فَدَلَّىٰهُمَا بِغُرُورٍ فَلَمَّا ذَاقَا ٱلشَّجَرَةَ بَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ وَنَادَىٰهُمَا رَبُّهُمَآ أَلَمْ أَنْهَكُمَا عَن تِلْكُمَا ٱلشَّجَرَةِ وَأَقُل لَّكُمَآ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ لَكُمَا عَدُوٌّ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy22. በማታለልም አዋረዳቸው:: ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ሀፍረተ ገላቸው የሁለቱም ተገለጠባቸው:: ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ (ይለጥፉ) ጀመር:: ጌታቸዉም «ይህችን ዛፍ አልከለከልኳችሁም ነበርን? ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁም ነበርን?» ሲል ጠራቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበማታለልም አዋረዳቸው፡፡ ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ኀፍረተ ገላቸው ለሁለቱም ተገለጠችላቸው፡፡ ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ ጀመሩ፡፡ ጌታቸውም «ከዚህ ዛፍ አልከለከልኋችሁምን ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁምን» ሲል ጠራቸው፡፡