذْءُومًا مَّدْحُورًا لَّمَن تَبِعَكَ مِنْهُمْ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy18. «የተጠላህ ብራሪ ስትሆን ከእርሷ ውጣ:: ከእነርሱ መካከልም አንተን ከተከተሉህ እና አንተንም ሁላችሁንም ገሀነምን በእርግጥ በእናንተ እሞላታለሁ።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰٓـَٔادَمُ ٱسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ ٱلْجَنَّةَ فَكُلَا مِنْ حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy19. ‹‹አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ እንደፈለጋችሁ ተመገቡ:: ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ:: ራሳቸውን ከሚበድሉት ትሆናላችሁና።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَوَسْوَسَ لَهُمَا ٱلشَّيْطَٰنُ لِيُبْدِىَ لَهُمَا مَا وُۥرِىَ عَنْهُمَا مِن سَوْءَٰتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَىٰكُمَا رَبُّكُمَا عَنْ هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةِ إِلَّآ أَن تَكُونَا مَلَكَيْنِ أَوْ تَكُونَا مِنَ ٱلْخَٰلِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy20. ሰይጣንም ከሀፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው። «ጌታችሁ እኮ መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ከዘላለም ኗዋሪዎቹ እንዳትሆኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّى لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy21. «እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሯችሁ ነኝ።» ሲልም ማለላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَدَلَّىٰهُمَا بِغُرُورٍ فَلَمَّا ذَاقَا ٱلشَّجَرَةَ بَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ وَنَادَىٰهُمَا رَبُّهُمَآ أَلَمْ أَنْهَكُمَا عَن تِلْكُمَا ٱلشَّجَرَةِ وَأَقُل لَّكُمَآ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ لَكُمَا عَدُوٌّ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy22. በማታለልም አዋረዳቸው:: ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ሀፍረተ ገላቸው የሁለቱም ተገለጠባቸው:: ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ (ይለጥፉ) ጀመር:: ጌታቸዉም «ይህችን ዛፍ አልከለከልኳችሁም ነበርን? ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁም ነበርን?» ሲል ጠራቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَآ أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy23. «ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን:: ባትምረንና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱهْبِطُوا۟ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ وَلَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy24. (አላህም) «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ከዚህ ዉጡ ወደ ምድር ውረዱ:: ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فِيهَا تَحْيَوْنَ وَفِيهَا تَمُوتُونَ وَمِنْهَا تُخْرَجُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. «በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ:: በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ:: ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ قَدْ أَنزَلْنَا عَلَيْكُمْ لِبَاسًا يُوَٰرِى سَوْءَٰتِكُمْ وَرِيشًا وَلِبَاسُ ٱلتَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ ذَٰلِكَ مِنْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy26. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስና ጌጥን በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን:: አላህን የመፍራትም ልብስም እርሱ የተሻለ ነው:: ይህ ከአላህ ተዓምራት ነው:: ይገሰጹ ዘንድ አወረደላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ لَا يَفْتِنَنَّكُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ كَمَآ أَخْرَجَ أَبَوَيْكُم مِّنَ ٱلْجَنَّةِ يَنزِعُ عَنْهُمَا لِبَاسَهُمَا لِيُرِيَهُمَا سَوْءَٰتِهِمَآ إِنَّهُۥ يَرَىٰكُمْ هُوَ وَقَبِيلُهُۥ مِنْ حَيْثُ لَا تَرَوْنَهُمْ إِنَّا جَعَلْنَا ٱلشَّيَٰطِينَ أَوْلِيَآءَ لِلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባታችሁንና እናታችሁን ሀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከእነርሱ የገፈፋቸው ሲሆን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተንም አይሞክራችሁ:: እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ሁነው ያያቹሀልና: እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا فَعَلُوا۟ فَٰحِشَةً قَالُوا۟ وَجَدْنَا عَلَيْهَآ ءَابَآءَنَا وَٱللَّهُ أَمَرَنَا بِهَا قُلْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَأْمُرُ بِٱلْفَحْشَآءِ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ፡- «በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን:: አላህም በእርሷ አዞናል።» ይላሉ። «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፤ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَمَرَ رَبِّى بِٱلْقِسْطِ وَأَقِيمُوا۟ وُجُوهَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَٱدْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ كَمَا بَدَأَكُمْ تَعُودُونَ
Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ በማስተካከል በፍትህ አዘዘ:: በየመስገጃ ቦታ ዘንድም ፊቶቻችሁን እርሱን ለመገዛት አስተካክሉ:: ሃይማኖትንም ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርጋችሁ አምልኩት:: መጀመሪያ እርሱ እንደፈጠራችሁ በመጨረሻም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁና።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ ٱلضَّلَٰلَةُ إِنَّهُمُ ٱتَّخَذُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينَ أَوْلِيَآءَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ:: ከፊሎቹ ደግሞ በእነርሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል:: እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና:: እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ እንደሆኑ ያስባሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ خُذُوا۟ زِينَتَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَكُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ وَلَا تُسْرِفُوٓا۟ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْمُسْرِفِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን ጌጦቻችሁን በየመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ:: ብሉም ጠጡም:: ግን አታባክኑ:: እርሱ (አላህ) አባካኞችን አይወድምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ مَنْ حَرَّمَ زِينَةَ ٱللَّهِ ٱلَّتِىٓ أَخْرَجَ لِعِبَادِهِۦ وَٱلطَّيِّبَٰتِ مِنَ ٱلرِّزْقِ قُلْ هِىَ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا خَالِصَةً يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያችን ለባሮች የፈጠራትን የአላህን ጌጥ ከሲሳይ ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው?» በላቸው። «እርሷ በትንሳኤ ቀን ለነዚያ በትክክል ላመኑት ብቻ ስትሆን በቅርቢቱ ህይወትም ተገቢያቸው ናት።» በላቸው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّىَ ٱلْفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَٱلْإِثْمَ وَٱلْبَغْىَ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا۟ بِٱللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِۦ سُلْطَٰنًا وَأَن تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እርም ያደረገው የተገለጸም ሆነ የተደበቀን መጥፎ ስራን፣ ኃጢአትን፤ ያለ አግባብ መበደልንም፣ በእርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን ጣኦት በአላህ ማጋራታችሁንና በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው። እናም ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትንም ሰዓት አይዘገዩም። ከጊዜያቱም አይቀድሙም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ إِمَّا يَأْتِيَنَّكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتِى فَمَنِ ٱتَّقَىٰ وَأَصْلَحَ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. (የአደም ልጆች ሆይ!) ከናንተ መካከል አንቀፆቼን የሚያነቡላችሁ መልዕክተኞች ቢመጡላችሁ ከናንተ ክህደትን የተጠነቀቁና በጎንም ተግባር የሠሩ ሁሉ ምንም ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም አያዝኑምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسْتَكْبَرُوا۟ عَنْهَآ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. እነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉና ከእርሷ የኮሩ ሁሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓ أُو۟لَٰٓئِكَ يَنَالُهُمْ نَصِيبُهُم مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوٓا۟ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ قَالُوا۟ ضَلُّوا۟ عَنَّا وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአናቅጹ ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነዚያ ከተጻፈላቸው ከመጽሐፉ ውስጥ ሲሆን ድርሻቸው ያገኛቸዋል:: የሞት መልዕክተኞቻችንም የሚገድሏቸው ሆነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል:: «ከእኛ ተሰወሩብን» ይላሉ:: እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱدْخُلُوا۟ فِىٓ أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُم مِّنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ فِى ٱلنَّارِ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا حَتَّىٰٓ إِذَا ٱدَّارَكُوا۟ فِيهَا جَمِيعًا قَالَتْ أُخْرَىٰهُمْ لِأُولَىٰهُمْ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ أَضَلُّونَا فَـَٔاتِهِمْ عَذَابًا ضِعْفًا مِّنَ ٱلنَّارِ قَالَ لِكُلٍّ ضِعْفٌ وَلَٰكِن لَّا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy38. «ከጋኔንና ከሰዉም ከናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ።» ይላቸዋል:: አንዲቱ ቡድን ህዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን ብጤዋን ቡድን ትረግማለች:: መላዉም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙ ጊዜ የኋለኛይቱ (ተከታዮች) ቡድን ለመጀመሪያይቱ (ለአስከታዮች) ቡድን፡- «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው።» ትላለች:: አላህም፡- «ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም።» ይላቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَتْ أُولَىٰهُمْ لِأُخْرَىٰهُمْ فَمَا كَانَ لَكُمْ عَلَيْنَا مِن فَضْلٍ فَذُوقُوا۟ ٱلْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. መጀመሪያይቱ ቡድንም ለኋለኛይቱ ቡድን «ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም ትላለች:: ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይሏቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسْتَكْبَرُوا۟ عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلْجَمَلُ فِى سَمِّ ٱلْخِيَاطِ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy40. