قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّىَ ٱلْفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَٱلْإِثْمَ وَٱلْبَغْىَ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا۟ بِٱللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِۦ سُلْطَٰنًا وَأَن تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እርም ያደረገው የተገለጸም ሆነ የተደበቀን መጥፎ ስራን፣ ኃጢአትን፤ ያለ አግባብ መበደልንም፣ በእርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን ጣኦት በአላህ ማጋራታችሁንና በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