أَوَعَجِبْتُمْ أَن جَآءَكُمْ ذِكْرٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنكُمْ لِيُنذِرَكُمْ وَٱذْكُرُوٓا۟ إِذْ جَعَلَكُمْ خُلَفَآءَ مِنۢ بَعْدِ قَوْمِ نُوحٍ وَزَادَكُمْ فِى ٱلْخَلْقِ بَصْۜطَةً فَٱذْكُرُوٓا۟ ءَالَآءَ ٱللَّهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. ያስጠነቅቃችሁ ዘንድ ከናንተው መካከል በሆነ ሰው ከጌታችሁ የሆነ ግሳጼ ስለመጣባችሁ ትደነቃላችሁን? ከኑህ ህዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጥረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የሻችሁትን ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ከጌታችሁ የኾነ ግሣጼ ከእናንተው ውስጥ ባንድ ሰው ላይ ያስጠነቀቃችሁ ዘንድ ቢመጣባችሁ ትደነቃላችሁን? ከኑሕም ሕዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጠረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ የሻችሁትንም ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡»