ሱረቱ As-Saaffaat الصافات
182 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 56
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ صَفًّا
Amharic Translation - Africa Academy1. መሰለፍን በሚሰለፉት፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱلزَّٰجِرَٰتِ زَجْرًا
Amharic Translation - Africa Academy2. (ደመና) መንዳትን በሚነዱት፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱلتَّٰلِيَٰتِ ذِكْرًا
Amharic Translation - Africa Academy3. ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ إِلَٰهَكُمْ لَوَٰحِدٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ ٱلْمَشَٰرِقِ
Amharic Translation - Africa Academy5. እርሱ ያ በሰማያትና በምድር በመካካለቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው:: የምስራቆችም ጌታ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنْيَا بِزِينَةٍ ٱلْكَوَاكِبِ
Amharic Translation - Africa Academy6. እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት (አስዋብናት)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَحِفْظًا مِّن كُلِّ شَيْطَٰنٍ مَّارِدٍ
Amharic Translation - Africa Academy7. አመጸኛ ከሆነ ሰይጣንም ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى ٱلْمَلَإِ ٱلْأَعْلَىٰ وَيُقْذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٍ
Amharic Translation - Africa Academy8. ወደ ላይኛው ሰራዊት አያደምጡም፤ ከየአቅጣጫውም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፤ (ይቀጠቀጣሉ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
دُحُورًا وَلَهُمْ عَذَابٌ وَاصِبٌ
Amharic Translation - Africa Academy9. የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፤ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا مَنْ خَطِفَ ٱلْخَطْفَةَ فَأَتْبَعَهُۥ شِهَابٌ ثَاقِبٌ
Amharic Translation - Africa Academy10. ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውኑም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር (እርሱ ይሰማዋል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱسْتَفْتِهِمْ أَهُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَم مَّنْ خَلَقْنَآ إِنَّا خَلَقْنَٰهُم مِّن طِينٍ لَّازِبٍۭ
Amharic Translation - Africa Academy11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ ከእነርሱ በፊት የፈጠረነው ፍጡር? እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ عَجِبْتَ وَيَسْخَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. ይልቁንም ማስተባበላቸው አስደነቀህ፤ በመደነቅህም ይሳለቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا ذُكِّرُوا۟ لَا يَذْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy13. በተገሰጹም ጊዜ አይገሰጹም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا رَأَوْا۟ ءَايَةً يَسْتَسْخِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ተዓምርንም ባዩ ጊዜ ለመሳለቅ ይጣጣራሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy15. አሉም: «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَءِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبْعُوثُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በሆን ጊዜ የምንቀስቀስ ነን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَءَابَآؤُنَا ٱلْأَوَّلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. «የቀድሞዎቹ አባቶቻችንም እንደዚሁ ይቀሰቀሳሉን?» (ይላሉ።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ نَعَمْ وَأَنتُمْ دَٰخِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አዎን! እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنَّمَا هِىَ زَجْرَةٌ وَٰحِدَةٌ فَإِذَا هُمْ يَنظُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy19. እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት:: እነርሱም ወዲያውኑ ምን እንደሚፈጸምባቸው ያያሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ يَٰوَيْلَنَا هَٰذَا يَوْمُ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy20. «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው።» (ይላሉም)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا يَوْمُ ٱلْفَصْلِ ٱلَّذِى كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉት የነበራችት መለያው ቀን ነው።» ይባላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱحْشُرُوا۟ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ وَأَزْوَٰجَهُمْ وَمَا كَانُوا۟ يَعْبُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy22. (ለመላዕክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ከአላህ ሌላ ይገዟቸው የነበሩትንም ጣዖታት በአንድ ሰብስቡ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِن دُونِ ٱللَّهِ فَٱهْدُوهُمْ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy23. ከአላህ ውጭ (ይገዟቸው የነበሩትን ሰብስቡ)። ከዚያም ወደ ገሀነም መንገድ ምሯቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقِفُوهُمْ إِنَّهُم مَّسْـُٔولُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. «እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና አቁሟቸዉም።» (ይባላል።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا لَكُمْ لَا تَنَاصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. ለነርሱም «ምን ሆናችሁ ነው የማትረዳዱት?» ይባላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ هُمُ ٱلْيَوْمَ مُسْتَسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy26. በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ማምለጫ የሌላቸው ወራዳዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَسَآءَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. እርስ በራሳቸውም የሚወቃቀሱም ሆነው ይመጣሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ إِنَّكُمْ كُنتُمْ تَأْتُونَنَا عَنِ ٱلْيَمِينِ
Amharic Translation - Africa Academy28. (ተከታዮቹ ለአስከታዮቻቸው) «እናንተ በጉልበት ትመጡብን ነበር» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ بَل لَّمْ تَكُونُوا۟ مُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. (አስከታዮቹም) ይላሉ፡- «አይደለም ፈጽሞ አማኞች አልነበራችሁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيْكُم مِّن سُلْطَٰنٍۭ بَلْ كُنتُمْ قَوْمًا طَٰغِينَ
