وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَٰهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُۥٓ أَخْلَدَ إِلَى ٱلْأَرْضِ وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ ٱلْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ذَّٰلِكَ مَثَلُ ٱلْقَوْمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱقْصُصِ ٱلْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy176. ብንፈልግ ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር:: እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ:: ፍላጎቱንም ተከተለ:: ብጤዉም ብታባርረዉም ባታባርረዉም ምላሱን አውጥቶ እንደሚያለከልክ ውሻ ነው:: ይህ የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