caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 195

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:195

أَلَهُمْ أَرْجُلٌ يَمْشُونَ بِهَآ أَمْ لَهُمْ أَيْدٍ يَبْطِشُونَ بِهَآ أَمْ لَهُمْ أَعْيُنٌ يُبْصِرُونَ بِهَآ أَمْ لَهُمْ ءَاذَانٌ يَسْمَعُونَ بِهَا قُلِ ٱدْعُوا۟ شُرَكَآءَكُمْ ثُمَّ كِيدُونِ فَلَا تُنظِرُونِ

Amharic Translation - Africa Academy195. ለእነርሱ የሚሄዱባቸው እግሮች አሏቸውን? ወይስ የሚጨብጡባቸው እጆች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚያዩባቸው አይኖች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸዉን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያጋራችኃቸውን ጥሩና ከዚያም አሲሩብኝ:: ጊዜም አትስጡኝ።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእነርሱ በእርሳቸው የሚኼዱባቸው እግሮች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በርሳቸው የሚጨብጡባቸው እጆች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸውን «ያጋራችኋቸውን ጥሩ ከዚያም ተተናኮሉኝ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ፤ (አልፈራችሁም)» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70