وَجَٰوَزْنَا بِبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْبَحْرَ فَأَتَوْا۟ عَلَىٰ قَوْمٍ يَعْكُفُونَ عَلَىٰٓ أَصْنَامٍ لَّهُمْ قَالُوا۟ يَٰمُوسَى ٱجْعَل لَّنَآ إِلَٰهًا كَمَا لَهُمْ ءَالِهَةٌ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy138. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሻገርናቸው:: ለእነርሱ በሆኑ ጣኦታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ህዝቦች አጠገብ አለፉም:: «ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ ለሰዎቹ አማልክት እንዳሏቸው ሁሉ ለኛም አምላክን አድርግልን።» አሉት:: «እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገርናቸው፡፡ ለእነርሱ በኾኑ ጣዖታት (መገዛት) ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ላይ አለፉም፡፡ «ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን» አሉት፡፡ «እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