ሱረቱ Saad ص
88 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 38
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ صٓ وَٱلْقُرْءَانِ ذِى ٱلذِّكْرِ
Amharic Translation - Africa Academy1. ሷድ፤ የግሳፄ ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فِى عِزَّةٍ وَشِقَاقٍ
Amharic Translation - Africa Academy2. ይልቁንም እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በከባድ ትዕቢትና በአጓጉል ክርክር ውስጥ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَمْ أَهْلَكْنَا مِن قَبْلِهِم مِّن قَرْنٍ فَنَادَوا۟ وَّلَاتَ حِينَ مَنَاصٍ
Amharic Translation - Africa Academy3. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙን አጥፍተናል:: ጊዜው የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ وَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٌ كَذَّابٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለመጣላቸውም ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ ድግምተኛ ጠንቋይ ውሸታም ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَجَعَلَ ٱلْـَٔالِهَةَ إِلَٰهًا وَٰحِدًا إِنَّ هَٰذَا لَشَىْءٌ عُجَابٌ
Amharic Translation - Africa Academy5. «አማልዕክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱنطَلَقَ ٱلْمَلَأُ مِنْهُمْ أَنِ ٱمْشُوا۟ وَٱصْبِرُوا۟ عَلَىٰٓ ءَالِهَتِكُمْ إِنَّ هَٰذَا لَشَىْءٌ يُرَادُ
Amharic Translation - Africa Academy6. ከእነርሱም መካከል ባላባቶቹ (እንዲህ) እያሉ አዘገሙ: «ሂዱ በአማልክቶቻችሁም መገዛት ላይ ጽኑ:: ይህ ከእኛ የሚፈለግ ነገር ነውና
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا سَمِعْنَا بِهَٰذَا فِى ٱلْمِلَّةِ ٱلْـَٔاخِرَةِ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا ٱخْتِلَٰقٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. «ይህንንም አስተምህሮት ከኋለኛይቱ (ከመጨረሻይቱ) ሃይማኖት አልሰማንም:: ይህ ውሸትን መፍጠር እንጂ ሌላ አይደለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَءُنزِلَ عَلَيْهِ ٱلذِّكْرُ مِنۢ بَيْنِنَا بَلْ هُمْ فِى شَكٍّ مِّن ذِكْرِى بَل لَّمَّا يَذُوقُوا۟ عَذَابِ
Amharic Translation - Africa Academy8. «ከመካከላችን በእርሱ ላይ ብቻ ቁርኣን ተወረደን?» (እያሉ አዘገሙ።) ይልቁን እነርሱ ከግሳጼየ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእርግጥም ቅጣትን ገና አልቀመሱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ عِندَهُمْ خَزَآئِنُ رَحْمَةِ رَبِّكَ ٱلْعَزِيزِ ٱلْوَهَّابِ
Amharic Translation - Africa Academy9. ወይስ የአሸናፊውና የለጋሹ ጌታህ የአላህ የችሮታው መካዚኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ لَهُم مُّلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَلْيَرْتَقُوا۟ فِى ٱلْأَسْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy10. ወይስ የሰማይ የምድር እና የመካከላቸዉም ንግስና የእነርሱ ነውን? (ነው ካሉ) እስቲ በመሰላሎች ወደ ላይ ይውጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
جُندٌ مَّا هُنَالِكَ مَهْزُومٌ مِّنَ ٱلْأَحْزَابِ
Amharic Translation - Africa Academy11. እነርሱም እዚያ ዘንድ ከአህዛብ ሁሉ ተሸናፊ የሆነ ሰራዊት ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَعَادٌ وَفِرْعَوْنُ ذُو ٱلْأَوْتَادِ
Amharic Translation - Africa Academy12. ከእነርሱም በፊት የኑህ ህዝቦች፤ ዓድ እና የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባብለዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَثَمُودُ وَقَوْمُ لُوطٍ وَأَصْحَٰبُ لْـَٔيْكَةِ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلْأَحْزَابُ
Amharic Translation - Africa Academy13. ሰሙድም፤ የሉጥ ሰዎችም፤ የአይካ ሰዎችም፤ አስተባበሉ:: እነዚህ አህዛቦቹ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن كُلٌّ إِلَّا كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ
Amharic Translation - Africa Academy14. ሁሉም መልዕክተኞችን ያስዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከዚያ ቅጣቴ ተረጋገጠባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَنظُرُ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً مَّا لَهَا مِن فَوَاقٍ
Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ያችን ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲት ጩኸት ብቻ እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ رَبَّنَا عَجِّل لَّنَا قِطَّنَا قَبْلَ يَوْمِ ٱلْحِسَابِ
Amharic Translation - Africa Academy16. (በመሳለቅም) «ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት ቅጣታችንን አጣድፍልን» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱذْكُرْ عَبْدَنَا دَاوُۥدَ ذَا ٱلْأَيْدِ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ
Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉት ነገር ላይ ታገስ:: የሃኃይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳው:: እርሱ በጣም መላሳ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا سَخَّرْنَا ٱلْجِبَالَ مَعَهُۥ يُسَبِّحْنَ بِٱلْعَشِىِّ وَٱلْإِشْرَاقِ
Amharic Translation - Africa Academy18. እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋዱም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን እንዲታዘዙት አገራንለት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلطَّيْرَ مَحْشُورَةً كُلٌّ لَّهُۥٓ أَوَّابٌ
Amharic Translation - Africa Academy19. በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው አገራንለት:: ሁሉም ለእርሱ ማወደስ የሚመላለስ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَشَدَدْنَا مُلْكَهُۥ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْحِكْمَةَ وَفَصْلَ ٱلْخِطَابِ
Amharic Translation - Africa Academy20. ንግስናውንም አበረታንለት ጥበብንና ንግግርን መለየትንም ሰጠነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهَلْ أَتَىٰكَ نَبَؤُا۟ ٱلْخَصْمِ إِذْ تَسَوَّرُوا۟ ٱلْمِحْرَابَ
Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከራካሪዎቹ ወሬ መጥቶልሃልን? እልፍኙን (ምኩራቡን) በተንጠላጠሉ ጊዜ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ دَخَلُوا۟ عَلَىٰ دَاوُۥدَ فَفَزِعَ مِنْهُمْ قَالُوا۟ لَا تَخَفْ خَصْمَانِ بَغَىٰ بَعْضُنَا عَلَىٰ بَعْضٍ فَٱحْكُم بَيْنَنَا بِٱلْحَقِّ وَلَا تُشْطِطْ وَٱهْدِنَآ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلصِّرَٰطِ
Amharic Translation - Africa Academy22. በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም ሁኔታ በደነገጠ ጊዜ (እንዲህ) አሉት: «አትፍራ። እኛ ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን። በመካከላችንም በእውነት ፍረድ። አታዳላም። ወደ ትክክለኛው መንገድም ምራን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰذَآ أَخِى لَهُۥ تِسْعٌ وَتِسْعُونَ نَعْجَةً وَلِىَ نَعْجَةٌ وَٰحِدَةٌ فَقَالَ أَكْفِلْنِيهَا وَعَزَّنِى فِى ٱلْخِطَابِ
Amharic Translation - Africa Academy23. «ይህ ወንድሜ ነው:: ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴት በጎች አሉት ለእኔም አንዲት ሴት በግ አለችኝ ‹እርሷንም ለእኔ አድርጋት› አለኝ:: በንግግርም አሸነፈኝ።» አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ لَقَدْ ظَلَمَكَ بِسُؤَالِ نَعْجَتِكَ إِلَىٰ نِعَاجِهِۦ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلْخُلَطَآءِ لَيَبْغِى بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَقَلِيلٌ مَّا هُمْ وَظَنَّ دَاوُۥدُ أَنَّمَا فَتَنَّٰهُ فَٱسْتَغْفَرَ رَبَّهُۥ وَخَرَّ رَاكِعًا وَأَنَابَ
Amharic Translation - Africa Academy24. «ሴት በግህን ወደ በጎቹ ለመቀላቀል በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ። ከተጋሪዎች ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ:: እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት ብቻ ሲቀሩ፤ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው።» አለ:: ዳውድም የፈተንነው መሆኑን ወዲያዉኑ አወቀ:: ከጌታዉም ምህረትን ለመነና ሰጋጅ ሆኖም ወደቀ። በመጸጸትም ተመለሰ:: {1}
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَغَفَرْنَا لَهُۥ ذَٰلِكَ وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلْفَىٰ وَحُسْنَ مَـَٔابٍ
