caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 38

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:38

قَالَ ٱدْخُلُوا۟ فِىٓ أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُم مِّنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ فِى ٱلنَّارِ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا حَتَّىٰٓ إِذَا ٱدَّارَكُوا۟ فِيهَا جَمِيعًا قَالَتْ أُخْرَىٰهُمْ لِأُولَىٰهُمْ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ أَضَلُّونَا فَـَٔاتِهِمْ عَذَابًا ضِعْفًا مِّنَ ٱلنَّارِ قَالَ لِكُلٍّ ضِعْفٌ وَلَٰكِن لَّا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy38. «ከጋኔንና ከሰዉም ከናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ።» ይላቸዋል:: አንዲቱ ቡድን ህዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን ብጤዋን ቡድን ትረግማለች:: መላዉም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙ ጊዜ የኋለኛይቱ (ተከታዮች) ቡድን ለመጀመሪያይቱ (ለአስከታዮች) ቡድን፡- «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው።» ትላለች:: አላህም፡- «ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም።» ይላቸዋል።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ከጋኔንም ከሰውም ከእናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር ኾናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ» ይላቸዋል፡፡ አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር (ያሳሳተቻትን) ብጤዋን ትረግማለች፡፡ መላውም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙም ጊዜ የኋለኛይቱ ለመጀመሪያይቱ (ተከታዮች ለአስከታዮች) «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን፡፡ ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው» ትላለች፡፡ (አላህም)፡- ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም ይላቸዋል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70