وَٱتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِنۢ بَعْدِهِۦ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُۥ خُوَارٌ أَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّهُۥ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ٱتَّخَذُوهُ وَكَانُوا۟ ظَٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy148. የሙሳም ህዝቦች ከእርሱ መሄድ በኋላ ከጌጦቻቸው በወይፈን ቅርጽ የተቀረጸውን እና የራሱ የሆነ ድምጽ የነበረውን አካል አምላክ አድርገው ያዙት:: እርሱ የማያናግራቸው መንገድን የማይመራቸው መሆኑን አይመለከቱምን? አምላክ አደረጉት:: በዳዮችም ሆኑ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ (መኼድ) በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለርሱ ማግሳት ያለውን (አምላክ አድርገው) ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን? (አምላክ አድርገው) ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