caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Qamar القمر

55 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 37

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱقْتَرَبَتِ ٱلسَّاعَةُ وَٱنشَقَّ ٱلْقَمَرُ

Amharic Translation - Africa Academy1. የትንሳኤ ቀን ተቃረበ:: ጨረቃም ተገመሰ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن يَرَوْا۟ ءَايَةً يُعْرِضُوا۟ وَيَقُولُوا۟ سِحْرٌ مُّسْتَمِرٌّ

Amharic Translation - Africa Academy2. ከሓዲያን ተዐምርን ቢያዩም እንቢ ብለው ይዞራሉ:: «ይህ ዘውታሪ ድግምት ነው» ይላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَّبُوا۟ وَٱتَّبَعُوٓا۟ أَهْوَآءَهُمْ وَكُلُّ أَمْرٍ مُّسْتَقِرٌّ

Amharic Translation - Africa Academy3.አስተባበሉም :: ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ:: ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው) ረጊ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ جَآءَهُم مِّنَ ٱلْأَنۢبَآءِ مَا فِيهِ مُزْدَجَرٌ

Amharic Translation - Africa Academy4. ከዜናዎቹ በእርሱ ውስጥ መገሰጫ የሚሆን ነገር ያለበት በእርግጥ መጣላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حِكْمَةٌۢ بَٰلِغَةٌ فَمَا تُغْنِ ٱلنُّذُرُ

Amharic Translation - Africa Academy5. ሙሉ ከሆነ ጥበብ (መጣላቸው):: ግን አስፈራሪዎች (ለማያምኑት) አይፈይዱም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَوَلَّ عَنْهُمْ يَوْمَ يَدْعُ ٱلدَّاعِ إِلَىٰ شَىْءٍ نُّكُرٍ

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ተውና ዙር። (ይልቁንስ) ጠሪው መልዓክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خُشَّعًا أَبْصَٰرُهُمْ يَخْرُجُونَ مِنَ ٱلْأَجْدَاثِ كَأَنَّهُمْ جَرَادٌ مُّنتَشِرٌ

Amharic Translation - Africa Academy7. ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነውና ፍጹም የተበተኑ አንበጣ መስለው ከየመቃብሮቻቸው ይወጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُّهْطِعِينَ إِلَى ٱلدَّاعِ يَقُولُ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا يَوْمٌ عَسِرٌ

Amharic Translation - Africa Academy8. ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎችና ቸኳዩች ሆነው ይወጣሉ:: ከሓዲያን ያን ጊዜ «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ فَكَذَّبُوا۟ عَبْدَنَا وَقَالُوا۟ مَجْنُونٌ وَٱزْدُجِرَ

Amharic Translation - Africa Academy9. ከእነርሱ በፊት የ(ነብዩ) ኑህ ህዝቦች አስተባበሉ:: ባሪያችንንም ኑህን አስተባበሉ:: «ዕብድ ነዉም» አሉት:: ተገላመጠም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَدَعَا رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَغْلُوبٌ فَٱنتَصِرْ

Amharic Translation - Africa Academy10. «ጌታውንም እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ተጣራ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَفَتَحْنَآ أَبْوَٰبَ ٱلسَّمَآءِ بِمَآءٍ مُّنْهَمِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy11. ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفَجَّرْنَا ٱلْأَرْضَ عُيُونًا فَٱلْتَقَى ٱلْمَآءُ عَلَىٰٓ أَمْرٍ قَدْ قُدِرَ

Amharic Translation - Africa Academy12. የምድርንም ምንጮች በሃይል አፈነዳን:: የሰማዩና የምድሩ ውሃዉም ቀድሞ በተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَحَمَلْنَٰهُ عَلَىٰ ذَاتِ أَلْوَٰحٍ وَدُسُرٍ

Amharic Translation - Africa Academy13. ባለ ብዙ ሳንቃዎችና ባለ ብዙ ሚስማሮች በሆነቸው ታንኳ ላይም ጫንነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَجْرِى بِأَعْيُنِنَا جَزَآءً لِّمَن كَانَ كُفِرَ

Amharic Translation - Africa Academy14. በጥበቃችን ስር ሆና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረ ሰው ምንዳ ይህን ሰራን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَد تَّرَكْنَٰهَآ ءَايَةً فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy15. ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት:: ተገሳጭ አለን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِى وَنُذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy16. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy17. ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገንዛቢ አለን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ عَادٌ فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِى وَنُذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy18. የዓድ ህዝቦች አስተባበሉ:: ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِيحًا صَرْصَرًا فِى يَوْمِ نَحْسٍ مُّسْتَمِرٍّ

Amharic Translation - Africa Academy19. እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በሆነ ቀን በኃይል የምንትሻሻ ነፋስን ላክንባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَنزِعُ ٱلنَّاسَ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ مُّنقَعِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy20. ሰዎችንም ልክ ከስሮቻቸው እንደተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከየተደበቁበት ትነቅላቸዋለች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِى وَنُذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy21. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy22. ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِٱلنُّذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy23. የሰሙድ ህዝቦች በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَالُوٓا۟ أَبَشَرًا مِّنَّا وَٰحِدًا نَّتَّبِعُهُۥٓ إِنَّآ إِذًا لَّفِى ضَلَٰلٍ وَسُعُرٍ

Amharic Translation - Africa Academy24. (እንዲህም) አሉ: «ከእኛ የሆነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያ! ጊዜ በስህተትና በእብደት ውስጥ ነን አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَءُلْقِىَ ٱلذِّكْرُ عَلَيْهِ مِنۢ بَيْنِنَا بَلْ هُوَ كَذَّابٌ أَشِرٌ

Amharic Translation - Africa Academy25. «ከእኛ መካከል በእርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራዕይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَعْلَمُونَ غَدًا مَّنِ ٱلْكَذَّابُ ٱلْأَشِرُ

Amharic Translation - Africa Academy26. ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا مُرْسِلُوا۟ ٱلنَّاقَةِ فِتْنَةً لَّهُمْ فَٱرْتَقِبْهُمْ وَٱصْطَبِرْ

Amharic Translation - Africa Academy27. እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን:: ተጠባበቃቸዉም ታገስም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَبِّئْهُمْ أَنَّ ٱلْمَآءَ قِسْمَةٌۢ بَيْنَهُمْ كُلُّ شِرْبٍ مُّحْتَضَرٌ

Amharic Translation - Africa Academy28. ውሃዉም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው:: ከውሃ የሆነ ፈንታ ሁሉ በየተራ የሚጣዱት ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَنَادَوْا۟ صَاحِبَهُمْ فَتَعَاطَىٰ فَعَقَرَ

Amharic Translation - Africa Academy29. ጓደኛቸውንም ጠሩት:: ወዲያዉም (ሰይፉን) ተቀበለ:: ወጋትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِى وَنُذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy30. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ صَيْحَةً وَٰحِدَةً فَكَانُوا۟ كَهَشِيمِ ٱلْمُحْتَظِرِ

Amharic Translation - Africa Academy31. እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው። ወዲያዉም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ እርጋፊ ሆኑ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy32. ቁርኣንን ለመገንዘብ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ قَوْمُ لُوطٍۭ بِٱلنُّذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy33. የ(ነብዩ) ሉጥ ህዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّآ ءَالَ لُوطٍ نَّجَّيْنَٰهُم بِسَحَرٍ

Amharic Translation - Africa Academy34. እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስ ላክን:: የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نِّعْمَةً مِّنْ عِندِنَا كَذَٰلِكَ نَجْزِى مَن شَكَرَ