Amharic Translation - Africa Academy30. «ለእኛም በናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም። በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ህዝቦች ነበራችሁና ነው እንጂ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَحَقَّ عَلَيْنَا قَوْلُ رَبِّنَآ إِنَّا لَذَآئِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy31. «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል የተረጋገጠብንና ሁላችንም ቅጣቱን ቀማሽ ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَغْوَيْنَٰكُمْ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. «እኛ ጠማሞች ስለ ነበርን ወደ ጥመት ጠራናችሁም።» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنَّهُمْ يَوْمَئِذٍ فِى ٱلْعَذَابِ مُشْتَرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفْعَلُ بِٱلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy34. እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሰራለን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُمْ كَانُوٓا۟ إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. እነርሱ «ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም» በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓا۟ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَّجْنُونٍۭ
Amharic Translation - Africa Academy36. «እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን እንዴ?» ይሉ ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ جَآءَ بِٱلْحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. አይደለም እውነቱን ሃይማኖት አመጣ፤ መልዕክተኞቹንም እውነተኝነታቸውን አረጋገጠ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّكُمْ لَذَآئِقُوا۟ ٱلْعَذَابِ ٱلْأَلِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy38. እናንተ አሳማሚውን ቅጣት እርግጥ ቀማሾች ናችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلْمُخْلَصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy40. ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ رِزْقٌ مَّعْلُومٌ
Amharic Translation - Africa Academy41. እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አለላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكْرَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. ፍራፋሬዎች (አሉላቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِى جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy43. በድሎት ገነቶች ውስጥ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَلَىٰ سُرُرٍ مُّتَقَٰبِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy44. ፊት ለፊት የሚተያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ ይንፈላሰሳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُطَافُ عَلَيْهِم بِكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍۭ
Amharic Translation - Africa Academy45. ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዙ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَيْضَآءَ لَذَّةٍ لِّلشَّٰرِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy46. ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከሆነች፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy47. በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም:: እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعِندَهُمْ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرْفِ عِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy48. እነርሱ ዘንድ ዓይናቸውን በባሎቻቸው ላይ ብቻ አሳጣሪዎች የሆኑ ዓይናማ ሴቶች አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَأَنَّهُنَّ بَيْضٌ مَّكْنُونٌ
Amharic Translation - Africa Academy49. እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) እንቁላል ይመስላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَسَآءَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy50. የሚጠያያቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ قَآئِلٌ مِّنْهُمْ إِنِّى كَانَ لِى قَرِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy51. ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ (እንዲህ) ይላል: «እኔ ጓደኛ ነበረኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَقُولُ أَءِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُصَدِّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy52. (እንዲህ) የሚል: ‹በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَءِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَدِينُونَ
Amharic Translation - Africa Academy53. ‹በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆነ ጊዜ እኛ በእርግጥ እኛ እንመረመራለን?› የሚልም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ هَلْ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy54. እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱطَّلَعَ فَرَءَاهُ فِى سَوَآءِ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy55. ይመለከታልም በገሀነም መካከልም ጓደኛውን ያየዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ تَٱللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرْدِينِ
Amharic Translation - Africa Academy56. ይላል «በአላህ እምላለሁ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْلَا نِعْمَةُ رَبِّى لَكُنتُ مِنَ ٱلْمُحْضَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy57. «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር።» (ይላል)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَا نَحْنُ بِمَيِّتِينَ
Amharic Translation - Africa Academy58. (የገነት ሰዎች ይላሉ)፡ «እኛ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን?»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا مَوْتَتَنَا ٱلْأُولَىٰ وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy59. «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር እኛም የምንቀጣ አይደለንም» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy60.ይህ ለገነት ሰዎች የተወሳው እርሱ በእርግጥ ታላቅ እድል ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِمِثْلِ هَٰذَا فَلْيَعْمَلِ ٱلْعَٰمِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy61. ለዚህ ብጤ ሰሪዎች ሁሉ ይስሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَذَٰلِكَ خَيْرٌ نُّزُلًا أَمْ شَجَرَةُ ٱلزَّقُّومِ
Amharic Translation - Africa Academy62. በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا جَعَلْنَٰهَا فِتْنَةً لِّلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy63. እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهَا شَجَرَةٌ تَخْرُجُ فِىٓ أَصْلِ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy64. እርሷ ከገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
طَلْعُهَا كَأَنَّهُۥ رُءُوسُ ٱلشَّيَٰطِينِ
Amharic Translation - Africa Academy65. እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنَّهُمْ لَـَٔاكِلُونَ مِنْهَا فَمَالِـُٔونَ مِنْهَا ٱلْبُطُونَ
