caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 32

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:32

قُلْ مَنْ حَرَّمَ زِينَةَ ٱللَّهِ ٱلَّتِىٓ أَخْرَجَ لِعِبَادِهِۦ وَٱلطَّيِّبَٰتِ مِنَ ٱلرِّزْقِ قُلْ هِىَ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا خَالِصَةً يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያችን ለባሮች የፈጠራትን የአላህን ጌጥ ከሲሳይ ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው?» በላቸው። «እርሷ በትንሳኤ ቀን ለነዚያ በትክክል ላመኑት ብቻ ስትሆን በቅርቢቱ ህይወትም ተገቢያቸው ናት።» በላቸው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«የአላህን ጌጥ ያችን ለባሮቹ የፈጠራትን ከሲሳይም ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው» በላቸው፡፡ «እርሷ በትንሣኤ ቀን ለእነዚያ ላመኑት ብቻ ስትኾን በቅርቢቱ ሕይወት ተገቢያቸው ናት» በላቸው፡፡ እንደዚሁ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70