Amharic Translation - Africa Academy25. ያንንም ማርነው። ለእርሱም እኛ ዘንድ የመቅረብ ክብር መልካም መመለሻም አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰدَاوُۥدُ إِنَّا جَعَلْنَٰكَ خَلِيفَةً فِى ٱلْأَرْضِ فَٱحْكُم بَيْنَ ٱلنَّاسِ بِٱلْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعِ ٱلْهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَضِلُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌۢ بِمَا نَسُوا۟ يَوْمَ ٱلْحِسَابِ
Amharic Translation - Africa Academy26. (እኛም አልነው) «ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሀልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ:: የግል ዝንባሌህንም አትከተል:: ከአላህ መንገድ ያሳስተሃልና።» እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ ሁሉ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا خَلَقْنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَٰطِلًا ذَٰلِكَ ظَنُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنَ ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy27. ሰማይን ምድርና በመካከላቸዉም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም:: ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው:: ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ሁሉ ከእሳት ወዮላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ نَجْعَلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ كَٱلْمُفْسِدِينَ فِى ٱلْأَرْضِ أَمْ نَجْعَلُ ٱلْمُتَّقِينَ كَٱلْفُجَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy28. በእውነቱ እነዚያ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልክ በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለንን? ወይስ አላህን ፈሪዎችን ልክ እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كِتَٰبٌ أَنزَلْنَٰهُ إِلَيْكَ مُبَٰرَكٌ لِّيَدَّبَّرُوٓا۟ ءَايَٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy29. ይህ መጽሀፍ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሀፍ ነው:: አናቅጽን እንዲያስተነትኑና የአእምሮ ባላቤቶችም እንዲገሰጹበት አወረድነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَهَبْنَا لِدَاوُۥدَ سُلَيْمَٰنَ نِعْمَ ٱلْعَبْدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ
Amharic Translation - Africa Academy30. ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው:: ሱለይማን ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱ ወደ ጌታው መላሳ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ عُرِضَ عَلَيْهِ بِٱلْعَشِىِّ ٱلصَّٰفِنَٰتُ ٱلْجِيَادُ
Amharic Translation - Africa Academy31. በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሶስት እግሮችና በአራተኛው እግር ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌ ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقَالَ إِنِّىٓ أَحْبَبْتُ حُبَّ ٱلْخَيْرِ عَن ذِكْرِ رَبِّى حَتَّىٰ تَوَارَتْ بِٱلْحِجَابِ
Amharic Translation - Africa Academy32. (እንዲህም) አለ: «ጸሀይ በግርዶ እስከተደበቀች ድረስ ጌታየን ከማስታወስ ፈንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رُدُّوهَا عَلَىَّ فَطَفِقَ مَسْحًۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلْأَعْنَاقِ
Amharic Translation - Africa Academy33. «በሉ ፈረሶችን ወደ እኔ መልሷቸው።» (አለ)። ከዚያም እግሮቻቸዉንና አንገቶቻቸዉን መቁረጥ ያዘ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ فَتَنَّا سُلَيْمَٰنَ وَأَلْقَيْنَا عَلَىٰ كُرْسِيِّهِۦ جَسَدًا ثُمَّ أَنَابَ
Amharic Translation - Africa Academy34. ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው። በመንበሩም ላይ የሆነ አካልን ጣልን:: ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ ٱغْفِرْ لِى وَهَبْ لِى مُلْكًا لَّا يَنۢبَغِى لِأَحَدٍ مِّنۢ بَعْدِىٓ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْوَهَّابُ
Amharic Translation - Africa Academy35. «ጌታዬ ሆይ! ማረኝ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባን ንግስናንም ስጠኝ:: ለጋሹ አንተ ብቻ ነህና» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَسَخَّرْنَا لَهُ ٱلرِّيحَ تَجْرِى بِأَمْرِهِۦ رُخَآءً حَيْثُ أَصَابَ