Amharic Translation - Africa Academy66. እነርሱ ከእርሷ በይዎች ናቸው:: ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ إِنَّ لَهُمْ عَلَيْهَا لَشَوْبًا مِّنْ حَمِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy67. ከዚያ ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅልን መጠጥ አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ إِنَّ مَرْجِعَهُمْ لَإِلَى ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy68. ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُمْ أَلْفَوْا۟ ءَابَآءَهُمْ ضَآلِّينَ
Amharic Translation - Africa Academy69. እነርሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَهُمْ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمْ يُهْرَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy70. እነርሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ضَلَّ قَبْلَهُمْ أَكْثَرُ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy71. ከእነርሱም በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ ህዝቦች አብዛሀኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy72. በውስጣቸዉም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُنذَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلْمُخْلَصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy74. ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ نَادَىٰنَا نُوحٌ فَلَنِعْمَ ٱلْمُجِيبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy75. ኑህም በእርግጥ ጠራን:: ምንኛ ያማርን ምላሽ ሰጪ ነን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَجَّيْنَٰهُ وَأَهْلَهُۥ مِنَ ٱلْكَرْبِ ٱلْعَظِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy76. እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلْنَا ذُرِّيَّتَهُۥ هُمُ ٱلْبَاقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy77. ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِى ٱلْـَٔاخِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy78. በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካምን ዝና ተውን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَلَٰمٌ عَلَىٰ نُوحٍ فِى ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy79. «በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑህ ላይ ይሁን።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy80. እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُۥ مِنْ عِبَادِنَا ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy81. እርሱ ከአማኞች ባሮቻችን ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ أَغْرَقْنَا ٱلْـَٔاخَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy82. ከዚያም ሌሎችን አሰመጥን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِۦ لَإِبْرَٰهِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ኢብራሂምም በእርግጥ ከወገኖቹ አንዱ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ جَآءَ رَبَّهُۥ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy84. ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ የሆነውን (አስታውስ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَاذَا تَعْبُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy85. ለአባቱና ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ: «ምንን ትገዛላችሁ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَئِفْكًا ءَالِهَةً دُونَ ٱللَّهِ تُرِيدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy86. «ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy87. «በዓለማቱ ጌታስ ሀሳባችሁ ምንድ ነው?።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَنَظَرَ نَظْرَةً فِى ٱلنُّجُومِ
Amharic Translation - Africa Academy88. በከዋክብት መመልከትን ተመለከተ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقَالَ إِنِّى سَقِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy89. እኔ «በሽተኛ ነኝ» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَوَلَّوْا۟ عَنْهُ مُدْبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy90. እነርሱም ከእርሱ የሸሹ ሆነው ሄዱ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَرَاغَ إِلَىٰٓ ءَالِهَتِهِمْ فَقَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy91. ከዚያ እሱ ወደ አማልዕክቶቻቸው ተዘነበለ፤ (እንዲህ) አለም፡- «አትበሉም እንዴ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا لَكُمْ لَا تَنطِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy92. «ምንም የማትናገሩበትስ ምን ምክኒያት አላችሁ?»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَرَاغَ عَلَيْهِمْ ضَرْبًۢا بِٱلْيَمِينِ
Amharic Translation - Africa Academy93. በቀኝ (እጁ) የሚመታቸዉም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَقْبَلُوٓا۟ إِلَيْهِ يَزِفُّونَ
Amharic Translation - Africa Academy94. ወደ እርሱም ሰዎቹ እየሮጡ መጡ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَتَعْبُدُونَ مَا تَنْحِتُونَ
Amharic Translation - Africa Academy95. አለ: «የምትጠርቡትን ትገዛላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy96. «አላህ እናንተንም ሆነ የምትሰሩትን ሁሉ የፈጠረ ሲሆን» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ ٱبْنُوا۟ لَهُۥ بُنْيَٰنًا فَأَلْقُوهُ فِى ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy97. «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَرَادُوا۟ بِهِۦ كَيْدًا فَجَعَلْنَٰهُمُ ٱلْأَسْفَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy98. ለእርሱ ተንኮልን አስቡ ወራዶችም አደረግናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ إِنِّى ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّى سَيَهْدِينِ
Amharic Translation - Africa Academy99. አለም፡- «እኔ ወደ ጌታየ ሂያጅ ነኝ፤ በእርግጥ ይመራኛልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy100. «ጌታየ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy101. ታጋሽም በሆነ ልጅም አበሰርነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy102. ከእርሱ ጋርም (ለስራ) በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በህልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ትላለህ?» አለው። «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ስራ፤ አላህ ቢሻ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّآ أَسْلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلْجَبِينِ
Amharic Translation - Africa Academy103. ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَٰدَيْنَٰهُ أَن يَٰٓإِبْرَٰهِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy104. ጠራነዉም: «ኢብራሂም ሆይ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَدْ صَدَّقْتَ ٱلرُّءْيَآ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy105. «ራዕዩን በርግጥ እውን አደረግክ።» እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ
Amharic Translation - Africa Academy106. ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَفَدَيْنَٰهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy107. በታላቅ እርድም መስዕዋት ቤዛ አደረግንለት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِى ٱلْـَٔاخِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy108. በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy109. ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy110. ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُۥ مِنْ عِبَادِنَا ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy111. እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy112. በኢስሐቅም አበሰርነው። ከመልካሞች የሆነ ነብይ ሲሆን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبَٰرَكْنَا عَلَيْهِ وَعَلَىٰٓ إِسْحَٰقَ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحْسِنٌ وَظَالِمٌ لِّنَفْسِهِۦ مُبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy113. በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን። ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሰሪ አለ:: ነፍሱን በግልጽ በዳይም አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy114. በሙሳና በሀሩን ላይ በእርግጥ ለገስን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَجَّيْنَٰهُمَا وَقَوْمَهُمَا مِنَ ٱلْكَرْبِ ٱلْعَظِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy115. እነርሱንም ሆነ ህዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَصَرْنَٰهُمْ فَكَانُوا۟ هُمُ ٱلْغَٰلِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy116. ረዳናቸውናም እነርሱ አሸናፊዎቹ ሆኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَءَاتَيْنَٰهُمَا ٱلْكِتَٰبَ ٱلْمُسْتَبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy117. በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهَدَيْنَٰهُمَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلْمُسْتَقِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy118. ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِمَا فِى ٱلْـَٔاخِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy119. በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካምን ዝናን ተውንላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَلَٰمٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy120. ሰላም በሙሳና በሀሩን ላይ ይሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy121. እኛ ልክ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُمَا مِنْ عِبَادِنَا ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy122. ሁለቱም በትክክል በአላህ ካመኑት ባሮቻችን ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy123. ኢልያስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦٓ أَلَا تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy124. ለህዝቦቹም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አላህን አትፈሩምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ ٱلْخَٰلِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy125. «ስዕልን ትገዛላችሁ? ከስዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነዉም አምላክ ትተዋላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهَ رَبَّكُمْ وَرَبَّ ءَابَآئِكُمُ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy126. «አላህ ጌታችሁና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁንም ጌታ ትተዋላችሁን?»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy127. አስተባበሉትም ስለዚህ እነርሱ ለቅጣት የሚጣዱ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلْمُخْلَصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy128. ንጹህ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِى ٱلْـَٔاخِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy129. በእነርሱ ላይም በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِلْ يَاسِينَ
Amharic Translation - Africa Academy130. ሰላም በኢልያስ ላይ ይሁን፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy131. እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُۥ مِنْ عِبَادِنَا ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy132. እርሱ በእርግጥ ከምዕመናን ባሮቻችን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ لُوطًا لَّمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy133. ሉጥም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ نَجَّيْنَٰهُ وَأَهْلَهُۥٓ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy134. እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳናቸው ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عَجُوزًا فِى ٱلْغَٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy135. በቅጣቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ دَمَّرْنَا ٱلْـَٔاخَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy136. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّكُمْ لَتَمُرُّونَ عَلَيْهِم مُّصْبِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy137. (መኮች ሆይ)፤ እናንተም በእነርሱ መኖሪያዎች ላይ ያነጋችሁ ስትሆኑ ታልፋላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبِٱلَّيْلِ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy138. በሌሊትም ታልፋላችሁ:: ልብ አታደርጉምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy139. ዩኑስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ أَبَقَ إِلَى ٱلْفُلْكِ ٱلْمَشْحُونِ
Amharic Translation - Africa Academy140. ወደ ተሞላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ ٱلْمُدْحَضِينَ
Amharic Translation - Africa Academy141. እጣም ተጣጣለ፤ ከተሸነፉትም ሆነ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱلْتَقَمَهُ ٱلْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy142. እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳ ነባሪው ዋጠው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَوْلَآ أَنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلْمُسَبِّحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy143. እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነ ኖሮ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَلَبِثَ فِى بَطْنِهِۦٓ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
