وَلَمَّا جَآءَ مُوسَىٰ لِمِيقَٰتِنَا وَكَلَّمَهُۥ رَبُّهُۥ قَالَ رَبِّ أَرِنِىٓ أَنظُرْ إِلَيْكَ قَالَ لَن تَرَىٰنِى وَلَٰكِنِ ٱنظُرْ إِلَى ٱلْجَبَلِ فَإِنِ ٱسْتَقَرَّ مَكَانَهُۥ فَسَوْفَ تَرَىٰنِى فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُۥ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُۥ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا فَلَمَّآ أَفَاقَ قَالَ سُبْحَٰنَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy143. ሙሳ ለቀጠሮው በመጣና ጌታዉም ባነጋገረው ጊዜ፡ «ጌታዬ ሆይ! በእርግጥ ራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና።» አለ። (አላህም)፡- «እኔን በፍጹም አታየኝም:: ግን ወደ ተራራው ተመልከትና በስፍራው ከረጋ አንተም ታየኛለህ።» አለው:: ጌታዉም ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው:: ሙሳም ጮኸና ወደቀ:: በአንሰራራም ጊዜ «ጌታዬ ጥራት ይገባህ ወደ አንተ ተመለስኩ:: እኔም በጊዜያቴ የአማኞች መጀመሪያ ነኝ።» አለ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ (አላህም)፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም (በወቅቱ) የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