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉና ከእርሷም የኮሩ ሁሉ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸዉም:: ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባ ድረስም ወደ ገነት አይገቡም:: ልክ እንደዚሁ አመጸኞችን እንቀጣለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَهُم مِّن جَهَنَّمَ مِهَادٌ وَمِن فَوْقِهِمْ غَوَاشٍ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy41. ለእነርሱም በሥራቸው ምክንያት ከገሀነም እሳት ምንጣፍ ከበላያቸዉም የእሳት መሸፈኛዎች አሉባቸው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَآ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካሞችን የሰሩ ማንኛውንም ነፍስ የችሎታዋን እንጂ አናስገድድም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَزَعْنَا مَا فِى صُدُورِهِم مِّنْ غِلٍّ تَجْرِى مِن تَحْتِهِمُ ٱلْأَنْهَٰرُ وَقَالُوا۟ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى هَدَىٰنَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهْتَدِىَ لَوْلَآ أَنْ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ لَقَدْ جَآءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلْحَقِّ وَنُودُوٓا۟ أَن تِلْكُمُ ٱلْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ጥላቻም እናስወግዳለን:: ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ:: «ለዚያም ወደዚህ ላደረሰን ሥራ ለመራን ለአላህ ብቻ ምስጋና ይገባው:: አላህ ባልመራን ኖሮ ወደዚህ አንመራም ነበር:: የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት ላይ ሲሆኑ መጥተውልናል።» ይላሉ:: «ይህ ገነት ትሠሩት በነበራችሁት እንድትወርሱት የተደረጋችሁት ነው።» በማለት ይጠራሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَادَىٰٓ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ أَصْحَٰبَ ٱلنَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا قَالُوا۟ نَعَمْ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌۢ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy44. የገነት ሰዎች የእሳት ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ሆኖ አገኘን እናንተስ ጌታችሁ የዛተባችሁን እውነት ሆኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ ይጣራሉ:: የእሳት ሰዎችም «አዎን አገኘን» ይላሉ:: በመካከላቸዉም «የአላህ እርግማን በበደለኞች ላይ ይሁን» ሲል አዋጅ ነጋሪ ያውጃል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا وَهُم بِٱلْـَٔاخِرَةِ كَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy45. በደለኞች ማለት እነዚያ ከአላህ መንገድ ሌሎችን ክፍሎች የሚከለክሉና የአላህ መንገድ እንድትጣመም የሚፈልጉ በመጨረሻዋ ዓለም ከሓዲያን የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ وَعَلَى ٱلْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّۢا بِسِيمَىٰهُمْ وَنَادَوْا۟ أَصْحَٰبَ ٱلْجَنَّةِ أَن سَلَٰمٌ عَلَيْكُمْ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy46. በገነት ሰዎችና በገሀነም ሰዎች መካከል አዕራፍ የሚባል ከባድ መጋረጃ አለ:: በአዕራፍ ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ:: የገነትን ሰዎችን «ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት ይጣራሉ:: የአዕራፍ ሰዎች ገነት መግባትን የሚከጅሉ ሲሆኑ ገና እንዲገቡ አልተደረጉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا صُرِفَتْ أَبْصَٰرُهُمْ تِلْقَآءَ أَصْحَٰبِ ٱلنَّارِ قَالُوا۟ رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy47. ዓይኖቻቸው ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜም፡- «ጌታችን ሆይ! እባክህ ከበደለኞች ጋር አታድርገን።» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَادَىٰٓ أَصْحَٰبُ ٱلْأَعْرَافِ رِجَالًا يَعْرِفُونَهُم بِسِيمَىٰهُمْ قَالُوا۟ مَآ أَغْنَىٰ عَنكُمْ جَمْعُكُمْ وَمَا كُنتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy48. የአዕራፍ ሰዎች በምልክታቸው የሚያውቋቸውን ታላላቅ ሰዎች ይጠራሉ:: «ክምችታችሁና (ብዛታችሁና) ኩራታችሁ ምን ጠቀማችሁ?» ይሏቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَهَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقْسَمْتُمْ لَا يَنَالُهُمُ ٱللَّهُ بِرَحْمَةٍ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمْ وَلَآ أَنتُمْ تَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy49. «እነዚያ የአላህ ችሮታው አይደርሳቸዉም ብላችሁ የማላችሁት ወገኖች ናቸውን? ገነትን ግቡ:: (አሁን ግን) ፍርሃት የለባችሁም:: እናንተም አታዝኑም።» (ተባሉ ይሏቸዋል::)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَادَىٰٓ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ أَصْحَٰبَ ٱلْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا۟ عَلَيْنَا مِنَ ٱلْمَآءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy50. የእሳት ሰዎች የገነት ሰዎችን «በእኛ ላይ ውሃ ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ እባካችሁ ጣሉልን (አፍስሱልን)።» ብለው ይጠሯቸዋል:: የገነት ሰዎችም «እነዚህ ሲሳዮች እኮ አላህ በከሓዲያን ላይ እርም አድርጓቸዋል።» ይሏቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ دِينَهُمْ لَهْوًا وَلَعِبًا وَغَرَّتْهُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا فَٱلْيَوْمَ نَنسَىٰهُمْ كَمَا نَسُوا۟ لِقَآءَ يَوْمِهِمْ هَٰذَا وَمَا كَانُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا يَجْحَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy51. ለእነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙና የቅርቢቱ ህይወት ያታለለቻቸው የዚህን ቀን መገናኘታቸውን እንደ ረሱና በተአምራታችን ይክዱ እንደ ነበሩ ሁሉ ዛሬ እኛም እንረሳቸዋለን (እንተዋቸዋለን)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ جِئْنَٰهُم بِكِتَٰبٍ فَصَّلْنَٰهُ عَلَىٰ عِلْمٍ هُدًى وَرَحْمَةً لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy52. ከእውቀት ጋር የዘረዘርነው የሆነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ህዝቦች መመሪያና እዝነት ሲሆን አመጣንላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأْوِيلَهُۥ يَوْمَ يَأْتِى تَأْوِيلُهُۥ يَقُولُ ٱلَّذِينَ نَسُوهُ مِن قَبْلُ قَدْ جَآءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلْحَقِّ فَهَل لَّنَا مِن شُفَعَآءَ فَيَشْفَعُوا۟ لَنَآ أَوْ نُرَدُّ فَنَعْمَلَ غَيْرَ ٱلَّذِى كُنَّا نَعْمَلُ قَدْ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy53. የዛቻውን ፍጻሜዉን እንጂ ሌላ ይጠባበቃሉን? (አይጠባበቁም):: ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን ግን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት መጥተዋል። ለእኛስ ያማልዱን ዘንድ አማላጆች አሉን? ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው የተለየ ስራ እንድንሰራ ዘንድ ዕድሉ ይሰጠናልን?» ይላሉ:: በእርግጥም ራሳቸውን ይከስራሉ:: ይቀጥፉት የነበረው ሁሉ ከንቱ ሆኖ ያገኙታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ يُغْشِى ٱلَّيْلَ ٱلنَّهَارَ يَطْلُبُهُۥ حَثِيثًا وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ وَٱلنُّجُومَ مُسَخَّرَٰتٍۭ بِأَمْرِهِۦٓ أَلَا لَهُ ٱلْخَلْقُ وَٱلْأَمْرُ تَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy54. (ሰዎች ሆይ) ጌታችሁ አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረና ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው። ቀኑንም በሌሊቱ ይሸፍነዋል:: ሁለቱም እርስ በእርስ በፍጥነት ይፈላለጋሉ:: ጸሐይ ጨረቃና ከዋክብት በትዕዛዙ የተገሩ ናቸው። አስተውሉ! መፍጠርም ማዘዝም የእርሱ (የአላህ) ነው:: የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ክብሩ ላቀ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱدْعُوا۟ رَبَّكُمْ تَضَرُّعًا وَخُفْيَةً إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْمُعْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy55. ጌታችሁን ተናንሳችሁና ተዋርዳችሁ በድብቅ ለምኑት:: እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَٰحِهَا وَٱدْعُوهُ خَوْفًا وَطَمَعًا إِنَّ رَحْمَتَ ٱللَّهِ قَرِيبٌ مِّنَ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy56. ምድር ከተበጀች በኋላ አታበላሿት:: አላህን ፈርታችሁና ከጅላችሁ ተገዙት:: የአላህ እዝነት ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ ቅርብ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهُوَ ٱلَّذِى يُرْسِلُ ٱلرِّيَٰحَ بُشْرًۢا بَيْنَ يَدَىْ رَحْمَتِهِۦ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَقَلَّتْ سَحَابًا ثِقَالًا سُقْنَٰهُ لِبَلَدٍ مَّيِّتٍ فَأَنزَلْنَا بِهِ ٱلْمَآءَ فَأَخْرَجْنَا بِهِۦ مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ كَذَٰلِكَ نُخْرِجُ ٱلْمَوْتَىٰ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy57. አላህ ያ ንፋሶችን ከዝናብ በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው:: ከባዶችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ሆነ አገር እንነዳዋለን:: በእነርሱም ውሃን እናወርዳለን:: እናም ከፍሬዎች ሁሉ በእነርሱ እናወጣለን:: ልክ እንደዚሁ ሙታንን ከመቃብር እናስወጣለን:: ይህን የምንለው ትገነዘቡ ዘንድ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْبَلَدُ ٱلطَّيِّبُ يَخْرُجُ نَبَاتُهُۥ بِإِذْنِ رَبِّهِۦ وَٱلَّذِى خَبُثَ لَا يَخْرُجُ إِلَّا نَكِدًا كَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy58. መልካሙ አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ ያማረ ሆኖ ይወጣል። ያ መጥፎ የሆነው አገር ደግሞ በቃዩ ደካማ ሆኖ እንጂ አይወጣም:: ልክ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ህዝቦች ተዓምራትን እናብራራለን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥٓ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy59. ኑሕን ወደ ወገኖቹ ላክነው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلْمَلَأُ مِن قَوْمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy60. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹ «እኛ በግልጽ ስህተት ውስጥ ሆነህ እናይሀለን።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰقَوْمِ لَيْسَ بِى ضَلَٰلَةٌ وَلَٰكِنِّى رَسُولٌ مِّن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy61. ኑሕም አለ: «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም። ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልዕክተኛ ነኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُبَلِّغُكُمْ رِسَٰلَٰتِ رَبِّى وَأَنصَحُ لَكُمْ وَأَعْلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy62. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ:: ለናንተም እመክራችኋለሁ:: ከአላህ በኩልም የማታውቁትን አውቃለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَعَجِبْتُمْ أَن جَآءَكُمْ ذِكْرٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنكُمْ لِيُنذِرَكُمْ وَلِتَتَّقُوا۟ وَلَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. «አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከናንተው ጎሳ መካከል በሆነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ስለመጣላችሁ ትደነቃላችሁን?» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَذَّبُوهُ فَأَنجَيْنَٰهُ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥ فِى ٱلْفُلْكِ وَأَغْرَقْنَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَآ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمًا عَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy64. ወዲያዉም አስተባበሉት:: እርሱንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያሉትንም በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው:: እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ግን በባህር አሰመጥናቸው:: እነርሱ ልበ እውራን ህዝቦች ነበሩና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا قَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥٓ أَفَلَا تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy65. ወደ ዓድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሁድን ላክን። «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: የአላህን ቅጣት አትፈሩምን?» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلْمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن قَوْمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِى سَفَاهَةٍ وَإِنَّا لَنَظُنُّكَ مِنَ ٱلْكَٰذِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy66. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹም «እኛ በሞኝነት ላይ ሆነህ እናይሀለን:: እኛ ከውሸተኞቹ ነህ ብለንም እንጠረጥርሀለን።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰقَوْمِ لَيْسَ بِى سَفَاهَةٌ وَلَٰكِنِّى رَسُولٌ مِّن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy67. እርሱም አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም:: ግን እኔ ከአለማት ጌታ የተላኩ ነኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُبَلِّغُكُمْ رِسَٰلَٰتِ رَبِّى وَأَنَا۠ لَكُمْ نَاصِحٌ أَمِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy68. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ። እኔም ለእናንተ ታማኝና መካሪ ነኝና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَعَجِبْتُمْ أَن جَآءَكُمْ ذِكْرٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنكُمْ لِيُنذِرَكُمْ وَٱذْكُرُوٓا۟ إِذْ جَعَلَكُمْ خُلَفَآءَ مِنۢ بَعْدِ قَوْمِ نُوحٍ وَزَادَكُمْ فِى ٱلْخَلْقِ بَصْۜطَةً فَٱذْكُرُوٓا۟ ءَالَآءَ ٱللَّهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. ያስጠነቅቃችሁ ዘንድ ከናንተው መካከል በሆነ ሰው ከጌታችሁ የሆነ ግሳጼ ስለመጣባችሁ ትደነቃላችሁን? ከኑህ ህዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጥረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የሻችሁትን ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ أَجِئْتَنَا لِنَعْبُدَ ٱللَّهَ وَحْدَهُۥ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy70. «አላህን አንድ አድርገን ብቻውን እንድንገዛውና አባቶቻችን ይገዟቸው የነበሩትን አማልክት እንድንተው መጣህብን? እውነተኛ ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ قَدْ وَقَعَ عَلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ رِجْسٌ وَغَضَبٌ أَتُجَٰدِلُونَنِى فِىٓ أَسْمَآءٍ سَمَّيْتُمُوهَآ أَنتُمْ وَءَابَآؤُكُم مَّا نَزَّلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَٰنٍ فَٱنتَظِرُوٓا۟ إِنِّى مَعَكُم مِّنَ ٱلْمُنتَظِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy71. «ከጌታችሁ የሆነ ቅጣትና ቁጣ በእናንተ ላይ በእውነት ተረጋገጠ:: እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእነርሱ ምንም ማስረጃ ላላወረደባቸው ትከራከሩኛላችሁን? ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَنجَيْنَٰهُ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَقَطَعْنَا دَابِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَمَا كَانُوا۟ مُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy72. እርሱንና እነዚያን አብረውት የነበሩትን በችሮታችን ከቅጣት አዳናቸው::የእነዚያንም በተአምራታችን ያስተባበሉትንና አማኞች ያልነበሩትን መሠረት ቆረጥን፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَٰلِحًا قَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥ قَدْ جَآءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمْ ءَايَةً فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِىٓ أَرْضِ ٱللَّهِ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy73. ወደ ሰሙድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን:: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም:: እውነተኛ ለመሆኔ ከጌታችሁ የሆነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች:: ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናትና ተዋት:: በአላህ ምድር ውስጥ እንደፈለገች ትብላ፤ ትጠጣም:: በክፉ አትንኳትም:: አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرُوٓا۟ إِذْ جَعَلَكُمْ خُلَفَآءَ مِنۢ بَعْدِ عَادٍ وَبَوَّأَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ تَتَّخِذُونَ مِن سُهُولِهَا قُصُورًا وَتَنْحِتُونَ ٱلْجِبَالَ بُيُوتًا فَٱذْكُرُوٓا۟ ءَالَآءَ ٱللَّهِ وَلَا تَعْثَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ مُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy74. ከዓድ ህዝቦችም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ከሜዳዎቿ ሸክላ ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ:: ከተራራዎቿም ቤቶችን ትጠርባላችሁ:: ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلْمَلَأُ ٱلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوا۟ مِن قَوْمِهِۦ لِلَّذِينَ ٱسْتُضْعِفُوا۟ لِمَنْ ءَامَنَ مِنْهُمْ أَتَعْلَمُونَ أَنَّ صَٰلِحًا مُّرْسَلٌ مِّن رَّبِّهِۦ قَالُوٓا۟ إِنَّا بِمَآ أُرْسِلَ بِهِۦ مُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy75. ከወገኖቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎች ለእነዚያ ለተሸነፉት በተለይም ከእነርሱ ላመኑት ክፍሎች: «ሷሊህ ከጌታው መላኩን ታውቃላችሁን?» አሏቸው:: እነርሱም «አዎን እናውቃለን:: እኛ እርሱ በተላከበት ነገር ሁሉ ትክክለኛ አማኞች ነን» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوٓا۟ إِنَّا بِٱلَّذِىٓ ءَامَنتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy76. እነዚያ የኮሩት እኛ ግን «በዚያ ባመናችሁበት ነገር ከሓዲያን ነን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَعَقَرُوا۟ ٱلنَّاقَةَ وَعَتَوْا۟ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِمْ وَقَالُوا۟ يَٰصَٰلِحُ ٱئْتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy77. እናም ወዲያው ግመሊቱን ወጓትና ከጌታቸው ትዕዛዝ ወጡ:: «ሷሊህ ሆይ! ከመልዕክተኞቹ እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ جَٰثِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy78. ወዲያዉም የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተደፍተው አደሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰقَوْمِ لَقَدْ أَبْلَغْتُكُمْ رِسَالَةَ رَبِّى وَنَصَحْتُ لَكُمْ وَلَٰكِن لَّا تُحِبُّونَ ٱلنَّٰصِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy79. ሷሊህም ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልዕክት በእርግጥ አደረስኩላችሁ:: ለእናንተም መከርኳችሁ:: ግን እናንተ መካሪዎችን አትወዱም።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَٰحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥም ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ከዓለማት ከናንተ በፊት አንድም ህዝብ ያልፈጸመውን አስቀያሚ ሥራ ትሠራላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy81. «እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል ትመጡባቸዋላችሁ። ይልቁንም እናንተ ወሰንን አላፊ ሕዝቦች ናችሁ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓا۟ أَخْرِجُوهُم مِّن قَرْيَتِكُمْ إِنَّهُمْ أُنَاسٌ يَتَطَهَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy82. የሕዝቦቹም መልስ «ሉጥንና ተከታዮቹን ከከተማችሁ አውጧቸው:: እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸው።» ከማለት ውጭ ሌላ አልነበረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَنجَيْنَٰهُ وَأَهْلَهُۥٓ إِلَّا ٱمْرَأَتَهُۥ كَانَتْ مِنَ ٱلْغَٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy83. ከዚያም እርሱንና ቤተሰቦቹን አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር:: እርሷማ ለጥፋት ከቀሩት ሰዎች ሆነች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy84. በእነርሱ ላይ የእሳት ዝናብን አዘነብንባቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኃጢአተኞች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا قَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥ قَدْ جَآءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَوْفُوا۟ ٱلْكَيْلَ وَٱلْمِيزَانَ وَلَا تَبْخَسُوا۟ ٱلنَّاسَ أَشْيَآءَهُمْ وَلَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَٰحِهَا ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy85. ወደ መድየን ሕዝብም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን። አላቸዉም: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ በስተቀር ምንም አምላክ የላችሁም:: ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ መጥቶላችኋል:: ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: የሰዎችንም ገንዘቦቻቸውን አታጉድሉባቸው:: ምድርንም ከተበጀች በኋላ አታበላሹ። አማኞች ከሆናችሁ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَقْعُدُوا۟ بِكُلِّ صِرَٰطٍ تُوعِدُونَ وَتَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ مَنْ ءَامَنَ بِهِۦ وَتَبْغُونَهَا عِوَجًا وَٱذْكُرُوٓا۟ إِذْ كُنتُمْ قَلِيلًا فَكَثَّرَكُمْ وَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy86. «ሰዎችን የምታስፈራሩ፤ ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱና የአላህን መንገድ መጥመሟንም የምትፈልጉ ሆናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ:: ጥቂቶች በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የአጥፊ ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረም ተመልከቱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن كَانَ طَآئِفَةٌ مِّنكُمْ ءَامَنُوا۟ بِٱلَّذِىٓ أُرْسِلْتُ بِهِۦ وَطَآئِفَةٌ لَّمْ يُؤْمِنُوا۟ فَٱصْبِرُوا۟ حَتَّىٰ يَحْكُمَ ٱللَّهُ بَيْنَنَا وَهُوَ خَيْرُ ٱلْحَٰكِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy87. «ከናንተም መካከል እኔ በተላኩበት ያመኑ ቡድኖችና ያላመኑ ቡድኖች ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሡ:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ እጅግ በላጭ ነው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلْمَلَأُ ٱلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوا۟ مِن قَوْمِهِۦ لَنُخْرِجَنَّكَ يَٰشُعَيْبُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَكَ مِن قَرْيَتِنَآ أَوْ لَتَعُودُنَّ فِى مِلَّتِنَا قَالَ أَوَلَوْ كُنَّا كَٰرِهِينَ
