caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yaseen يس

83 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 41

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يسٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ያሲን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْقُرْءَانِ ٱلْحَكِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy2-ጥበብ በተሞላበት ቁርኣን እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy4. አንተ በእርግጥ በቀጥታው መንገድ ላይ ነህ ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَنزِيلَ ٱلْعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy5.ቁርኣን አሸናፊውና አዛኙ ከሆነው አምላክ ከአላህ ተወረደ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِتُنذِرَ قَوْمًا مَّآ أُنذِرَ ءَابَآؤُهُمْ فَهُمْ غَٰفِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ህዝቦች ልታስጠነቅቅበት ቁርኣን ተወረደ። እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ حَقَّ ٱلْقَوْلُ عَلَىٰٓ أَكْثَرِهِمْ فَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7. በአብዛኞቻቸቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا جَعَلْنَا فِىٓ أَعْنَٰقِهِمْ أَغْلَٰلًا فَهِىَ إِلَى ٱلْأَذْقَانِ فَهُم مُّقْمَحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን። (እንዛዝላይቱም) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት። እናም ከዚያም እነርሱ ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلْنَا مِنۢ بَيْنِ أَيْدِيهِمْ سَدًّا وَمِنْ خَلْفِهِمْ سَدًّا فَأَغْشَيْنَٰهُمْ فَهُمْ لَا يُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9. ከበስተፊታቸዉም ግርዶን ከበስተኋላቸዉም ግርዶን አደረግንና ሸፈንናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያዩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسَوَآءٌ عَلَيْهِمْ ءَأَنذَرْتَهُمْ أَمْ لَمْ تُنذِرْهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا تُنذِرُ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلذِّكْرَ وَخَشِىَ ٱلرَّحْمَٰنَ بِٱلْغَيْبِ فَبَشِّرْهُ بِمَغْفِرَةٍ وَأَجْرٍ كَرِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አር-ረህማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው:: እናም በምህረትና በመልካም ምንዳ አብስረው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا نَحْنُ نُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا۟ وَءَاثَٰرَهُمْ وَكُلَّ شَىْءٍ أَحْصَيْنَٰهُ فِىٓ إِمَامٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy12. እኛ ሙታንን በእርግጥ ህያው እናደርጋለን:: ያስቀደሙትንም ስራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን:: ሁሉን ነገርም ገላጭና መሪ በሆነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلًا أَصْحَٰبَ ٱلْقَرْيَةِ إِذْ جَآءَهَا ٱلْمُرْسَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልዕክተኞች በመጧት ጊዜ የሆነውን ግለጽላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ أَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمُ ٱثْنَيْنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزْنَا بِثَالِثٍ فَقَالُوٓا۟ إِنَّآ إِلَيْكُم مُّرْسَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸውም ጊዜ፤ በሶስተኛም ባበረታናቸውና «እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን» ባሏቸው ጊዜ የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ مَآ أَنتُمْ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُنَا وَمَآ أَنزَلَ ٱلرَّحْمَٰنُ مِن شَىْءٍ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا تَكْذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. «እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም:: አር-ረህማንም ምንንም ነገር አላወረደም:: እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም» አሏቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ رَبُّنَا يَعْلَمُ إِنَّآ إِلَيْكُمْ لَمُرْسَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy16. መልዕክተኞቹም አሉ: «ጌታችን ያውቃል። እኛ ወደ እናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا عَلَيْنَآ إِلَّا ٱلْبَلَٰغُ ٱلْمُبِينُ