Amharic Translation - Africa Academy36. ንፋስንም በትዕዛዙ ወደ ፈለገበት ስፍራ ልዝብ ሆና የምትነፍስ ስትሆን ገራንለት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلشَّيَٰطِينَ كُلَّ بَنَّآءٍ وَغَوَّاصٍ
Amharic Translation - Africa Academy37. ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰማጮችን ሁሉ ገራንለት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَءَاخَرِينَ مُقَرَّنِينَ فِى ٱلْأَصْفَادِ
Amharic Translation - Africa Academy38. ሌሎችንም በሰንሰለቶች ተቆራኞችን ገራንለት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا عَطَآؤُنَا فَٱمْنُنْ أَوْ أَمْسِكْ بِغَيْرِ حِسَابٍ
Amharic Translation - Africa Academy39. ይህ ስጦታችን ነው ያለ ግምት ለግስ:: ወይም ጨብጥ (አልነው)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلْفَىٰ وَحُسْنَ مَـَٔابٍ
Amharic Translation - Africa Academy40. ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ መልካም መመለሻም በእርግጥ አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرْ عَبْدَنَآ أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَسَّنِىَ ٱلشَّيْطَٰنُ بِنُصْبٍ وَعَذَابٍ
Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባሪያችን አዩብንም: «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ።የሆነውን አስታውስ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱرْكُضْ بِرِجْلِكَ هَٰذَا مُغْتَسَلٌۢ بَارِدٌ وَشَرَابٌ
Amharic Translation - Africa Academy42. በእግርህ ምድርን ምታ:: ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው (ተባለ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَهَبْنَا لَهُۥٓ أَهْلَهُۥ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنَّا وَذِكْرَىٰ لِأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy43. ለእርሱ ከእኛ ዘንድ በሆነ ችሮታ ባለ አእምሮዎችንም ለመገሰጽ ቤተሰቦቹንም ከእነርሱ ጋር መሰላቸውን ሰጠነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَخُذْ بِيَدِكَ ضِغْثًا فَٱضْرِب بِّهِۦ وَلَا تَحْنَثْ إِنَّا وَجَدْنَٰهُ صَابِرًا نِّعْمَ ٱلْعَبْدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ
Amharic Translation - Africa Academy44. «በእጅህ ጭብጥ አርጩሜን ያዝ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ። ማላህንም አታፍርስ።» (አልነው) እነሆ ታጋሽ ሆኖ አገኘነው:: ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱም በጣም መላሳ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرْ عِبَٰدَنَآ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ أُو۟لِى ٱلْأَيْدِى وَٱلْأَبْصَٰرِ
Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዚያን የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የሆኑትን ባሮቻችንም ኢብራሂምን ኢስሐቅንና ያዕቆብንም ለህዝቦችህ አውሳላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَخْلَصْنَٰهُم بِخَالِصَةٍ ذِكْرَى ٱلدَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy46. እኛ ጥሩ በሆነች ጠባይ መረጥናቸው፤ እርሷም የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّهُمْ عِندَنَا لَمِنَ ٱلْمُصْطَفَيْنَ ٱلْأَخْيَارِ
Amharic Translation - Africa Academy47. እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرْ إِسْمَٰعِيلَ وَٱلْيَسَعَ وَذَا ٱلْكِفْلِ وَكُلٌّ مِّنَ ٱلْأَخْيَارِ
Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢስማኢልንም፤ ኢልያስንም፤ ዙልኪፍልንም አውሳ፤ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا ذِكْرٌ وَإِنَّ لِلْمُتَّقِينَ لَحُسْنَ مَـَٔابٍ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ መልካም ዝና ነው:: አላህን ለሚፈሩም በእርግጥ ውብ የሆነ መመለሻ አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
جَنَّٰتِ عَدْنٍ مُّفَتَّحَةً لَّهُمُ ٱلْأَبْوَٰبُ
Amharic Translation - Africa Academy50. በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲሆኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مُتَّكِـِٔينَ فِيهَا يَدْعُونَ فِيهَا بِفَٰكِهَةٍ كَثِيرَةٍ وَشَرَابٍ
Amharic Translation - Africa Academy51. በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ሆነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعِندَهُمْ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرْفِ أَتْرَابٌ
Amharic Translation - Africa Academy52. እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን በባሎቻቸው ላይ አሳጣሪዎች እኩያዎች ሴቶች አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوْمِ ٱلْحِسَابِ
Amharic Translation - Africa Academy53. ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተስፋ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰذَا لَرِزْقُنَا مَا لَهُۥ مِن نَّفَادٍ
Amharic Translation - Africa Academy54. ይህ ሲሳያችን ነው:: ለእርሱ ምንም ማለቅ የለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا وَإِنَّ لِلطَّٰغِينَ لَشَرَّ مَـَٔابٍ
Amharic Translation - Africa Academy55. ይህ (ለትክክለኛ አማኞች ሲሆን።) ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
جَهَنَّمَ يَصْلَوْنَهَا فَبِئْسَ ٱلْمِهَادُ
Amharic Translation - Africa Academy56. የሚገቧት ስትሆን ገሀነም አለቻቸው:: ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا فَلْيَذُوقُوهُ حَمِيمٌ وَغَسَّاقٌ
Amharic Translation - Africa Academy57. ይህ ለከሓዲያን ነው:: ይቅመሱትም የፈላ ውሃና እዥ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَءَاخَرُ مِن شَكْلِهِۦٓ أَزْوَٰجٌ
Amharic Translation - Africa Academy58. ሌላም እነርሱን ከመሰሉ ብዙ አይነቶች አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا فَوْجٌ مُّقْتَحِمٌ مَّعَكُمْ لَا مَرْحَبًۢا بِهِمْ إِنَّهُمْ صَالُوا۟ ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy59. ይህ ከናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ቡድን ነው (ይባላሉ):: ለእነርሱ አይስፋቸዉም:: እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ بَلْ أَنتُمْ لَا مَرْحَبًۢا بِكُمْ أَنتُمْ قَدَّمْتُمُوهُ لَنَا فَبِئْسَ ٱلْقَرَارُ
Amharic Translation - Africa Academy60. ተከታዮቹም ይላሉ፡- «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ። እናንተ ክህደቱን ለእኛ አቀረባችሁት መርጊያይቱም ገሀነም ከፋች።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ رَبَّنَا مَن قَدَّمَ لَنَا هَٰذَا فَزِدْهُ عَذَابًا ضِعْفًا فِى ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy61. «ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ ድርብ ቅጣትን ጨምርለት» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالًا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ ٱلْأَشْرَارِ
Amharic Translation - Africa Academy62. ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች እዚህ አናይምሳ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَتَّخَذْنَٰهُمْ سِخْرِيًّا أَمْ زَاغَتْ عَنْهُمُ ٱلْأَبْصَٰرُ
Amharic Translation - Africa Academy63. «(ሳይገባቸው) መቀለጃ አድርገን ይዘናቸው ነውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነርሱ ዋለሉ?»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ذَٰلِكَ لَحَقٌّ تَخَاصُمُ أَهْلِ ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy64. ይህ በእርግጥ እውነት ነው:: እርሱም የእሳት ሰዎች የእርስ በርስ የመካሰስ ወሬ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ مُنذِرٌ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّارُ
Amharic Translation - Africa Academy65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ። ኃያልና አንድ ከሆነ አላህ በስተቀር ምንም አምላክ የለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفَّٰرُ
Amharic Translation - Africa Academy66. «የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊና መሐሪ ነው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ هُوَ نَبَؤٌا۟ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَنتُمْ عَنْهُ مُعْرِضُونَ
