caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 150

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:150

وَلَمَّا رَجَعَ مُوسَىٰٓ إِلَىٰ قَوْمِهِۦ غَضْبَٰنَ أَسِفًا قَالَ بِئْسَمَا خَلَفْتُمُونِى مِنۢ بَعْدِىٓ أَعَجِلْتُمْ أَمْرَ رَبِّكُمْ وَأَلْقَى ٱلْأَلْوَاحَ وَأَخَذَ بِرَأْسِ أَخِيهِ يَجُرُّهُۥٓ إِلَيْهِ قَالَ ٱبْنَ أُمَّ إِنَّ ٱلْقَوْمَ ٱسْتَضْعَفُونِى وَكَادُوا۟ يَقْتُلُونَنِى فَلَا تُشْمِتْ بِىَ ٱلْأَعْدَآءَ وَلَا تَجْعَلْنِى مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy150. ሙሳ እየተቆጣና እያዘነ ወደ ህዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «በእኔ ቦታ የተካችሁት ነገር ምንኛ ከፋ! የጌታችሁን ትዕዛዝ ተቻኮላችሁን?» አላቸውና ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው። የወንድሙን የራስ ጸጉር ወደ እርሱ እየጎተተው ያዘ:: ወንድሙም፡- «የእናቴ ልጅ ሆይ! ህዝቦቹ ናቁኝ ሊገድሉኝም ተቃረቡ:: ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ። ከአመጸኞች ህዝቦችም ጋር አታድርገኝ።» አለው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳም እየተቆጣና እያዘነ ወደ ሕዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «ከእኔ በኋላ በእኔ ላይ የተካችሁት ነገር ከፋ! የጌታችሁን ትእዛዝ ተቻኮላችሁን?» አላቸው፡፡ ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው፡፡ የወንድሙንም ራስ (ጸጉር) ወደርሱ የሚጎትተው ሲኾን ያዘ፡፡ (ወንድሙም)፡- «የናቴ ልጅ ሆይ! ሕዝቦቹ ናቁኝ፡፡ ሊገድሉኝም ተቃራቡ፡፡ ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ፡፡ ከአመጸኞች ሕዝቦችም ጋር አታድርገኝ» አለው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70