Amharic Translation - Africa Academy17. «በእኛ ላይም ግልጽ የሆነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ إِنَّا تَطَيَّرْنَا بِكُمْ لَئِن لَّمْ تَنتَهُوا۟ لَنَرْجُمَنَّكُمْ وَلَيَمَسَّنَّكُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy18. ህዝቦቹም «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ሆንን። ከዚህ ጥሪያችሁ ባትከለክሉም በእርግጥ እንወግራችኋለን:: ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ طَٰٓئِرُكُم مَّعَكُمْ أَئِن ذُكِّرْتُم بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. «ገደ ቢስነታችሁ ከናንተው ጋር ነው:: ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊ ህዝቦች ናችሁ» አሏቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَآءَ مِنْ أَقْصَا ٱلْمَدِينَةِ رَجُلٌ يَسْعَىٰ قَالَ يَٰقَوْمِ ٱتَّبِعُوا۟ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy20. ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣና (እንዲህ) አለ: «ወገኖቼ ሆይ! መልዕክተኞቹን ተከተሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱتَّبِعُوا۟ مَن لَّا يَسْـَٔلُكُمْ أَجْرًا وَهُم مُّهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. «እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲሆኑ ክፍያን የማይጠይቋችሁን ሰዎች ተከተሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا لِىَ لَآ أَعْبُدُ ٱلَّذِى فَطَرَنِى وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22. «ያንንም የፈጠረኝንና ወደ እርሱም የምትመለሱበትን ጌታ የማልገዛበት ምን ምክንያት አለኝ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً إِن يُرِدْنِ ٱلرَّحْمَٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّى شَفَٰعَتُهُمْ شَيْـًٔا وَلَا يُنقِذُونِ

Amharic Translation - Africa Academy23. «ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልራህማን ሊጎዳኝ ቢፈልግ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም አያድኑኝምም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّىٓ إِذًا لَّفِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy24. «እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّىٓ ءَامَنتُ بِرَبِّكُمْ فَٱسْمَعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy25. «እኔ በጌታችሁ አመንኩ። ስሙኝም።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قِيلَ ٱدْخُلِ ٱلْجَنَّةَ قَالَ يَٰلَيْتَ قَوْمِى يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. {1} «ገነትን ግባ» ተባለም። እርሱም አለ: «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِمَا غَفَرَ لِى رَبِّى وَجَعَلَنِى مِنَ ٱلْمُكْرَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy27. «ጌታዬ ለእኔ ምህረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መሆኑን።» (ቢያውቁ ተመኘሁ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَنزَلْنَا عَلَىٰ قَوْمِهِۦ مِنۢ بَعْدِهِۦ مِن جُندٍ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا كُنَّا مُنزِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy28. ከእርሱም በኋላ በህዝቦቹ ላይ ልናጠፋቸው ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም (በማንም) ላይ አውራጆችም አልነበርንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن كَانَتْ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً فَإِذَا هُمْ خَٰمِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy29. ቅጣታቸው አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም:: ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ሆኑ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰحَسْرَةً عَلَى ٱلْعِبَادِ مَا يَأْتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy30. በባሮች ላይ ዋ ቁጭት! ከመልዕክተኛ አንድም አልመጣላቸዉም በእርሱ ያፌዙበት ቢሆን እንጂ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَرَوْا۟ كَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّنَ ٱلْقُرُونِ أَنَّهُمْ إِلَيْهِمْ لَا يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy31. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንንና እነርሱ የማይመለሱ መሆናቸውን አላወቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن كُلٌّ لَّمَّا جَمِيعٌ لَّدَيْنَا مُحْضَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. ሁሉም እኛ ዘንድ (የሚሰበሰቡ) የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَايَةٌ لَّهُمُ ٱلْأَرْضُ ٱلْمَيْتَةُ أَحْيَيْنَٰهَا وَأَخْرَجْنَا مِنْهَا حَبًّا فَمِنْهُ يَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. የሞተችዉም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት:: ህያው አደረግናት:: ከእርሷ ፍሬን አወጣን፤ ከእሱም ይበላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلْنَا فِيهَا جَنَّٰتٍ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعْنَٰبٍ وَفَجَّرْنَا فِيهَا مِنَ ٱلْعُيُونِ

