وَٱكْتُبْ لَنَا فِى هَٰذِهِ ٱلدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِى ٱلْـَٔاخِرَةِ إِنَّا هُدْنَآ إِلَيْكَ قَالَ عَذَابِىٓ أُصِيبُ بِهِۦ مَنْ أَشَآءُ وَرَحْمَتِى وَسِعَتْ كُلَّ شَىْءٍ فَسَأَكْتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِنَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy156. «ጌታችን ሆይ! ለእኛ በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም ዓለም መልካሟን ጻፍልን:: እኛ ወደ አንተ ተመልሰናል።» (ሲል ሙሳ ጌታውን ለመነ):: አላህም አለ: «ቅጣቴ በእርሱ ልቀጣው የምፈልገውን ሰው እቀጣበታለሁ:: ችሮታዬ ከሁሉም ነገር የሰፋ ነው:: ለእነዚያ ለሚጠነቀቁ ዘካንም ለሚሰጡ ለእነዚያም በአናቅጻችን ለሚያምኑ ሁሉ በእርግጥ እጽፈዋለሁ::»
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ለእኛም በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም (መልካሟን) ጻፍልን፡፡ እኛ ወደ አንተ ተመለስን፡፡» (ሲል ሙሳ ጸለየ፤ አላህም) አለ፡- «ቅጣቴ በእርሱ የምሻውን ሰው እቀጣበታለሁ፡፡ ችሮታየም ነገሩን ሁሉ ሰፋች፡፡ ለእነዚያም ለሚጠነቀቁ፣ ዘካንም ለሚሰጡ፣ ለእነዚያም እነሱ በአንቀጾቻችን ለሚያምኑ በእርግጥ» እጽፋታለሁ፡፡