وَلَا تَقْعُدُوا۟ بِكُلِّ صِرَٰطٍ تُوعِدُونَ وَتَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ مَنْ ءَامَنَ بِهِۦ وَتَبْغُونَهَا عِوَجًا وَٱذْكُرُوٓا۟ إِذْ كُنتُمْ قَلِيلًا فَكَثَّرَكُمْ وَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy86. «ሰዎችን የምታስፈራሩ፤ ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱና የአላህን መንገድ መጥመሟንም የምትፈልጉ ሆናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ:: ጥቂቶች በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የአጥፊ ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረም ተመልከቱ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq« (ሰዎችን) የምታስፈራሩና ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱ መጥመሟንም የምትፈልጉዋት ኾናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ፡፡ ጥቂቶችም በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ፡፡»