caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 53

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:53

هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأْوِيلَهُۥ يَوْمَ يَأْتِى تَأْوِيلُهُۥ يَقُولُ ٱلَّذِينَ نَسُوهُ مِن قَبْلُ قَدْ جَآءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلْحَقِّ فَهَل لَّنَا مِن شُفَعَآءَ فَيَشْفَعُوا۟ لَنَآ أَوْ نُرَدُّ فَنَعْمَلَ غَيْرَ ٱلَّذِى كُنَّا نَعْمَلُ قَدْ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. የዛቻውን ፍጻሜዉን እንጂ ሌላ ይጠባበቃሉን? (አይጠባበቁም):: ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን ግን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት መጥተዋል። ለእኛስ ያማልዱን ዘንድ አማላጆች አሉን? ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው የተለየ ስራ እንድንሰራ ዘንድ ዕድሉ ይሰጠናልን?» ይላሉ:: በእርግጥም ራሳቸውን ይከስራሉ:: ይቀጥፉት የነበረው ሁሉ ከንቱ ሆኖ ያገኙታል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(የዛቻውን) ፍጻሜውን እንጂ ሌላ ይጠባበቃሉን? (አይጠባበቁም)፡፡ ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልክተኞች በእርግጥ በውነት መጥተዋል፡፡ ለእኛ ያማልዱም ዘንድ አማላጆች አልሉን ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላን ሥራ እንሠራ ዘንድ (ወደ ምድረ ዓለም) እንመለሳለን» ይላሉ፡፡ ነፍሶቻቸውን በእርግጥ አከሰሩ፡፡ ይቀጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ጠፋቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70