وَإِذْ قَالَتْ أُمَّةٌ مِّنْهُمْ لِمَ تَعِظُونَ قَوْمًا ٱللَّهُ مُهْلِكُهُمْ أَوْ مُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا قَالُوا۟ مَعْذِرَةً إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከፊሎቹ ህዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጫቸው የሆኑትን ህዝቦች ለምን ትገስጻላችሁ?» ባሉ ጊዜ ገሳጮቹም «በጌታችሁ ዘንድ በቂ ምክንያት እንዲሆንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው።» ባሉበት ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእነሱም (ከፊሎቹ) ሕዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጪአቸው የኾኑትን ሕዝቦች ለምን ትገስፃጻላችሁ» ባሉ ጊዜ (ገሳጮቹ) «ወደ ጌታችሁ በቂ ምክንያት እንዲኾንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው» አሉ፡፡