caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-A'raaf፣ አንቀጽ 187

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 39 · 7:187

يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلسَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَىٰهَا قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ رَبِّى لَا يُجَلِّيهَا لِوَقْتِهَآ إِلَّا هُوَ ثَقُلَتْ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَا تَأْتِيكُمْ إِلَّا بَغْتَةً يَسْـَٔلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِىٌّ عَنْهَا قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy187. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትንሳኤ መቼ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ብቻ ነው:: በመከሰቻዋ ጊዜም እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጽላችሁም:: በሰማያትና በምድርም ከበደች:: በድንገት ቢሆን እንጂ አትመጣባችሁም።» በላቸው:: ስለ እርሷ በደንብ እንደተረዳ አድርገው ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ ግን አላህ ዘንድ ብቻ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን ነገር ጠንቅቀው አያውቁም።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከሰዓቲቱ መቼ እንደምትረጋ (እንደምትመጣ) ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ነው፡፡ በጊዜዋ እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጣትም፡፡ በሰማያትና በምድርም ከበደች፡፡ በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣችሁም» በላቸው፡፡ ከእርሷ አጥብቀህ እንደ ተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70