caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 54

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:54

إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ يُغْشِى ٱلَّيْلَ ٱلنَّهَارَ يَطْلُبُهُۥ حَثِيثًا وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ وَٱلنُّجُومَ مُسَخَّرَٰتٍۭ بِأَمْرِهِۦٓ أَلَا لَهُ ٱلْخَلْقُ وَٱلْأَمْرُ تَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy54. (ሰዎች ሆይ) ጌታችሁ አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረና ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው። ቀኑንም በሌሊቱ ይሸፍነዋል:: ሁለቱም እርስ በእርስ በፍጥነት ይፈላለጋሉ:: ጸሐይ ጨረቃና ከዋክብት በትዕዛዙ የተገሩ ናቸው። አስተውሉ! መፍጠርም ማዘዝም የእርሱ (የአላህ) ነው:: የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ክብሩ ላቀ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም (ለክብሩ በምስማማ መልኩ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70