وَإِذْ قِيلَ لَهُمُ ٱسْكُنُوا۟ هَٰذِهِ ٱلْقَرْيَةَ وَكُلُوا۟ مِنْهَا حَيْثُ شِئْتُمْ وَقُولُوا۟ حِطَّةٌ وَٱدْخُلُوا۟ ٱلْبَابَ سُجَّدًا نَّغْفِرْ لَكُمْ خَطِيٓـَٰٔتِكُمْ سَنَزِيدُ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለነርሱም «በዚች ከተማ ተቀመጡ:: ከእርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ ብሉ:: ‹የምንፈልገው የኃጢታችንን መርገፍ ብቻ ነው።› በሉም:: የከተማይቱን በር አጎንብሳችሁ ግቡ ኃጢአቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና:: በጎ ለሠሩት ሰዎች በእርግጥ እንጨምራለን።» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእነርሱም በተባሉ ጊዜ (አስታውስ) «በዚህች ከተማ ተቀመጡ፡፡ ከእርሷም በሻችሁት ስፍራ ብሉ፡፡ (የምንፈልገው) የኃጢኣታችንን መርገፍ ነው በሉም፡፡ የከተማይቱንም በር አጎንብሳችሁ ግቡ፡፡ ኃጢኣቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና፡፡ በጎ ለሠሩት በእርግጥ እንጨምራለን፡፡»