ሱረቱ An-Najm النجم
62 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 23
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلنَّجْمِ إِذَا هَوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy1. በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمْ وَمَا غَوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy2. (እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ)፤ ባልደረባችሁ ሙሐመድ ከሐቅ አልተሳሳተም። አላፈነገጠም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلْهَوَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy3. ከልብ ወለድ ስሜቱም አይናገርም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْىٌ يُوحَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy4. እርሱ (ንግግሩ) ከአላህ የተወረደ እንጂ ሌላ አይደለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلْقُوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy5. ሀይለ ብርቱ የሆነው አስተማረው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذُو مِرَّةٍ فَٱسْتَوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy6. የእውቀት ባለቤት የሆነው:: ከዚያም ላይ ሆኖ ተመቻቸ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهُوَ بِٱلْأُفُقِ ٱلْأَعْلَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy7. በላይኛው አድማስ ላይ ሆኖ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy8. ከዚያም (ነቢዩን) ቀረበው፤ በጣም ተጠጋውም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَانَ قَابَ قَوْسَيْنِ أَوْ أَدْنَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy9. ከዚያም የሁለት ደጋን ጫፎች ያህል ወይም ከዚያም ባነሰ ርቀት ላይ ሆነም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَوْحَىٰٓ إِلَىٰ عَبْدِهِۦ مَآ أَوْحَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy10. እናም (አላህ) ለአገልጋዩ (ለሙሐመድ) ማውረድ የሻውን አወረደ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا كَذَبَ ٱلْفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy11. ያየውን ነገር ሁሉ ልቦናው አላስተባበለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy12. ታዲያ (ከሓዲያን ሆይ!) በሚያየው ጉዳይ ላይ ትከራከሩታላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ رَءَاهُ نَزْلَةً أُخْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy13. እርግጥ በሌላይቱም መውረድ (ነቢዩ ሙሐመድ መልዐኩ ጂብሪልን) አይቶታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عِندَ سِدْرَةِ ٱلْمُنتَهَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy14. ይኸዉም ሲድረቱ አል-ሙንተሃ (የመጨረሻቱ ቁርቁራ) በተባለው ዓለም ላይ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عِندَهَا جَنَّةُ ٱلْمَأْوَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy15. እርሷ ዘንድ መኖርያ የሆነችው ገነት አለች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ يَغْشَى ٱلسِّدْرَةَ مَا يَغْشَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy16. (ቁርቁራይቱን) ሸፋኝ ነገር በሸፈናት ጊዜ (አየው)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا زَاغَ ٱلْبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy17. አይኑ አልተዘነበለም:: ወሰንም አላለፈም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَقَدْ رَأَىٰ مِنْ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلْكُبْرَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy18. ከጌታው ታላላቅ ተዐምራት በእርግጥ ተመለከተ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَرَءَيْتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلْعُزَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy19. (ቁርይሾች ሆይ!) ላትንና ዑዛን አያችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلْأُخْرَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy20. ስለ ሶስተኛዋ መናትም የምታውቁትን እስቲ ንገሩኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلْأُنثَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy21. ለእናንተ ወንድ ወንድ ለእሱ ግን ሴት ሴት ታደርጋላችሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ إِذًا قِسْمَةٌ ضِيزَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy22. ይህ ተግባር አድሏዊ ክፍፍል ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنْ هِىَ إِلَّآ أَسْمَآءٌ سَمَّيْتُمُوهَآ أَنتُمْ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَٰنٍ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهْوَى ٱلْأَنفُسُ وَلَقَدْ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلْهُدَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy23. እነዚያ ጣዖታት እናንተና አባቶቻችሁ የሰየማችኋቸው ስሞች ብቻ እንጂ ሌላ አይደሉም::አላህ በእርሷ (መገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ጣኡት አምላኪዎች ሁሉ ከጌታቸው የተላከላቸው ቅኑ መመሪያ እያለ የሚከተሉት ግን ጥርጣሬንና ስሜትን ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ لِلْإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy24. የሰው ልጅ የፈለገውን ሁሉ ያገኛልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلِلَّهِ ٱلْـَٔاخِرَةُ وَٱلْأُولَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy25. መጪውን ዓለምም ሆነ የመጀመሪያው ዓለም የአላህ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغْنِى شَفَٰعَتُهُمْ شَيْـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعْدِ أَن يَأْذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرْضَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy26. በሰማያት ውስጥ ካሉ መላዕክት አላህ የሚሻውንና የሚወደውን ለሰው ያማልዱ ዘንድ ከፈቀደላቸው በኋላ እንጂ ምልጃቸው የማይፈይድ አያሌዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ لَيُسَمُّونَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ تَسْمِيَةَ ٱلْأُنثَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy27. እነዚያ በመጪው ዓለም የማያምኑት መላዕክትን በእንስት ስም ይሰይማሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغْنِى مِنَ ٱلْحَقِّ شَيْـًٔا
Amharic Translation - Africa Academy28. ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የላቸውም። እነርሱ የሚከተሉት ጥርጣሬን ብቻ ነው:: ጥርጣሬ ደግሞ ሀቅን አይተካም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَعْرِضْ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكْرِنَا وَلَمْ يُرِدْ إِلَّا ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا
Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አፈንግጦና የዚችን ዓለም ኑሮ እንጂ ሌላ ከማይመኝ ሰው እራስህን አሽሽ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ مَبْلَغُهُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ ٱهْتَدَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy30. ይህ የእውቀታቸው ጣሪያ (መጨረሻ) ነው:: ጌታህ ግን መንገዱን የሳተውን ሁሉ አዋቂ ነው:: የተቀናውንም እንዲሁ አዋቂ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ لِيَجْزِىَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔوا۟ بِمَا عَمِلُوا۟ وَيَجْزِىَ ٱلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ بِٱلْحُسْنَى
Amharic Translation - Africa Academy31. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያን ያጠፉትን በተግባራቸው ለመመንዳትና እነዚያን መልካም የሰሩትንም በመልካሟ (በገነት) ሊመነዳ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلْمَغْفِرَةِ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ وَإِذْ أَنتُمْ أَجِنَّةٌ فِى بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمْ فَلَا تُزَكُّوٓا۟ أَنفُسَكُمْ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy32. እነርሱም ከጥቃቅን ጥፋቶች በቀር ከባባድ ወንጀሎችንና አጸያፊ ተግባሮችን የራቁ ናቸው:: ጌታህ ምህረተ ሰፊ ነው:: እርሱ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜም ሆነ በእናቶቻችሁ ማሕጸን ውስጥ ጽንሶች በሁናችሁበት ጊዜ ያውቃችኋል:: ስለዚህ እራሳችሁን አታሞግሱ:: እርሱ በትክክል የሚፈራውን ሰው ከሁሉም ይበልጥ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَرَءَيْتَ ٱلَّذِى تَوَلَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy33. ያን ከእምነት የሸሸውን አየህን (እስቲ ንገረኝ)?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَعْطَىٰ قَلِيلًا وَأَكْدَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy34. ጥቂትን ብቻ ሰጥቶ ያቋረጠውን፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَعِندَهُۥ عِلْمُ ٱلْغَيْبِ فَهُوَ يَرَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy35, ለመሆኑ የሚያውቀው የሩቅ ሚስጢር አለውና እርሱንም ያያልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِى صُحُفِ مُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy36. ወይስ በሙሳ ፅሁፍ ያለው አልተነገረውም?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِبْرَٰهِيمَ ٱلَّذِى وَفَّىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy37. በኢብራሂም (ትእዛዛቱን) በፈፀመው ያለውስ አልተነገረዉምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy38. ይኸዉም ወንጀለኛ ነፍስ የሌላውን ነፍስ ወንጀል በፍጹም አትሸከምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy39. የሰው ልጅም የለፋበትን ብቻ እንጂ ሌላ የለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّ سَعْيَهُۥ سَوْفَ يُرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy40. የሰራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ يُجْزَىٰهُ ٱلْجَزَآءَ ٱلْأَوْفَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy41. ከዚያም ጌታው ሙሉ ምንዳውን ይመነዳዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلْمُنتَهَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሁሉም መጨረሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَضْحَكَ وَأَبْكَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy43. እርሱ ያ ያሳቀና ያስለቀሰ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَمَاتَ وَأَحْيَا
Amharic Translation - Africa Academy44. እርሱ ያ የገደለና ሕያው ያደረገም ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy45. እርሱ ያ ጥንድን፤ ወንድንና ሴትን የፈጠረ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِن نُّطْفَةٍ إِذَا تُمْنَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy46. ይኸዉም ከፍትወት ጠብታ በማሕጸን ውስጥ በምትፈሰስ ጊዜ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّ عَلَيْهِ ٱلنَّشْأَةَ ٱلْأُخْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy47. ሌላውን ማስገኘትም በእርሱ ላይ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَغْنَىٰ وَأَقْنَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy48. እርሱ ያ ሀብትን የሰጠና ያብቃቃ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ هُوَ رَبُّ ٱلشِّعْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy49. እርሱ የሺዕራ ጌታ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥٓ أَهْلَكَ عَادًا ٱلْأُولَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy50. እርሱ የቀድሞ ሰዎችን የአድ ሕዝቦችንም አጠፋ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَثَمُودَا۟ فَمَآ أَبْقَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy51. ሰሙድንም አጠፋ:: አንድንም አላስቀረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَوْمَ نُوحٍ مِّن قَبْلُ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ هُمْ أَظْلَمَ وَأَطْغَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy52. በፊትም የኑህን ህዝቦች አጥፍቷል:: እነርሱ እጅግ በዳዮችና በጣም አመጸኞች ነበሩና ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy53.የተገለበጡትንም ደፋ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَغَشَّىٰهَا مَا غَشَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy54. ባሸፈናት ሸፈናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy55. (የሰው ልጅ ሆይ)፤ ከጌታህ ጸጋዎች በየትኛው ነው የምትጠራጠረው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا نَذِيرٌ مِّنَ ٱلنُّذُرِ ٱلْأُولَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከቀድሞዎቹ አስጠንቃቂዎች አንዱ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَزِفَتِ ٱلْـَٔازِفَةُ
Amharic Translation - Africa Academy57. ቀራቢቱም ቀረበች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَيْسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ كَاشِفَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy58. ከአላህ በስተቀር ገላጭ የላትም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمِنْ هَٰذَا ٱلْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy59. በዚህ ዘገባ ትደነቃላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy60 ትስቃላችሁን? አታለቅሱምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنتُمْ سَٰمِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy61. እናንተ ዘወትር ዘንጊዎች ናችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱسْجُدُوا۟ لِلَّهِ وَٱعْبُدُوا۟
Amharic Translation - Africa Academy62. ለአላህ ስገዱ በብቸኝነትም አምልኩትም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→