Amharic Translation - Africa Academy88. ከህዝቦቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎችም፡- «ሹዐይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ካንተ ጋር ያመኑትን ከከተማችን እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «የጠላንም ብንሆን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَدِ ٱفْتَرَيْنَا عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِى مِلَّتِكُم بَعْدَ إِذْ نَجَّىٰنَا ٱللَّهُ مِنْهَا وَمَا يَكُونُ لَنَآ أَن نَّعُودَ فِيهَآ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّنَا وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَىْءٍ عِلْمًا عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا ٱفْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِٱلْحَقِّ وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْفَٰتِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy89. «አላህ ከእርሷ ከአዳንን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፍን:: አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ወደ እርሷ ልንመለስ አይገባንም:: የጌታችን እውቀቱ ከሁሉ ሰፋ:: በአላህ ላይ ብቻ ተመካን:: ጌታችን ሆይ! በእኛና በወገኖቻችን መካከል ፍረድ:: አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህና።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلْمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن قَوْمِهِۦ لَئِنِ ٱتَّبَعْتُمْ شُعَيْبًا إِنَّكُمْ إِذًا لَّخَٰسِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy90. ከወገኖቹም መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት መሪዎች ለሕዝቡ «ሹዐይብን ብትከተሉ እናንተ ያኔ ከሳሪዎች ናችሁ።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ جَٰثِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy91. ወዲያውኑ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤታቸው ውስጥ ተደፍተው አደሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ شُعَيْبًا كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا۟ فِيهَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ شُعَيْبًا كَانُوا۟ هُمُ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy92. እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ሰዎች በእርሷ እንዳልነበሩባት ሆኑ:: እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ከሳሪዎቹ እነርሱው ሆኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰقَوْمِ لَقَدْ أَبْلَغْتُكُمْ رِسَٰلَٰتِ رَبِّى وَنَصَحْتُ لَكُمْ فَكَيْفَ ءَاسَىٰ عَلَىٰ قَوْمٍ كَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy93. ሹዐይብም ትቷቸው ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልእክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ። ለእናንተም መከርኩ:: ታዲያ በከሃዲ ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ?» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَرْسَلْنَا فِى قَرْيَةٍ مِّن نَّبِىٍّ إِلَّآ أَخَذْنَآ أَهْلَهَا بِٱلْبَأْسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ لَعَلَّهُمْ يَضَّرَّعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy94. በየትኛዉም ከተማ ለአላህ ይተናነሱ ዘንድ በድህነትና በችግር የያዝናቸው ብንሆን እንጂ አንድንም ነብይ አልላክንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ بَدَّلْنَا مَكَانَ ٱلسَّيِّئَةِ ٱلْحَسَنَةَ حَتَّىٰ عَفَوا۟ وَّقَالُوا۟ قَدْ مَسَّ ءَابَآءَنَا ٱلضَّرَّآءُ وَٱلسَّرَّآءُ فَأَخَذْنَٰهُم بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy95.ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ ٱلْقُرَىٰٓ ءَامَنُوا۟ وَٱتَّقَوْا۟ لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَٰتٍ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ وَلَٰكِن كَذَّبُوا۟ فَأَخَذْنَٰهُم بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy96. የከተሞቹ (ሰዎችም) በትክክል ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይና ከምድር በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር:: ግን አስተባበሉ:: ይሠሩት በነበሩትም ኃጢአት ምክኒያት ቀጣናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَأَمِنَ أَهْلُ ٱلْقُرَىٰٓ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَٰتًا وَهُمْ نَآئِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy97. የከተሞቹ (ሰዎች) የተኙ ሆነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَأَمِنَ أَهْلُ ٱلْقُرَىٰٓ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy98. የከተሞቹ ሰዎችም የሚጫወቱ ሆነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋዱ ሊመጣባቸው አይፈሩምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَأَمِنُوا۟ مَكْرَ ٱللَّهِ فَلَا يَأْمَنُ مَكْرَ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْقَوْمُ ٱلْخَٰسِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy99. የአላህን ማዘናጋት አይፈሩምን? ተማመኑን? የአላህን ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር ማንም የሚተማመን የለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَهْدِ لِلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلْأَرْضَ مِنۢ بَعْدِ أَهْلِهَآ أَن لَّوْ نَشَآءُ أَصَبْنَٰهُم بِذُنُوبِهِمْ وَنَطْبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy100. ለእነዚያ ምድርን ከባለቤቶቿ ጥፋት በኋላ ለሚወርሱት ብንሻ ኖሮ በኃጢአቶቻቸው ምክኒያት የምንቀጣቸው መሆናችን አልተገለጸላቸዉምን? በልቦቻቸውም ላይ እናትማለን:: ስለዚህም እነርሱ አይሰሙም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ ٱلْقُرَىٰ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآئِهَا وَلَقَدْ جَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانُوا۟ لِيُؤْمِنُوا۟ بِمَا كَذَّبُوا۟ مِن قَبْلُ كَذَٰلِكَ يَطْبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy101. እነዚህ ከተሞች ከወሬዎቻቸው ባንተ ላይ እንተርካለን:: መልዕክተኞቻቸዉም በግልጽ ተዓምራት መጥተውላቸዋል:: ከመምጣታቸው በፊት ባስተባበሉትም ነገር የሚያምኑ አልሆነም:: ልክ እንደዚሁ አላህ በከሓዲያን ልቦች ላይ ያትማል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا وَجَدْنَا لِأَكْثَرِهِم مِّنْ عَهْدٍ وَإِن وَجَدْنَآ أَكْثَرَهُمْ لَفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy102. ለብዙዎቻቸው በቃል ኪዳናቸው መሙላትን አላገኘንም:: ይልቁንም አብዛኞቻቸውን አመጸኞች ሆነው አገኘናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ بَعَثْنَا مِنۢ بَعْدِهِم مُّوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ فَظَلَمُوا۟ بِهَا فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy103. ከዚያም ከበኋላቸው ነብዩ ሙሳን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቶቹ ተዓምራታችንን አስይዘን ላክነው:: በእርሷም ካዱ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአጥፊዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ እስቲ ተመልከት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰفِرْعَوْنُ إِنِّى رَسُولٌ مِّن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy104. ሙሳም አለ፡- «ፈርዖን! ሆይ እኔ ከዓለማት ጌታ የተላኩ መልክተኛ ነኝ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
حَقِيقٌ عَلَىٰٓ أَن لَّآ أَقُولَ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَرْسِلْ مَعِىَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ
Amharic Translation - Africa Academy105. «በአላህ ላይ ከእውነት በስተቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው:: ከጌታችሁ ተዓምር ይዤ መጥቻለሁና የኢስራኢል ልጆችን ከእኔ ጋር ልቀቅ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِن كُنتَ جِئْتَ بِـَٔايَةٍ فَأْتِ بِهَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy106. ፈርዖንም፡ «በተዓምር የመጣህ ከሆንክና ከእውነተኞቹ ከሆንክ እስቲ አምጣት።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِىَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy107. ሙሳም ዘንጉን ምድር ላይ ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَزَعَ يَدَهُۥ فَإِذَا هِىَ بَيْضَآءُ لِلنَّٰظِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy108. እጁንም አወጣ:: እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ሆነች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱلْمَلَأُ مِن قَوْمِ فِرْعَوْنَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy109. ከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹም አሉ፡ «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُرِيدُ أَن يُخْرِجَكُم مِّنْ أَرْضِكُمْ فَمَاذَا تَأْمُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy110. «ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል።» አሉ። (ፊርዓውንም) «ታዲያ ምን? ታዛላችሁ?» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ أَرْجِهْ وَأَخَاهُ وَأَرْسِلْ فِى ٱلْمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy111. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደ ከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَأْتُوكَ بِكُلِّ سَٰحِرٍ عَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy112. «አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَآءَ ٱلسَّحَرَةُ فِرْعَوْنَ قَالُوٓا۟ إِنَّ لَنَا لَأَجْرًا إِن كُنَّا نَحْنُ ٱلْغَٰلِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy113. ድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡና «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለኛ ክፍያ አለን?» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ نَعَمْ وَإِنَّكُمْ لَمِنَ ٱلْمُقَرَّبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy114. ፈርዖንም: «አዎን። እናንተ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰمُوسَىٰٓ إِمَّآ أَن تُلْقِىَ وَإِمَّآ أَن نَّكُونَ نَحْنُ ٱلْمُلْقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy115. እነርሱም «ሙሳ ሆይ! ዘንግህን በፊት ትጥላለህ ወይስ ፊት ጣዮቹ እኛ እንሁን?» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَلْقُوا۟ فَلَمَّآ أَلْقَوْا۟ سَحَرُوٓا۟ أَعْيُنَ ٱلنَّاسِ وَٱسْتَرْهَبُوهُمْ وَجَآءُو بِسِحْرٍ عَظِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy116. ሙሳም «በፊት እናንተ ጣሉ።» አላቸው:: ከዚያም ገመዶቻቸውን በጣሉ ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸውና አስፈራሯቸው:: ትልቅ ድግምትንም አመጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ فَإِذَا هِىَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy117. ወደ ሙሳም «ዘንግህን ጣል» ስንል ላክንበት (ጣላትም) ወዲውኑም የሚቀጣጥፉትን ማታለያ ሁሉ መዋጥ ጀመረች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَوَقَعَ ٱلْحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy118. እውነቱም ተገለጸ:: ይሠሩት የነበሩት ድግምትም ተበላሸ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَغُلِبُوا۟ هُنَالِكَ وَٱنقَلَبُوا۟ صَٰغِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy119. እዚያ ላይ ተሸነፉና ወራዶች ሆነው ተመለሱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُلْقِىَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy120. ድግምተኞቹም ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ ወረዱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy121. አሉም: «በዓለማት ጌታ አመንን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy122. «በሙሳና በሃሩን ጌታ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فِرْعَوْنُ ءَامَنتُم بِهِۦ قَبْلَ أَنْ ءَاذَنَ لَكُمْ إِنَّ هَٰذَا لَمَكْرٌ مَّكَرْتُمُوهُ فِى ٱلْمَدِينَةِ لِتُخْرِجُوا۟ مِنْهَآ أَهْلَهَا فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy123. (ፊርዓውንም) አለ፡ «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን? ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰውን ከእርሷ ለማውጣት የተስማማችሁበት ተንኮል ነው:: ወደፊት የሚደርሰባችሁን ታውቃላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَٰفٍ ثُمَّ لَأُصَلِّبَنَّكُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy124. «እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ:: ከዚያም ሁላችሁንም በእንጨት ላይ እስቅላችኋለሁ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy125. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا تَنقِمُ مِنَّآ إِلَّآ أَنْ ءَامَنَّا بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا لَمَّا جَآءَتْنَا رَبَّنَآ أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَتَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy126. «የጌታችን ተዓምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በስተቀር ከእኛ አትጠላም:: ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ:: ሙስሊሞችም ሆነን ግደለን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلْمَلَأُ مِن قَوْمِ فِرْعَوْنَ أَتَذَرُ مُوسَىٰ وَقَوْمَهُۥ لِيُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ وَيَذَرَكَ وَءَالِهَتَكَ قَالَ سَنُقَتِّلُ أَبْنَآءَهُمْ وَنَسْتَحْىِۦ نِسَآءَهُمْ وَإِنَّا فَوْقَهُمْ قَٰهِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy127. ከፈርዖን ሰዎች ቅምጥሎቹ ለፈርዖን: «ሙሳንና ሰዎችን በምድር ላይ እንዲያበላሹና ሙሳም አንተንና አምልኮትህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን?» አሉ:: እሱም «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን:: ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን:: እኛም ከበላያቸው ነን አሸናፊዎች ነን» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ ٱسْتَعِينُوا۟ بِٱللَّهِ وَٱصْبِرُوٓا۟ إِنَّ ٱلْأَرْضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ وَٱلْعَٰقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy128. ሙሳም ለሰዎቹ፡- «በአላህ ታገዙ፤ ታገሱም። ምድር ለአላህ ናትና ከባሮቹ መካከል ለሚሻው ያወርሳታል:: ምስጉኗም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ أُوذِينَا مِن قَبْلِ أَن تَأْتِيَنَا وَمِنۢ بَعْدِ مَا جِئْتَنَا قَالَ عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُهْلِكَ عَدُوَّكُمْ وَيَسْتَخْلِفَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرَ كَيْفَ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy129. ህዝቦቹም «አንተ ከመምጣትህ በፊትም ሆነ ከመጣህልን በኋላ ተሰቃየን።» አሉት:: ሙሳም «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋና እንዴት እንደምትሰሩ ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይከጀላል።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَخَذْنَآ ءَالَ فِرْعَوْنَ بِٱلسِّنِينَ وَنَقْصٍ مِّنَ ٱلثَّمَرَٰتِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy130. የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅና የፍራፍሬ ምርታቸውን በመቀነስ በእርግጥ ቀጣናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا جَآءَتْهُمُ ٱلْحَسَنَةُ قَالُوا۟ لَنَا هَٰذِهِۦ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَطَّيَّرُوا۟ بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ أَلَآ إِنَّمَا طَٰٓئِرُهُمْ عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy131. ምቾት በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ ተገቢ ናት።» ይላሉ። ክፋት ባገኛቸው ጊዜ ግን ሙሳና አብረውት ያሉት ክፉ ገዶቻቸው እንደሆኑ ያስባሉ። አስተውሉ! ክፉ እድላቸው (ገደቢስነታቸው) ከአላህ ዘንድ ነው:: አብዛኞቻቸው ግን ይህን አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ مَهْمَا تَأْتِنَا بِهِۦ مِنْ ءَايَةٍ لِّتَسْحَرَنَا بِهَا فَمَا نَحْنُ لَكَ بِمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy132. «በማንኛይቱም ተዓምር ልትደግምብን ብታመጣም የምናምንልህ አይደለንም።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ ٱلطُّوفَانَ وَٱلْجَرَادَ وَٱلْقُمَّلَ وَٱلضَّفَادِعَ وَٱلدَّمَ ءَايَٰتٍ مُّفَصَّلَٰتٍ فَٱسْتَكْبَرُوا۟ وَكَانُوا۟ قَوْمًا مُّجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy133. ወዲያዉም የውሃን ማጥለቅለቅ፤ አንበጣን፤ ቅማልን፤ እንቁራሪቶችን፤ ደምን፤ የተለያዩ ተዓምራት ሲሆኑ በእነርሱ ላይ ላክን:: እነርሱ ግን ኮሩም:: ተንኮለኞችም ህዝቦች ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا وَقَعَ عَلَيْهِمُ ٱلرِّجْزُ قَالُوا۟ يَٰمُوسَى ٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَ لَئِن كَشَفْتَ عَنَّا ٱلرِّجْزَ لَنُؤْمِنَنَّ لَكَ وَلَنُرْسِلَنَّ مَعَكَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ
Amharic Translation - Africa Academy134. በእነርሱ ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸውም ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ መሠረት ለምንልንና ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ላንተ እናምንልሀለን:: የኢስራኢልን ልጆችም ካንተ ጋር እንለቃለን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا كَشَفْنَا عَنْهُمُ ٱلرِّجْزَ إِلَىٰٓ أَجَلٍ هُم بَٰلِغُوهُ إِذَا هُمْ يَنكُثُونَ
Amharic Translation - Africa Academy135. ለሚደርሱበት የተወሰነ ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነርሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን አፈረሱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱنتَقَمْنَا مِنْهُمْ فَأَغْرَقْنَٰهُمْ فِى ٱلْيَمِّ بِأَنَّهُمْ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُوا۟ عَنْهَا غَٰفِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy136. እነርሱም በተዓምራታችን ስላስተባበሉና ከእርሷ ዘንጊዎች ስለሆኑ ተበቀልናቸው:: በባህር ውስጥም አሰመጥናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَوْرَثْنَا ٱلْقَوْمَ ٱلَّذِينَ كَانُوا۟ يُسْتَضْعَفُونَ مَشَٰرِقَ ٱلْأَرْضِ وَمَغَٰرِبَهَا ٱلَّتِى بَٰرَكْنَا فِيهَا وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلْحُسْنَىٰ عَلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ بِمَا صَبَرُوا۟ وَدَمَّرْنَا مَا كَانَ يَصْنَعُ فِرْعَوْنُ وَقَوْمُهُۥ وَمَا كَانُوا۟ يَعْرِشُونَ
Amharic Translation - Africa Academy137. እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ህዝቦች ያቺን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምስራቋንም ምዕራቧንም አወረስናቸው:: መልዕክተኛችን ሆይ! የጌታህ መልካሚቱ ቃል በኢስራኢል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች:: ፈርዖንና ሰዎቹ ይሰሩት የነበረውን ህንጻና ዳስ ያደርጉት የነበረውንም አፈረስን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَٰوَزْنَا بِبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْبَحْرَ فَأَتَوْا۟ عَلَىٰ قَوْمٍ يَعْكُفُونَ عَلَىٰٓ أَصْنَامٍ لَّهُمْ قَالُوا۟ يَٰمُوسَى ٱجْعَل لَّنَآ إِلَٰهًا كَمَا لَهُمْ ءَالِهَةٌ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy138. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሻገርናቸው:: ለእነርሱ በሆኑ ጣኦታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ህዝቦች አጠገብ አለፉም:: «ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ ለሰዎቹ አማልክት እንዳሏቸው ሁሉ ለኛም አምላክን አድርግልን።» አሉት:: «እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ مُتَبَّرٌ مَّا هُمْ فِيهِ وَبَٰطِلٌ مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy139. «እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው:: ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِيكُمْ إِلَٰهًا وَهُوَ فَضَّلَكُمْ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy140. «እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲሆን ከአላህ ሌላ የምትገዙትን አምላክ እፈልግላችኋለሁን?» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ أَنجَيْنَٰكُم مِّنْ ءَالِ فِرْعَوْنَ يَسُومُونَكُمْ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ يُقَتِّلُونَ أَبْنَآءَكُمْ وَيَسْتَحْيُونَ نِسَآءَكُمْ وَفِى ذَٰلِكُم بَلَآءٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy141. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ ወንዶች ልጆቻችሁንም የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆኑ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ):: በዚህ ውስጥ ከጌታችሁ የሆነ ከባድ ፈተና አለበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَٰعَدْنَا مُوسَىٰ ثَلَٰثِينَ لَيْلَةً وَأَتْمَمْنَٰهَا بِعَشْرٍ فَتَمَّ مِيقَٰتُ رَبِّهِۦٓ أَرْبَعِينَ لَيْلَةً وَقَالَ مُوسَىٰ لِأَخِيهِ هَٰرُونَ ٱخْلُفْنِى فِى قَوْمِى وَأَصْلِحْ وَلَا تَتَّبِعْ سَبِيلَ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy142. ነብዩ ሙሳን ሰላሳን ሌሊት (ሊፆምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው:: በአስርም (ሌሊት) ሞላናት:: የጌታዉም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲሆን ተፈጸመ:: ሙሳም ለወንድሙ ለሀሩን «በህዝቦቼ ላይ ተተካኝና አሳምር:: የአጥፊዎችን መንገድ አትከተል።» አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا جَآءَ مُوسَىٰ لِمِيقَٰتِنَا وَكَلَّمَهُۥ رَبُّهُۥ قَالَ رَبِّ أَرِنِىٓ أَنظُرْ إِلَيْكَ قَالَ لَن تَرَىٰنِى وَلَٰكِنِ ٱنظُرْ إِلَى ٱلْجَبَلِ فَإِنِ ٱسْتَقَرَّ مَكَانَهُۥ فَسَوْفَ تَرَىٰنِى فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُۥ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُۥ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا فَلَمَّآ أَفَاقَ قَالَ سُبْحَٰنَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy143. ሙሳ ለቀጠሮው በመጣና ጌታዉም ባነጋገረው ጊዜ፡ «ጌታዬ ሆይ! በእርግጥ ራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና።» አለ። (አላህም)፡- «እኔን በፍጹም አታየኝም:: ግን ወደ ተራራው ተመልከትና በስፍራው ከረጋ አንተም ታየኛለህ።» አለው:: ጌታዉም ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው:: ሙሳም ጮኸና ወደቀ:: በአንሰራራም ጊዜ «ጌታዬ ጥራት ይገባህ ወደ አንተ ተመለስኩ:: እኔም በጊዜያቴ የአማኞች መጀመሪያ ነኝ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ إِنِّى ٱصْطَفَيْتُكَ عَلَى ٱلنَّاسِ بِرِسَٰلَٰتِى وَبِكَلَٰمِى فَخُذْ مَآ ءَاتَيْتُكَ وَكُن مِّنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy144. አላህም አለ፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልዕክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ:: የሰጠሁህንም ያዝ። ከአመስጋኞችም ሁን።