Amharic Translation - Africa Academy34. በእርሷ ውስጥ ከዘምባባዎችና ከወይኖች የሆነ አትክልቶችን አደረግን:: በእርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيَأْكُلُوا۟ مِن ثَمَرِهِۦ وَمَا عَمِلَتْهُ أَيْدِيهِمْ أَفَلَا يَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. ከፍሬዉና እጆቻቸው ከሰሩትም ይበሉ ዘንድ ይህን አደረግን:: አያመሰግኑምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سُبْحَٰنَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَزْوَٰجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. ያ! ምድር ከምታበቅለው፤ ወንዴንና ሴቴን ከነፍሶቻቸዉም ከማያውቁትም ነገር (ዓይነቶችን) ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَايَةٌ لَّهُمُ ٱلَّيْلُ نَسْلَخُ مِنْهُ ٱلنَّهَارَ فَإِذَا هُم مُّظْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy37. ሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው:: ከእርሱ ላይ ቀንን አንገፋለን:: ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلشَّمْسُ تَجْرِى لِمُسْتَقَرٍّ لَّهَا ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ ٱلْعَزِيزِ ٱلْعَلِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy38. ጸሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው አምላክ የአላህ ውሳኔ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْقَمَرَ قَدَّرْنَٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلْعُرْجُونِ ٱلْقَدِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy39. ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ አሮጌ ዘንባባ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ መሄዱን ለካነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا ٱلشَّمْسُ يَنۢبَغِى لَهَآ أَن تُدْرِكَ ٱلْقَمَرَ وَلَا ٱلَّيْلُ سَابِقُ ٱلنَّهَارِ وَكُلٌّ فِى فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy40. ጸሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም:: ሌሊትም ቀንን ያለ ጊዜው ቀዳሚ አይሆንም:: ሁሉም በየመዞሪያቸው (በፈለክ) ውስጥ ይዋኛሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَايَةٌ لَّهُمْ أَنَّا حَمَلْنَا ذُرِّيَّتَهُمْ فِى ٱلْفُلْكِ ٱلْمَشْحُونِ

Amharic Translation - Africa Academy41. እኛም የቀድሞ ትውልዳቸውን (አባቶቻቸውን) በተሞላች መርከብ ውስጥ የጫን መሆናችን ለእነርሱ ምልክት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَخَلَقْنَا لَهُم مِّن مِّثْلِهِۦ مَا يَرْكَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy42. ከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن نَّشَأْ نُغْرِقْهُمْ فَلَا صَرِيخَ لَهُمْ وَلَا هُمْ يُنقَذُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. ስንፈልግ እናሰምጣቸዋለን:: ለእነርሱም ነፃ የሚያደርጋቸው ረዳት የላቸዉም:: እንዲድኑ የሚደረጉም አይደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا رَحْمَةً مِّنَّا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy44. እኛ ግን በችሮታችንና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም አዳንናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّقُوا۟ مَا بَيْنَ أَيْدِيكُمْ وَمَا خَلْفَكُمْ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy45. ለእነርሱም «በስተፊታችሁና በኋላችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁ፤ ይታዘንላችኋልና» በተባለ ጊዜ ፊታቸውን ያዞራሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا تَأْتِيهِم مِّنْ ءَايَةٍ مِّنْ ءَايَٰتِ رَبِّهِمْ إِلَّا كَانُوا۟ عَنْهَا مُعْرِضِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. ከጌታቸውም ተዓምራት አንዲትም ተዓምር አትመጣላቸዉም ከእርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጅ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ أَنفِقُوا۟ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنُطْعِمُ مَن لَّوْ يَشَآءُ ٱللَّهُ أَطْعَمَهُۥٓ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy47. ለእነርሱም «አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ» በተባሉ ጊዜ እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነዚያ በአላህ ላመኑት «አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን እናበላለን? እናንተ በግልጽ ስህተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy48. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا يَنظُرُونَ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً تَأْخُذُهُمْ وَهُمْ يَخِصِّمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. እነርሱ የሚከራከሩ ሲሆኑ በድንገት የምትይዛቸው የሆነችን አንዲትን ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا يَسْتَطِيعُونَ تَوْصِيَةً وَلَآ إِلَىٰٓ أَهْلِهِمْ يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50. ያን ጊዜ መናዘዝን እንኳን አይችሉም:: ወደ ቤተሰቦቻቸዉም አይመለሱም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنُفِخَ فِى ٱلصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ ٱلْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy51. በቀንዱም ይነፋል:: ወዲያውኑም እነርሱ ከየመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰوَيْلَنَا مَنۢ بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا هَٰذَا مَا وَعَدَ ٱلرَّحْمَٰنُ وَصَدَقَ ٱلْمُرْسَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy52. «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልዕክተኞቹም እውነቱን የነገሩን ነው።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن كَانَتْ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً فَإِذَا هُمْ جَمِيعٌ لَّدَيْنَا مُحْضَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. እርሷ አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አይደለችም:: ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلْيَوْمَ لَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْـًٔا وَلَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy54. ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም (ይባላሉ።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ أَصْحَٰبَ ٱلْجَنَّةِ ٱلْيَوْمَ فِى شُغُلٍ فَٰكِهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy55. የገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በስራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُمْ وَأَزْوَٰجُهُمْ فِى ظِلَٰلٍ عَلَى ٱلْأَرَآئِكِ مُتَّكِـُٔونَ

Amharic Translation - Africa Academy56. እነርሱም ሆኑ ሚስቶቻቸው በጥላዎች ውስጥ ናቸው:: ባለ አጎበር አልጋዎች ላይም ተደጋፊዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَهُمْ فِيهَا فَٰكِهَةٌ وَلَهُم مَّا يَدَّعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. በውስጧ ለእነርሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው:: ለእነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَلَٰمٌ قَوْلًا مِّن رَّبٍّ رَّحِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy58. ለእነርሱም አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አለላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱمْتَٰزُوا۟ ٱلْيَوْمَ أَيُّهَا ٱلْمُجْرِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59. (አላህም ይላል): «እናንተ አመጸኞች ሆይ! ዛሬ ከትክክለኛ አማኞች ተለዩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا۟ ٱلشَّيْطَٰنَ إِنَّهُۥ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy60. «የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنِ ٱعْبُدُونِى هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy61. «ተገዙኝም ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው በማለትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَضَلَّ مِنكُمْ جِبِلًّا كَثِيرًا أَفَلَمْ تَكُونُوا۟ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy62. «ከናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል:: የምታውቁም አልነበራችሁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy63. «ይህቺ ያቺ ትቀጠሯት የነበረችው ገሀነም ናት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱصْلَوْهَا ٱلْيَوْمَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy64. «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬዉኑ ግቧት።» (ይባላሉ።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰٓ أَفْوَٰهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَآ أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል:: እግሮቻቸዉም ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ نَشَآءُ لَطَمَسْنَا عَلَىٰٓ أَعْيُنِهِمْ فَٱسْتَبَقُوا۟ ٱلصِّرَٰطَ فَأَنَّىٰ يُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy66. ብንፈልግ ኖሮ በዓይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር:: መንገድንም እንደ ልማዳቸው በተሸቀዳደሙ ነበር:: እንዴትስ ያያሉ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ نَشَآءُ لَمَسَخْنَٰهُمْ عَلَىٰ مَكَانَتِهِمْ فَمَا ٱسْتَطَٰعُوا۟ مُضِيًّا وَلَا يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. ብንፈልግ ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጥናቸው ነበር:: ከዚያም መሄድንም ሆነ መመለስን ባልቻሉም ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن نُّعَمِّرْهُ نُنَكِّسْهُ فِى ٱلْخَلْقِ أَفَلَا يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy68. እድሜውንም የምናረዝመውን በፍጥረቱ ወደ ደካማነት እንመልሰዋለን:: አያውቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا عَلَّمْنَٰهُ ٱلشِّعْرَ وَمَا يَنۢبَغِى لَهُۥٓ إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ وَقُرْءَانٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy69. (ሙሐመድን) ቅኔንም አላስተማርነዉም:: ለእርሱም አይገባዉም:: እርሱ (መጽሐፉ) መገሰጫና ገላጭ ቁርኣን አንጅ (ቅኔ አይደለም)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّيُنذِرَ مَن كَانَ حَيًّا وَيَحِقَّ ٱلْقَوْلُ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy70. ግሳጼነቱም ልቡ ህያው የሆነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሓዲያን ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَآ أَنْعَٰمًا فَهُمْ لَهَا مَٰلِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. እኛ እጆቻችን ከሰሩት ለእነርሱ እንሰሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَذَلَّلْنَٰهَا لَهُمْ فَمِنْهَا رَكُوبُهُمْ وَمِنْهَا يَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. ለእነርሱም ገራናት:: ስለዚህ ከእርሷ ውስጥ የሚጋልቡት አለ:: ከእርሷም ይመገባሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُمْ فِيهَا مَنَٰفِعُ وَمَشَارِبُ أَفَلَا يَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy73. ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ሌሎች ጥቅሞችና መጠጦችም አሏቸው። ታዲያ አያመሰግኑምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةً لَّعَلَّهُمْ يُنصَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy74. መረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አመለኩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَهُمْ وَهُمْ لَهُمْ جُندٌ مُّحْضَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy75. ሊረዷቸውም አይችሉም። እነርሱም ለእርሳቸው ወደ እሳት የተቀረቡ ሰራዊት ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا يَحْزُنكَ قَوْلُهُمْ إِنَّا نَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy76. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: እኛ የሚደብቁትንም የሚገልፁትንም እናውቃለንና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَرَ ٱلْإِنسَٰنُ أَنَّا خَلَقْنَٰهُ مِن نُّطْفَةٍ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy77. ሰው እኛ ከፍትወት ጠብታ የፈጠርነው መሆናችንን አላወቀምን? ወዲያዉም እርሱ ትንሳኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِىَ خَلْقَهُۥ قَالَ مَن يُحْىِ ٱلْعِظَٰمَ وَهِىَ رَمِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy78. ለእኛም ምሳሌን አደረገልን:: መፈጠሩንም ረሳ:: «አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲሆኑ ህያው የሚያደርጋቸው ማነው?» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ يُحْيِيهَا ٱلَّذِىٓ أَنشَأَهَآ أَوَّلَ مَرَّةٍ وَهُوَ بِكُلِّ خَلْقٍ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy79. «ያ! በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ጌታ እንደገና ህያው ያደረጋታል:: እርሱም በፍጡሩ ሁሉ ሁኔታ አዋቂ ነው።» በለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلشَّجَرِ ٱلْأَخْضَرِ نَارًا فَإِذَآ أَنتُم مِّنْهُ تُوقِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy80. ያ! ለእናንተ ከእርጥብ ዛፍ እሳትን የፈጠረላችሁ ነው:: ወዲያውኑም እናንተ ከእርሱ ታቀጣጥላላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَيْسَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يَخْلُقَ مِثْلَهُم بَلَىٰ وَهُوَ ٱلْخَلَّٰقُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy81. ያ! ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? እንዴታ ቻይ ነው እንጂ:: እርሱም በብዙ ፈጣሪውና እጅግ አዋቂው ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَآ أَمْرُهُۥٓ إِذَآ أَرَادَ شَيْـًٔا أَن يَقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

Amharic Translation - Africa Academy82. ነገሩ አንድን ነገር በሻ ጊዜ ሁን ማለት ብቻ ነው:: ከዚያ ወዲያው ይሆናልም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسُبْحَٰنَ ٱلَّذِى بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَىْءٍ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy83. እናም ያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው:: ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70