وَنَادَىٰٓ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ أَصْحَٰبَ ٱلنَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا قَالُوا۟ نَعَمْ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌۢ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy44. የገነት ሰዎች የእሳት ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ሆኖ አገኘን እናንተስ ጌታችሁ የዛተባችሁን እውነት ሆኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ ይጣራሉ:: የእሳት ሰዎችም «አዎን አገኘን» ይላሉ:: በመካከላቸዉም «የአላህ እርግማን በበደለኞች ላይ ይሁን» ሲል አዋጅ ነጋሪ ያውጃል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