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَتَبْنَا لَهُۥ فِى ٱلْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَىْءٍ مَّوْعِظَةً وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَىْءٍ فَخُذْهَا بِقُوَّةٍ وَأْمُرْ قَوْمَكَ يَأْخُذُوا۟ بِأَحْسَنِهَا سَأُو۟رِيكُمْ دَارَ ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy145. ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከሁሉ ነገር ግሳጼንና ለሁሉ ነገር ማብራራትን ጻፍንለትና አልንም: «በብርታትም ያዛት። ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው። የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَأَصْرِفُ عَنْ ءَايَٰتِىَ ٱلَّذِينَ يَتَكَبَّرُونَ فِى ٱلْأَرْضِ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ وَإِن يَرَوْا۟ كُلَّ ءَايَةٍ لَّا يُؤْمِنُوا۟ بِهَا وَإِن يَرَوْا۟ سَبِيلَ ٱلرُّشْدِ لَا يَتَّخِذُوهُ سَبِيلًا وَإِن يَرَوْا۟ سَبِيلَ ٱلْغَىِّ يَتَّخِذُوهُ سَبِيلًا ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُوا۟ عَنْهَا غَٰفِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy146. እነዚያን ያለ አግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀፆቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ:: ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ እንኳን አያምኑም:: ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም:: ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል:: ይህ እነርሱ በአንቀፆቻችን ስለ አስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለሆኑ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآءِ ٱلْـَٔاخِرَةِ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ هَلْ يُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy147. እነዚያም በአናቅጻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ:: ይሰሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِنۢ بَعْدِهِۦ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُۥ خُوَارٌ أَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّهُۥ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ٱتَّخَذُوهُ وَكَانُوا۟ ظَٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy148. የሙሳም ህዝቦች ከእርሱ መሄድ በኋላ ከጌጦቻቸው በወይፈን ቅርጽ የተቀረጸውን እና የራሱ የሆነ ድምጽ የነበረውን አካል አምላክ አድርገው ያዙት:: እርሱ የማያናግራቸው መንገድን የማይመራቸው መሆኑን አይመለከቱምን? አምላክ አደረጉት:: በዳዮችም ሆኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا سُقِطَ فِىٓ أَيْدِيهِمْ وَرَأَوْا۟ أَنَّهُمْ قَدْ ضَلُّوا۟ قَالُوا۟ لَئِن لَّمْ يَرْحَمْنَا رَبُّنَا وَيَغْفِرْ لَنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy149. በተጸጸቱና እነርሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መሆናቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ካላዘነልንና ካልማረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا رَجَعَ مُوسَىٰٓ إِلَىٰ قَوْمِهِۦ غَضْبَٰنَ أَسِفًا قَالَ بِئْسَمَا خَلَفْتُمُونِى مِنۢ بَعْدِىٓ أَعَجِلْتُمْ أَمْرَ رَبِّكُمْ وَأَلْقَى ٱلْأَلْوَاحَ وَأَخَذَ بِرَأْسِ أَخِيهِ يَجُرُّهُۥٓ إِلَيْهِ قَالَ ٱبْنَ أُمَّ إِنَّ ٱلْقَوْمَ ٱسْتَضْعَفُونِى وَكَادُوا۟ يَقْتُلُونَنِى فَلَا تُشْمِتْ بِىَ ٱلْأَعْدَآءَ وَلَا تَجْعَلْنِى مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy150. ሙሳ እየተቆጣና እያዘነ ወደ ህዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «በእኔ ቦታ የተካችሁት ነገር ምንኛ ከፋ! የጌታችሁን ትዕዛዝ ተቻኮላችሁን?» አላቸውና ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው። የወንድሙን የራስ ጸጉር ወደ እርሱ እየጎተተው ያዘ:: ወንድሙም፡- «የእናቴ ልጅ ሆይ! ህዝቦቹ ናቁኝ ሊገድሉኝም ተቃረቡ:: ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ። ከአመጸኞች ህዝቦችም ጋር አታድርገኝ።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ ٱغْفِرْ لِى وَلِأَخِى وَأَدْخِلْنَا فِى رَحْمَتِكَ وَأَنتَ أَرْحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy151. ሙሳም፡- «ጌታዬ ሆይ! ለኔም ለወንድሜም ማረን:: በእዝነትህ ውስጥም አስገባን። አንተም ከአዛኞቹ ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህና።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ ٱلْعِجْلَ سَيَنَالُهُمْ غَضَبٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَذِلَّةٌ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُفْتَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy152. እነዚያ ወይፈኑን አምላክ ያደረጉት ሰዎች ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ በቅርቢቱም ህይወት ውርደት ያገኛቸዋል:: ቀጣፊዎችን ልክ እንዲዚሁ እንቀጣለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ عَمِلُوا۟ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ثُمَّ تَابُوا۟ مِنۢ بَعْدِهَا وَءَامَنُوٓا۟ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy153. እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም በኋላ የተጸጸቱና በአላህ ያመኑ ጌታህ ከእርሷ በኋላ መሀሪና አዛኝ ነው:: (ጸጸታቸውን ይቀበላቸዋል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى ٱلْغَضَبُ أَخَذَ ٱلْأَلْوَاحَ وَفِى نُسْخَتِهَا هُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ هُمْ لِرَبِّهِمْ يَرْهَبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy154. ሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን አነሳቸው:: በግልባጫቸውም ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ መምሪያና እዝነት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱخْتَارَ مُوسَىٰ قَوْمَهُۥ سَبْعِينَ رَجُلًا لِّمِيقَٰتِنَا فَلَمَّآ أَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ قَالَ رَبِّ لَوْ شِئْتَ أَهْلَكْتَهُم مِّن قَبْلُ وَإِيَّٰىَ أَتُهْلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَّآ إِنْ هِىَ إِلَّا فِتْنَتُكَ تُضِلُّ بِهَا مَن تَشَآءُ وَتَهْدِى مَن تَشَآءُ أَنتَ وَلِيُّنَا فَٱغْفِرْ لَنَا وَٱرْحَمْنَا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْغَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy155. ሙሳም ከህዝቦቹ መካከል ለቀጠሯችን ሰባ ሰዎችን መረጠ:: ከዚያ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በደረሰባቸው ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! ብትፈልግ ኖሮ ከአሁን በፊት ባጠፋሀቸው ነበር:: እኔንም ባጠፋኸኝ ነበር:: ከእኛ መሀከል ቂሎቹ በሠሩት ጥፋት ታጠፋናለህን? ፈተናይቱ የአንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም:: በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ። የምትሻውንም ታቀናለህ:: አንተ ረዳታችን ነህና:: ለእኛ ምህረት አድርግልን። እዘንልንም:: አንተ ከመሀሪዎች ሁሉ በላጭ ነህና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱكْتُبْ لَنَا فِى هَٰذِهِ ٱلدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِى ٱلْـَٔاخِرَةِ إِنَّا هُدْنَآ إِلَيْكَ قَالَ عَذَابِىٓ أُصِيبُ بِهِۦ مَنْ أَشَآءُ وَرَحْمَتِى وَسِعَتْ كُلَّ شَىْءٍ فَسَأَكْتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِنَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy156. «ጌታችን ሆይ! ለእኛ በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም ዓለም መልካሟን ጻፍልን:: እኛ ወደ አንተ ተመልሰናል።» (ሲል ሙሳ ጌታውን ለመነ):: አላህም አለ: «ቅጣቴ በእርሱ ልቀጣው የምፈልገውን ሰው እቀጣበታለሁ:: ችሮታዬ ከሁሉም ነገር የሰፋ ነው:: ለእነዚያ ለሚጠነቀቁ ዘካንም ለሚሰጡ ለእነዚያም በአናቅጻችን ለሚያምኑ ሁሉ በእርግጥ እጽፈዋለሁ::»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَتَّبِعُونَ ٱلرَّسُولَ ٱلنَّبِىَّ ٱلْأُمِّىَّ ٱلَّذِى يَجِدُونَهُۥ مَكْتُوبًا عِندَهُمْ فِى ٱلتَّوْرَىٰةِ وَٱلْإِنجِيلِ يَأْمُرُهُم بِٱلْمَعْرُوفِ وَيَنْهَىٰهُمْ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ ٱلْخَبَٰٓئِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَٱلْأَغْلَٰلَ ٱلَّتِى كَانَتْ عَلَيْهِمْ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِهِۦ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَٱتَّبَعُوا۟ ٱلنُّورَ ٱلَّذِىٓ أُنزِلَ مَعَهُۥٓ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy157. ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብን መልዕክተኛ የሚከተሉ ለሆኑ (ሁሉ በእርግጥ እጽፋታለሁ):: በበጎ ሥራ ያዛቸዋል:: ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል:: መልካም ነገሮችንም ለእነርሱ ይፈቅድላቸዋል:: መጥፎ ነገሮችንም በነሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል:: ከእነርሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንደ እንዛዝላ ይከብዱ የነበሩ ከባድ ህግጋትን ያነሳላቸዋል:: እነዚያ በእርሱ ያመኑ፤ ያከበሩት፤ የረዱትና ያንን ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ ሁሉ እነዚያ እነርሱ ከቅጣት የሚድኑ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنِّى رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا ٱلَّذِى لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِ ٱلنَّبِىِّ ٱلْأُمِّىِّ ٱلَّذِى يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَكَلِمَٰتِهِۦ وَٱتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ:: እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነ ነው:: እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ በሆነው መልዕክተኛውም እመኑ:: ወደ ቅኑ መንገድ ትመሩ ዘንድም ተከተሉት።