قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ لَٱسْتَكْثَرْتُ مِنَ ٱلْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِىَ ٱلسُّوٓءُ إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy188. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የፈለገዉን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ሆነ ጉዳት ማምጣት አልችልም:: የሩቅን ሚስጥር የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ሁሉ ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር:: እኔም ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡ ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፡፡ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