caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 189

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:189

هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَٰحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا فَلَمَّا تَغَشَّىٰهَا حَمَلَتْ حَمْلًا خَفِيفًا فَمَرَّتْ بِهِۦ فَلَمَّآ أَثْقَلَت دَّعَوَا ٱللَّهَ رَبَّهُمَا لَئِنْ ءَاتَيْتَنَا صَٰلِحًا لَّنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy189. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁና ከእርሷም መቀናጆዋን ወደ እርሷ ይረካ ዘንድ የፈጠረ ነው:: በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች:: ጽንሱን ይዛው ሄደች:: ባረገዘችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው፡፡ በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች፡፡ እርሱንም (ፅንሱን) ይዛው ኼደች፡፡ በከበደችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንኾናለን፤» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70