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِن قَوْمِ مُوسَىٰٓ أُمَّةٌ يَهْدُونَ بِٱلْحَقِّ وَبِهِۦ يَعْدِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy159. ከሙሳ ህዝቦች መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካከሉ ቡድኖችም አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَطَّعْنَٰهُمُ ٱثْنَتَىْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ إِذِ ٱسْتَسْقَىٰهُ قَوْمُهُۥٓ أَنِ ٱضْرِب بِّعَصَاكَ ٱلْحَجَرَ فَٱنۢبَجَسَتْ مِنْهُ ٱثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا قَدْ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٍ مَّشْرَبَهُمْ وَظَلَّلْنَا عَلَيْهِمُ ٱلْغَمَٰمَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْهِمُ ٱلْمَنَّ وَٱلسَّلْوَىٰ كُلُوا۟ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقْنَٰكُمْ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy160. የሙሳን ህዝቦች አስራ ሁለት ነገዶች አድርገን ከፋፈልናቸው:: ወደ ሙሳም ወገኖቹ ውሃን በፈለጉበት ጊዜ ድንጋዩን በበትርህ ምታው ስንል ላክን:: (መታዉም) አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ:: ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ አወቁ:: በእነርሱም ላይ ዳመናን አጠለልን:: በእነርሱም ላይ "መንን" እና ድርጭትን አወረድን:: «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ።» አልን:: ጸጋዎቻችንን በመካዳቸው አልበደሉንም:: ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ህዝቦች ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قِيلَ لَهُمُ ٱسْكُنُوا۟ هَٰذِهِ ٱلْقَرْيَةَ وَكُلُوا۟ مِنْهَا حَيْثُ شِئْتُمْ وَقُولُوا۟ حِطَّةٌ وَٱدْخُلُوا۟ ٱلْبَابَ سُجَّدًا نَّغْفِرْ لَكُمْ خَطِيٓـَٰٔتِكُمْ سَنَزِيدُ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለነርሱም «በዚች ከተማ ተቀመጡ:: ከእርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ ብሉ:: ‹የምንፈልገው የኃጢታችንን መርገፍ ብቻ ነው።› በሉም:: የከተማይቱን በር አጎንብሳችሁ ግቡ ኃጢአቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና:: በጎ ለሠሩት ሰዎች በእርግጥ እንጨምራለን።» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَبَدَّلَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ قَوْلًا غَيْرَ ٱلَّذِى قِيلَ لَهُمْ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِجْزًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ بِمَا كَانُوا۟ يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy162. ከእነርሱም ውስጥ እነዚያ ራሳቸውን የበደሉ ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የሆነን ቃል ለወጡ:: በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል ምክንያት መአትን ከሰማይ ላክንባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَسْـَٔلْهُمْ عَنِ ٱلْقَرْيَةِ ٱلَّتِى كَانَتْ حَاضِرَةَ ٱلْبَحْرِ إِذْ يَعْدُونَ فِى ٱلسَّبْتِ إِذْ تَأْتِيهِمْ حِيتَانُهُمْ يَوْمَ سَبْتِهِمْ شُرَّعًا وَيَوْمَ لَا يَسْبِتُونَ لَا تَأْتِيهِمْ كَذَٰلِكَ نَبْلُوهُم بِمَا كَانُوا۟ يَفْسُقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም በባህሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በቅዳሜ ቀን ወሰን ባለፉ ጊዜ በሰንበታቸው ቀን አሳዎቻቸው የተከማቹ ሆነው በሚመጡላቸው ጊዜ የሆነውን ጠይቃቸው:: ሰንበትንም በማያከብሩበት (በሌላው) ቀን አይመጡላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ በአመፃቸው ምክንያት እንሞክራቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَتْ أُمَّةٌ مِّنْهُمْ لِمَ تَعِظُونَ قَوْمًا ٱللَّهُ مُهْلِكُهُمْ أَوْ مُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا قَالُوا۟ مَعْذِرَةً إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከፊሎቹ ህዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጫቸው የሆኑትን ህዝቦች ለምን ትገስጻላችሁ?» ባሉ ጊዜ ገሳጮቹም «በጌታችሁ ዘንድ በቂ ምክንያት እንዲሆንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው።» ባሉበት ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا نَسُوا۟ مَا ذُكِّرُوا۟ بِهِۦٓ أَنجَيْنَا ٱلَّذِينَ يَنْهَوْنَ عَنِ ٱلسُّوٓءِ وَأَخَذْنَا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ بِعَذَابٍۭ بَـِٔيسٍۭ بِمَا كَانُوا۟ يَفْسُقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy165. የተገሰጹበትንም ነገር በተው ጊዜ እነዚያን ከክፉ የሚከለክሉትን ክፍሎች አዳንን:: እነዚያንም የበደሉትን ሰዎች ያምጹ በነበሩበት ምክንያት በብርቱ ቅጣት ቀጣናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا عَتَوْا۟ عَن مَّا نُهُوا۟ عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا۟ قِرَدَةً خَٰسِـِٔينَ
Amharic Translation - Africa Academy166. ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮዎች ሁኑ።» አልን:: (ሆኑም)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبْعَثَنَّ عَلَيْهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ مَن يَسُومُهُمْ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ ٱلْعِقَابِ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እስከ ትንሳኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ወገን በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መሆኑን ባስታወቀ ጊዜ (የሆነውን አስታውሳቸው):: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው:: እርሱም በእርግጥ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَطَّعْنَٰهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ أُمَمًا مِّنْهُمُ ٱلصَّٰلِحُونَ وَمِنْهُمْ دُونَ ذَٰلِكَ وَبَلَوْنَٰهُم بِٱلْحَسَنَٰتِ وَٱلسَّيِّـَٔاتِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy168. (የኢስራኢልን ልጆችን) በምድር ላይ የተለያዩ ህዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው:: ከእነርሱ መልካሞች አሉ:: ከእነርሱም ከዚያ ሌላ የሆኑ አሉ:: ይመለሱ ዘንድም በተድላዎችና በመከራዎቻች ሞከርናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَخَلَفَ مِنۢ بَعْدِهِمْ خَلْفٌ وَرِثُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ يَأْخُذُونَ عَرَضَ هَٰذَا ٱلْأَدْنَىٰ وَيَقُولُونَ سَيُغْفَرُ لَنَا وَإِن يَأْتِهِمْ عَرَضٌ مِّثْلُهُۥ يَأْخُذُوهُ أَلَمْ يُؤْخَذْ عَلَيْهِم مِّيثَٰقُ ٱلْكِتَٰبِ أَن لَّا يَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ وَدَرَسُوا۟ مَا فِيهِ وَٱلدَّارُ ٱلْـَٔاخِرَةُ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy169. ከኋላቸዉም መጽሐፉን የወረሱ መጥፎ ምትኮች በእነርሱ ቦታ ተተኩ:: የዚህም የቅርቡን ጠፊ ጥቅም ይይዛሉ:: ብጤዉም ጥቅም ቢመጣላቸው የሚይዙት ሲሆኑ «በሠራነው ለእኛ ምህረት ይደርግልናል።» ይላሉ:: በአላህ ላይ በእውነት በስተቀር እንዳይናገሩ በእነርሱ ላይ የመጽሐፉ ቃል ኪዳን አልተያዘባቸዉምን? በእርሱ ውስጥ ያለውንም አላነበቡምን? የመጨረሻይቱን አገር ለእነዚያ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ በላጭ ናት:: አታውቁምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ يُمَسِّكُونَ بِٱلْكِتَٰبِ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُصْلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy170. እነዚያም መጽሐፉን ጠብቀው የሚይዙ፤ ሶላትንም በደንቡ የሰገዱ ሁሉ (ምንዳቸውን እንከፍላቸዋለን):: እኛ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አናጠፋምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ نَتَقْنَا ٱلْجَبَلَ فَوْقَهُمْ كَأَنَّهُۥ ظُلَّةٌ وَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُۥ وَاقِعٌۢ بِهِمْ خُذُوا۟ مَآ ءَاتَيْنَٰكُم بِقُوَّةٍ وَٱذْكُرُوا۟ مَا فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy171. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጡርን ተራራ ነቅለን ከበላያቸው እንደ ጥላ ሆኖ ባነሳነውና እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ መሆኑን ባረጋገጡ ጊዜ የሆነውን( አስታውስ):: «የሰጠናችሁን በብርታት ያዙ:: ትጠነቀቁም ዘንድ በዉስጡ ያለውን ተገንዘቡ።» አልን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِنۢ بَنِىٓ ءَادَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ قَالُوا۟ بَلَىٰ شَهِدْنَآ أَن تَقُولُوا۟ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَٰذَا غَٰفِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy172. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ። በትንሳኤ ቀን «ከዚህ ቃል ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوْ تَقُولُوٓا۟ إِنَّمَآ أَشْرَكَ ءَابَآؤُنَا مِن قَبْلُ وَكُنَّا ذُرِّيَّةً مِّنۢ بَعْدِهِمْ أَفَتُهْلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلْمُبْطِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy173. ወይም «ጣኦታትን ያጋሩት ከኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው:: እኛም ከእነርሱ በኋላ የሆንን ዘሮች ነበርን አጥፊዎቹ በሠሩት ጥፋት እኛን ታጠፋናለህን?» እንዳትሉ አስመሰከርናችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ وَلَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy174. ልክ እንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አናቅጽን እናብራራለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ٱلَّذِىٓ ءَاتَيْنَٰهُ ءَايَٰتِنَا فَٱنسَلَخَ مِنْهَا فَأَتْبَعَهُ ٱلشَّيْطَٰنُ فَكَانَ مِنَ ٱلْغَاوِينَ
Amharic Translation - Africa Academy175. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከዚያ እርሱም ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን በዚህም ምክንያት ከጠማሞቹ የሆነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَٰهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُۥٓ أَخْلَدَ إِلَى ٱلْأَرْضِ وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ ٱلْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ذَّٰلِكَ مَثَلُ ٱلْقَوْمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱقْصُصِ ٱلْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy176. ብንፈልግ ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር:: እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ:: ፍላጎቱንም ተከተለ:: ብጤዉም ብታባርረዉም ባታባርረዉም ምላሱን አውጥቶ እንደሚያለከልክ ውሻ ነው:: ይህ የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَآءَ مَثَلًا ٱلْقَوْمُ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَأَنفُسَهُمْ كَانُوا۟ يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy177. የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉትና ነፍሶቻቸውን ይበድሉ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ከፋ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن يَهْدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلْمُهْتَدِى وَمَن يُضْلِلْ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy178. አላህ የሚያቀናው ሰው ሁሉ ቅን ማለት እርሱው ነው:: የሚያጠማቸዉም ሰዎች እነዚያ ከሳሪዎቹ ማለት እነርሱው ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ ءَاذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَآ أُو۟لَٰٓئِكَ كَٱلْأَنْعَٰمِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْغَٰفِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy179. ከአጋንንትም ሆነ ከሰዎች መካከል ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን:: ለእነርሱ የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው:: ለእነርሱም የማያዩባቸው ዓይኖች አሏቸው:: ለእነርሱም የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸው:: እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው:: ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ህዝቦች