Amharic Translation - Africa Academy68. «እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا كَانَ لِىَ مِنْ عِلْمٍۭ بِٱلْمَلَإِ ٱلْأَعْلَىٰٓ إِذْ يَخْتَصِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛዋ ሰራዊት ለእኔ ምንም እውቀት አልነበረኝም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن يُوحَىٰٓ إِلَىَّ إِلَّآ أَنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy70. «ወደ እኔም አስፈራሪ ገላጭ በመሆኔ እንጂ በሌላ አይወርድልኝም።» በል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّى خَٰلِقٌۢ بَشَرًا مِّن طِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታህ ለመላዕክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ (የነበረዉን አስታውስ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا سَوَّيْتُهُۥ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِى فَقَعُوا۟ لَهُۥ سَٰجِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy72. «ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ሁላችሁም ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።» (አልኩ።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَسَجَدَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ كُلُّهُمْ أَجْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy73. መላው መላዕክትም በአንድነት ሰገዱ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّآ إِبْلِيسَ ٱسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy74. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ
Amharic Translation - Africa Academy75. አላህ «ዲያብሎስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ለአደም ከመስገድ ምን ከለከለህ? ኮርተህ ነው? ወይስ ፊቱኑ ከትዕቢተኞች ነበርክ?» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَنَا۠ خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِى مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُۥ مِن طِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy76. ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የተሻልኩ ነኝ። እኔን ከእሳት የፈጠርከኝ ስትሆን እሱን ግን ከጭቃ ነው የፈጠርከው።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَٱخْرُجْ مِنْهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy77. (አላህም) አለ፡- «ከእርሷ ውጣ። አንተ የተባረርክ ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ عَلَيْكَ لَعْنَتِىٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy78. «እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይሁን።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ فَأَنظِرْنِىٓ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
Amharic Translation - Africa Academy79. (ዲያብሎስም) «ጌታየ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ እባክህ አቆየኝ።» አለ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلْمُنظَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy80. (አላህም) አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْوَقْتِ ٱلْمَعْلُومِ
Amharic Translation - Africa Academy81. «እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy82. (እርሱም) አለ: «በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ሁላቸዉንም አሳስታቸዋለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ ٱلْمُخْلَصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy83. «ከእነርሱ መካከል ምርጥ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَٱلْحَقُّ وَٱلْحَقَّ أَقُولُ
Amharic Translation - Africa Academy84. (አላህም) አለ: «እውነቱም ከእኔ ነው:: እውነትንም እላለሁ(እናገራለሁ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكَ وَمِمَّن تَبِعَكَ مِنْهُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy85. «በአንተና ከእነርሱ መካከል በተከተሉህም ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ مَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلْمُتَكَلِّفِينَ
Amharic Translation - Africa Academy86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አል ጠይቃችሁም:: እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy87. «እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُۥ بَعْدَ حِينٍۭ
Amharic Translation - Africa Academy88. «የትንቢቱን እውነትነት ከጊዜ በኋላም ቢሆን በእርግጥ ታውቁታላችሁ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→