وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبْعَثَنَّ عَلَيْهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ مَن يَسُومُهُمْ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ ٱلْعِقَابِ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እስከ ትንሳኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ወገን በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መሆኑን ባስታወቀ ጊዜ (የሆነውን አስታውሳቸው):: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው:: እርሱም በእርግጥ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጌታህም እስከ ትንሣኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ሰው በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መኾኑን ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሳቸው)፡፡ ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ እርሱም በእርግጥ እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