Amharic Translation - Africa Academy144. እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَنَبَذْنَٰهُ بِٱلْعَرَآءِ وَهُوَ سَقِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy145. እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው ባህር ዳርቻ ላይ ጣልነዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنۢبَتْنَا عَلَيْهِ شَجَرَةً مِّن يَقْطِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy146. በእርሱም ላይ በአጠገቡ ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَرْسَلْنَٰهُ إِلَىٰ مِا۟ئَةِ أَلْفٍ أَوْ يَزِيدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy147. ወደ መቶ ሺህ ሰዎችም ላክነው፤ ከቶውንም ይጨምራሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَـَٔامَنُوا۟ فَمَتَّعْنَٰهُمْ إِلَىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy148. አመኑም። እስከ ጊዜው ድረስም አጣቀምናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱسْتَفْتِهِمْ أَلِرَبِّكَ ٱلْبَنَاتُ وَلَهُمُ ٱلْبَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመካን ሰዎች ጠይቃቸዉም: «ለጌታህ ሴት ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ خَلَقْنَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ إِنَٰثًا وَهُمْ شَٰهِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy150. «ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላዕክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَآ إِنَّهُم مِّنْ إِفْكِهِمْ لَيَقُولُونَ
Amharic Translation - Africa Academy151. አስተውሉ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው የተነሳ ይላሉ:
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَدَ ٱللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy152.፡- «አላህ መላዕክትን ወለደ።» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَصْطَفَى ٱلْبَنَاتِ عَلَى ٱلْبَنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy153. በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጠን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy154. ለእናንተ ምን አስረጂ አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy155. አትገነዘቡምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ لَكُمْ سُلْطَٰنٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy156. ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጂ አላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأْتُوا۟ بِكِتَٰبِكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy157. «እውነተኞች እንደሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلُوا۟ بَيْنَهُۥ وَبَيْنَ ٱلْجِنَّةِ نَسَبًا وَلَقَدْ عَلِمَتِ ٱلْجِنَّةُ إِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy158. በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ:: አጋንንትም ሆኑ ይህን ባዩች በእሳት የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ አውቀዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy159. አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلْمُخْلَصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy160. ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች በአላህ ላይ አይዋሹም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy161. (ካሐዲያን ሆይ!) እናንተም የምትገዟቸዉም ሁሉ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَآ أَنتُمْ عَلَيْهِ بِفَٰتِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy162. በእርሱ በአላህ ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا مَنْ هُوَ صَالِ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy163. ያንን እርሱ ገሀነም ገቢ የሆነውን ቢሆን እንጂ (አጥማሚዎች አይደላችሁም)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا مِنَّآ إِلَّا لَهُۥ مَقَامٌ مَّعْلُومٌ
Amharic Translation - Africa Academy164. (መላእክቶችም አሉ)? «ከእኛ አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّا لَنَحْنُ ٱلصَّآفُّونَ
Amharic Translation - Africa Academy165. «እኛም ጌታን ለመገዛት ተሰላፊዎቹ እኛ ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّا لَنَحْنُ ٱلْمُسَبِّحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy166. «እኛም አላህን አጥሪዎቹ እኛው ነን።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن كَانُوا۟ لَيَقُولُونَ
Amharic Translation - Africa Academy167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ (ከሓዲያን) በእርግጥ ይሉ ነበር:
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَوْ أَنَّ عِندَنَا ذِكْرًا مِّنَ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy168. «ከቀድሞዎቹ መጽሐፍ ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረ ኖሮ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَكُنَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلْمُخْلَصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy169. «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَفَرُوا۟ بِهِۦ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy170. ግን ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ላይ ካዱ። ወደ ፊትም በእርግጥ ያውቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ سَبَقَتْ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy171. የእርዳታ ቃላችንም መልዕክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُمْ لَهُمُ ٱلْمَنصُورُونَ
Amharic Translation - Africa Academy172. እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ ٱلْغَٰلِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy173. ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy174. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከመካ ከሓዲያን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር ተዋቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَبْصِرْهُمْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy175. ተመልከታቸዉም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ያያሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَبِعَذَابِنَا يَسْتَعْجِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy176. በቅጣታችንም ያቻኩሉናልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمْ فَسَآءَ صَبَاحُ ٱلْمُنذَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy177. በቀያቸዉም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy178. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ተዋቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَبْصِرْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy179. ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سُبْحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy180. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy181. በመልዕክተኞቹም ላይ ሰላም ይሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy182. ምስጋና ሁሉም ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→