Amharic Translation - Africa Academy35. ከእኛ በሆነ ጸጋ አዳናቸው:: ልክ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَنذَرَهُم بَطْشَتَنَا فَتَمَارَوْا۟ بِٱلنُّذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy36. ብርቱ አያያዛችንን በእርግጥ አስጠነቀቅናቸው:: በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ رَٰوَدُوهُ عَن ضَيْفِهِۦ فَطَمَسْنَآ أَعْيُنَهُمْ فَذُوقُوا۟ عَذَابِى وَنُذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy37. ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት። ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን። ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎቹን ቅመሱ አልናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ صَبَّحَهُم بُكْرَةً عَذَابٌ مُّسْتَقِرٌّ

Amharic Translation - Africa Academy38. በማለዳም ዘወታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَذُوقُوا۟ عَذَابِى وَنُذُرِ

Amharic Translation - Africa Academy39. ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎችም ቅመሱ ተባሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy40 ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ جَآءَ ءَالَ فِرْعَوْنَ ٱلنُّذُرُ

Amharic Translation - Africa Academy41.የፈርዖንን ቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጧቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا كُلِّهَا فَأَخَذْنَٰهُمْ أَخْذَ عَزِيزٍ مُّقْتَدِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy42. በተዓምራታችንም በሁሏም አስተባበሉ:: የብርቱ ቻይንም አቀጣጥ ቀጣናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَكُفَّارُكُمْ خَيْرٌ مِّنْ أُو۟لَٰٓئِكُمْ أَمْ لَكُم بَرَآءَةٌ فِى ٱلزُّبُرِ

Amharic Translation - Africa Academy43. የእናንተ ከሓዲያኖቻችሁ ከእነዚያችሁ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለእናንተ በመጽሐፎች ውስጥ በተለየ የተነገረ ነፃነት አላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ يَقُولُونَ نَحْنُ جَمِيعٌ مُّنتَصِرٌ

Amharic Translation - Africa Academy44. ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيُهْزَمُ ٱلْجَمْعُ وَيُوَلُّونَ ٱلدُّبُرَ

Amharic Translation - Africa Academy45. ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ:: ጀርባዎቻቸውንም ያዞራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلِ ٱلسَّاعَةُ مَوْعِدُهُمْ وَٱلسَّاعَةُ أَدْهَىٰ وَأَمَرُّ

Amharic Translation - Africa Academy46. ይልቁንም ሰዓቲቱ ትንሳኤ ቀጠሯቸው ናት:: ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُجْرِمِينَ فِى ضَلَٰلٍ وَسُعُرٍ

Amharic Translation - Africa Academy47. አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يُسْحَبُونَ فِى ٱلنَّارِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمْ ذُوقُوا۟ مَسَّ سَقَرَ

Amharic Translation - Africa Academy48. በእሳት ውስጥ በፊታቸው በሚጎተቱበት ቀን የሰቀርን (የገሀነምን) ቅጣት መንካትን ቅመሱ ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا كُلَّ شَىْءٍ خَلَقْنَٰهُ بِقَدَرٍ

Amharic Translation - Africa Academy49. እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَمْرُنَآ إِلَّا وَٰحِدَةٌ كَلَمْحٍۭ بِٱلْبَصَرِ

Amharic Translation - Africa Academy50. ትዕዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት የሆነች አንዲት ቃል እንጂ ሌላ አይደለችም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَهْلَكْنَآ أَشْيَاعَكُمْ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy51. ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፤ ተገሳጭ አለን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكُلُّ شَىْءٍ فَعَلُوهُ فِى ٱلزُّبُرِ

Amharic Translation - Africa Academy52. የሰሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكُلُّ صَغِيرٍ وَكَبِيرٍ مُّسْتَطَرٌ

Amharic Translation - Africa Academy53. ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተፃፈ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُتَّقِينَ فِى جَنَّٰتٍ وَنَهَرٍ

Amharic Translation - Africa Academy54. አላህን ፈሪ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى مَقْعَدِ صِدْقٍ عِندَ مَلِيكٍ مُّقْتَدِرٍۭ

Amharic Translation - Africa Academy55. እነርሱም (ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ላይ ከሆነው ንጉስ አላህ ዘንድ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70