وَنَزَعْنَا مَا فِى صُدُورِهِم مِّنْ غِلٍّ تَجْرِى مِن تَحْتِهِمُ ٱلْأَنْهَٰرُ وَقَالُوا۟ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى هَدَىٰنَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهْتَدِىَ لَوْلَآ أَنْ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ لَقَدْ جَآءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلْحَقِّ وَنُودُوٓا۟ أَن تِلْكُمُ ٱلْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ጥላቻም እናስወግዳለን:: ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ:: «ለዚያም ወደዚህ ላደረሰን ሥራ ለመራን ለአላህ ብቻ ምስጋና ይገባው:: አላህ ባልመራን ኖሮ ወደዚህ አንመራም ነበር:: የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት ላይ ሲሆኑ መጥተውልናል።» ይላሉ:: «ይህ ገነት ትሠሩት በነበራችሁት እንድትወርሱት የተደረጋችሁት ነው።» በማለት ይጠራሉ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበደረቶቻቸው ውስጥ ያለውንም ጥላቻ እናስወግዳለን፡፡ ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ፡፡ «ለዚያም ወደዚህ (ላደረሰን ሥራ) ለመራን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡ አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር፡፡ የጌታችን መልክተኞች በእውነት ላይ ሲኾኑ በእርግጥ መጥተውልናል» ይላሉ፡፡ ይህች ገነት ትሠሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ፡፡