caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 131

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:131

فَإِذَا جَآءَتْهُمُ ٱلْحَسَنَةُ قَالُوا۟ لَنَا هَٰذِهِۦ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَطَّيَّرُوا۟ بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ أَلَآ إِنَّمَا طَٰٓئِرُهُمْ عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy131. ምቾት በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ ተገቢ ናት።» ይላሉ። ክፋት ባገኛቸው ጊዜ ግን ሙሳና አብረውት ያሉት ክፉ ገዶቻቸው እንደሆኑ ያስባሉ። አስተውሉ! ክፉ እድላቸው (ገደቢስነታቸው) ከአላህ ዘንድ ነው:: አብዛኞቻቸው ግን ይህን አያውቁም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqደጊቱም ነገር (ምቾት) በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ (ተገቢ) ናት» ይላሉ፡፡ ክፉትም ብታገኛቸው በሙሳና አብረውት ባሉት ገደቢስነት ያመካኛሉ፡፡ ንቁ! ገደቢስነታቸው አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70