وَإِذَا لَمْ تَأْتِهِم بِـَٔايَةٍ قَالُوا۟ لَوْلَا ٱجْتَبَيْتَهَا قُلْ إِنَّمَآ أَتَّبِعُ مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ مِن رَّبِّى هَٰذَا بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمْ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy203. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዓምርም ባላመጣህላቸው ጊዜ «በራስህ ለምን አትመርጣትም።» ይላሉ:: «ከጌታዬ ወደ እኔ የተወረደውን ብቻ ነው የምከተለው:: ይህ ቁርኣን ከጌታችሁ የተወረደ ሲሆን ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ መረጃ፤ መመሪያና እዝነት ነው።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበተዓምርም ባልመጣሃቸው ጊዜ (በራስህ) «ለምን አትፈጥራትም» ይላሉ፡፡ ከጌታዬ ወደኔ የተወረደውን ብቻ እከተላለሁ፡፡ ይህ (ቁርኣን) ከጌታችሁ ሲኾን ለሚያምኑ ሕዝቦች መረጃዎችና መምሪያ እዝነትም ነው በላቸው፡፡