قَدِ ٱفْتَرَيْنَا عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِى مِلَّتِكُم بَعْدَ إِذْ نَجَّىٰنَا ٱللَّهُ مِنْهَا وَمَا يَكُونُ لَنَآ أَن نَّعُودَ فِيهَآ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّنَا وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَىْءٍ عِلْمًا عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا ٱفْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِٱلْحَقِّ وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْفَٰتِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy89. «አላህ ከእርሷ ከአዳንን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፍን:: አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ወደ እርሷ ልንመለስ አይገባንም:: የጌታችን እውቀቱ ከሁሉ ሰፋ:: በአላህ ላይ ብቻ ተመካን:: ጌታችን ሆይ! በእኛና በወገኖቻችን መካከል ፍረድ:: አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህና።» አለ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«አላህ ከእርሷ ከአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን፡፡ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለእኛ ወደ እርሷ ልንመለስ አይገባንም፡፡ ጌታችን ዕውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ፡፡ በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ፡፡ አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ» (አለ)