ናቸው:: እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱው ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِلَّهِ ٱلْأَسْمَآءُ ٱلْحُسْنَىٰ فَٱدْعُوهُ بِهَا وَذَرُوا۟ ٱلَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِىٓ أَسْمَٰٓئِهِۦ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy180. ለአላህ መልካም ስሞች አሉት:: (ዱዓ ስታደርጉ) በእርሷ ጥሩት:: እነዚያን ስሞቹን የሚያጣምሙትን ክፍሎች ተዋቸው:: ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِمَّنْ خَلَقْنَآ أُمَّةٌ يَهْدُونَ بِٱلْحَقِّ وَبِهِۦ يَعْدِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy181. ከፈጠርናቸዉም መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካክሉ ህዝቦችም አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا سَنَسْتَدْرِجُهُم مِّنْ حَيْثُ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy182. እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ሰዎች ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ እናዘናጋቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُمْلِى لَهُمْ إِنَّ كَيْدِى مَتِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy183. ለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ:: ጥበቤ ብርቱ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَتَفَكَّرُوا۟ مَا بِصَاحِبِهِم مِّن جِنَّةٍ إِنْ هُوَ إِلَّا نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy184. በነብያቸው በሙሐመድ ምንም እብደት የሌለበት መሆኑን አያስተውሉምን? እርሱ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَنظُرُوا۟ فِى مَلَكُوتِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا خَلَقَ ٱللَّهُ مِن شَىْءٍ وَأَنْ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ قَدِ ٱقْتَرَبَ أَجَلُهُمْ فَبِأَىِّ حَدِيثٍۭ بَعْدَهُۥ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy185. በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛዉም ነገር አላህ በፈጠራቸው ሁሉ የሞት ጊዜያቸዉም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መሆኑን አያስተውሉምን? ለመሆኑ እነርሱ ከቁርኣን ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَلَا هَادِىَ لَهُۥ وَيَذَرُهُمْ فِى طُغْيَٰنِهِمْ يَعْمَهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy186. አላህ የሚያጠመውን ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ይተዋቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلسَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَىٰهَا قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ رَبِّى لَا يُجَلِّيهَا لِوَقْتِهَآ إِلَّا هُوَ ثَقُلَتْ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَا تَأْتِيكُمْ إِلَّا بَغْتَةً يَسْـَٔلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِىٌّ عَنْهَا قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy187. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትንሳኤ መቼ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ብቻ ነው:: በመከሰቻዋ ጊዜም እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጽላችሁም:: በሰማያትና በምድርም ከበደች:: በድንገት ቢሆን እንጂ አትመጣባችሁም።» በላቸው:: ስለ እርሷ በደንብ እንደተረዳ አድርገው ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ ግን አላህ ዘንድ ብቻ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን ነገር ጠንቅቀው አያውቁም።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ لَٱسْتَكْثَرْتُ مِنَ ٱلْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِىَ ٱلسُّوٓءُ إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy188. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የፈለገዉን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ሆነ ጉዳት ማምጣት አልችልም:: የሩቅን ሚስጥር የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ሁሉ ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር:: እኔም ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَٰحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا فَلَمَّا تَغَشَّىٰهَا حَمَلَتْ حَمْلًا خَفِيفًا فَمَرَّتْ بِهِۦ فَلَمَّآ أَثْقَلَت دَّعَوَا ٱللَّهَ رَبَّهُمَا لَئِنْ ءَاتَيْتَنَا صَٰلِحًا لَّنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy189. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁና ከእርሷም መቀናጆዋን ወደ እርሷ ይረካ ዘንድ የፈጠረ ነው:: በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች:: ጽንሱን ይዛው ሄደች:: ባረገዘችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّآ ءَاتَىٰهُمَا صَٰلِحًا جَعَلَا لَهُۥ شُرَكَآءَ فِيمَآ ءَاتَىٰهُمَا فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy190. መልካምን ልጅ በሰጣቸዉም ጊዜ በሰጣቸው ልጅ (ስም) ለእርሱ ተጋሪዎችን አደረጉለት:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ላቀ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْـًٔا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy191. ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱ ራሳቸው የሚፈጠሩትን ፍጡሮች በአላህ ያጋራሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا يَسْتَطِيعُونَ لَهُمْ نَصْرًا وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy192. ለነርሱም መርዳትንም የማይችሉትን፤ ነፍሶቻቸውንም እንኳን የማይረዱትን ያጋራሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن تَدْعُوهُمْ إِلَى ٱلْهُدَىٰ لَا يَتَّبِعُوكُمْ سَوَآءٌ عَلَيْكُمْ أَدَعَوْتُمُوهُمْ أَمْ أَنتُمْ صَٰمِتُونَ
Amharic Translation - Africa Academy193. ወደ ቅን መንገድ ብትጠሯቸዉም አይከተሏችሁም:: ብትጠሯቸው ወይም ዝምተኞች ብትሆኑም በእናንተ ላይ እኩል ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy194. (ከሀዲያን ሆይ!) እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦቶች ብጤዎቻችሁ የአላህ ባሮች ናቸው:: እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ጥሯቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ:: (መመለስ አይችሉም።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَهُمْ أَرْجُلٌ يَمْشُونَ بِهَآ أَمْ لَهُمْ أَيْدٍ يَبْطِشُونَ بِهَآ أَمْ لَهُمْ أَعْيُنٌ يُبْصِرُونَ بِهَآ أَمْ لَهُمْ ءَاذَانٌ يَسْمَعُونَ بِهَا قُلِ ٱدْعُوا۟ شُرَكَآءَكُمْ ثُمَّ كِيدُونِ فَلَا تُنظِرُونِ
Amharic Translation - Africa Academy195. ለእነርሱ የሚሄዱባቸው እግሮች አሏቸውን? ወይስ የሚጨብጡባቸው እጆች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚያዩባቸው አይኖች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸዉን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያጋራችኃቸውን ጥሩና ከዚያም አሲሩብኝ:: ጊዜም አትስጡኝ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ وَلِـِّۧىَ ٱللَّهُ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْكِتَٰبَ وَهُوَ يَتَوَلَّى ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy196. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ በላቸው) «የእኔ ረዳቴ ያ ቁርኣንን ያወረደልኝ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ ይረዳልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy197. (አጋሪዎች ሆይ! ) «እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦታት ሁሉ ሊረዷችሁ ፍጽሞ አይችሉም:: ነፍሶቻቸውንም እንኳን አይረዱም።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن تَدْعُوهُمْ إِلَى ٱلْهُدَىٰ لَا يَسْمَعُوا۟ وَتَرَىٰهُمْ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ وَهُمْ لَا يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy198. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ቀናው መንገድ እንዲመሩ ብትጠሯቸው አይሰሙም። እነርሱንም የማያዩ ሲሆኑ ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خُذِ ٱلْعَفْوَ وَأْمُرْ بِٱلْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ ٱلْجَٰهِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy199. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይቅርባይነትን ያዝ:: በመልካምም እዘዝ:: ባለጌዎቹንም ተዋቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ نَزْغٌ فَٱسْتَعِذْ بِٱللَّهِ إِنَّهُۥ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy200. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሰይጣን የተንኮል ጉትጎታ ቢያጋጥምህ በአላህ ብቻ ተጠበቅ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ إِذَا مَسَّهُمْ طَٰٓئِفٌ مِّنَ ٱلشَّيْطَٰنِ تَذَكَّرُوا۟ فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy201.እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ:: ወዲያዉም እነርሱ ተመልካቾች ይሆናሉ:
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِخْوَٰنُهُمْ يَمُدُّونَهُمْ فِى ٱلْغَىِّ ثُمَّ لَا يُقْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy202. ወንድሞቻቸዉም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል:: ከዚያም እነርሱ አይገቱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا لَمْ تَأْتِهِم بِـَٔايَةٍ قَالُوا۟ لَوْلَا ٱجْتَبَيْتَهَا قُلْ إِنَّمَآ أَتَّبِعُ مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ مِن رَّبِّى هَٰذَا بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمْ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy203. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዓምርም ባላመጣህላቸው ጊዜ «በራስህ ለምን አትመርጣትም።» ይላሉ:: «ከጌታዬ ወደ እኔ የተወረደውን ብቻ ነው የምከተለው:: ይህ ቁርኣን ከጌታችሁ የተወረደ ሲሆን ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ መረጃ፤ መመሪያና እዝነት ነው።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قُرِئَ ٱلْقُرْءَانُ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥ وَأَنصِتُوا۟ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy204. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቁርኣን በሚነበብበት ጊዜ እርሱን በጥሞና አድምጡ:: ጸጥም በሉ። ይታዘንላችኋልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُر رَّبَّكَ فِى نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ ٱلْجَهْرِ مِنَ ٱلْقَوْلِ بِٱلْغُدُوِّ وَٱلْـَٔاصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْغَٰفِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህን በሚስጥር ተናንሰህና ፈርተህ ከጩኸት በታች በሆነ ድምጽ በጥዋትና በማታ አውሳው:: ከዘንጊዎቹም አትሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَيُسَبِّحُونَهُۥ وَلَهُۥ يَسْجُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy206. እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት እንኳን እርሱን ከመገዛት ፈጽሞ አይኮሩም:: ሁል ጊዜም ያወድሱታል:: ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→