ሱረቱ At-Tur الطور
49 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 76
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلطُّورِ
Amharic Translation - Africa Academy1. በጡር (ጋራ)፤ እምላለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكِتَٰبٍ مَّسْطُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy2. በተጻፈው መጽሓፍም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِى رَقٍّ مَّنشُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy3. በተዘረጋው ብራና ላይ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْبَيْتِ ٱلْمَعْمُورِ
Amharic Translation - Africa Academy4. በደመቀው ቤትም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلسَّقْفِ ٱلْمَرْفُوعِ
Amharic Translation - Africa Academy5. ከፍ በተደረገው ጣራም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْبَحْرِ ٱلْمَسْجُورِ
Amharic Translation - Africa Academy6. በእሳት በተሞላው ባህርም እምላለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ لَوَٰقِعٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው (የማይቀር ነው)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا لَهُۥ مِن دَافِعٍ
Amharic Translation - Africa Academy8. ለእርሱ ምንም ገፍታሪ የለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ تَمُورُ ٱلسَّمَآءُ مَوْرًا
Amharic Translation - Africa Academy9. ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይሆናል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَسِيرُ ٱلْجِبَالُ سَيْرًا
Amharic Translation - Africa Academy10. ተራራዎችም መሄድን በሚሄዱበት ቀን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَوَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy11. ላስተባባዮችም ሁሉ ያን ጊዜ ወዮላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ هُمْ فِى خَوْضٍ يَلْعَبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. ለነዚያ ለእነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለሆኑት ሰዎች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ يُدَعُّونَ إِلَىٰ نَارِ جَهَنَّمَ دَعًّا
Amharic Translation - Africa Academy13. ወደ ገሀነም እሳት በሀይል መገፍተርን በሚገፈተሩበት ቀን
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذِهِ ٱلنَّارُ ٱلَّتِى كُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. «ይህች ያቺ በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት ይባላሉ»።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَسِحْرٌ هَٰذَآ أَمْ أَنتُمْ لَا تُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. «ይህ (ፊት ትሉን እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱصْلَوْهَا فَٱصْبِرُوٓا۟ أَوْ لَا تَصْبِرُوا۟ سَوَآءٌ عَلَيْكُمْ إِنَّمَا تُجْزَوْنَ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. «ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሱ በእናንተ ላይ እኩል ነው:: የምትመነዱት ትሰሩት የነበራችሁትን ፍዳ ብቻ ነው» ይባላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلْمُتَّقِينَ فِى جَنَّٰتٍ وَنَعِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy17. አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٰكِهِينَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمْ رَبُّهُمْ وَوَقَىٰهُمْ رَبُّهُمْ عَذَابَ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy18. ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ሆነው በገነት ውስጥ ናቸው:: የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ هَنِيٓـًٔۢا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy19. «ትሰሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ሆናችሁ ብሉ ጠጡም» (ይባላሉ።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ سُرُرٍ مَّصْفُوفَةٍ وَزَوَّجْنَٰهُم بِحُورٍ عِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy20. በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ሆነው በገነት ይኖራሉ:: አይናማዎች በሆኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱتَّبَعَتْهُمْ ذُرِّيَّتُهُم بِإِيمَٰنٍ أَلْحَقْنَا بِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَمَآ أَلَتْنَٰهُم مِّنْ عَمَلِهِم مِّن شَىْءٍ كُلُّ ٱمْرِئٍۭ بِمَا كَسَبَ رَهِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy21. እነዚያም በአላህ ያመኑና ዝርያቸዉም በእውነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን ከእነርሱ ጋር እናስጠጋቸዋለን:: ከስራዎቻቸዉም ምንንም አናጎድልባቸዉም:: ሰው ሁሉ በሰራው ስራ ተጠያቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَمْدَدْنَٰهُم بِفَٰكِهَةٍ وَلَحْمٍ مِّمَّا يَشْتَهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy22. ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَتَنَٰزَعُونَ فِيهَا كَأْسًا لَّا لَغْوٌ فِيهَا وَلَا تَأْثِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ:: በውስጧ ውድቅ ንግግርና መወንጀልም የለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ غِلْمَانٌ لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ لُؤْلُؤٌ مَّكْنُونٌ
Amharic Translation - Africa Academy24. ለእነርሱም የሆኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሰላፍ ይዘዋወራሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَسَآءَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. የሚጠያየቁ ሆነዉም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ إِنَّا كُنَّا قَبْلُ فِىٓ أَهْلِنَا مُشْفِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy26. ይላሉም: «እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ ከቅጣት ፈሪዎች ነበርን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَنَّ ٱللَّهُ عَلَيْنَا وَوَقَىٰنَا عَذَابَ ٱلسَّمُومِ
Amharic Translation - Africa Academy27. «አላህ በእኛ ላይ ለገሰ:: የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلُ نَدْعُوهُ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْبَرُّ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy28. «እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን:: እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَذَكِّرْ فَمَآ أَنتَ بِنِعْمَتِ رَبِّكَ بِكَاهِنٍ وَلَا مَجْنُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሰዎችን) አስታውስ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም እብድም አይደለህም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يَقُولُونَ شَاعِرٌ نَّتَرَبَّصُ بِهِۦ رَيْبَ ٱلْمَنُونِ
Amharic Translation - Africa Academy30. «ይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የሆነ ባለ ቅኔ ነው» ይላሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ تَرَبَّصُوا۟ فَإِنِّى مَعَكُم مِّنَ ٱلْمُتَرَبِّصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ تَأْمُرُهُمْ أَحْلَٰمُهُم بِهَٰذَآ أَمْ هُمْ قَوْمٌ طَاغُونَ
Amharic Translation - Africa Academy32. አእምሮዎቻቸው በዚህ ተግባር ያዟቸዋልን? ወይስ በእውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊ ህዝቦች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يَقُولُونَ تَقَوَّلَهُۥ بَل لَّا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. ወይም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም። ይልቁንም አያምኑም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلْيَأْتُوا۟ بِحَدِيثٍ مِّثْلِهِۦٓ إِن كَانُوا۟ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy34. እውነተኞችም ከሆኑ መሰሉ የሆነን ንግግር ያምጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ خُلِقُوا۟ مِنْ غَيْرِ شَىْءٍ أَمْ هُمُ ٱلْخَٰلِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. ወይስ ያለ አንዳች ፈጣሪ ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ خَلَقُوا۟ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بَل لَّا يُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም፤ አያረጋግጡም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ عِندَهُمْ خَزَآئِنُ رَبِّكَ أَمْ هُمُ ٱلْمُصَۣيْطِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy37. ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸው?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ لَهُمْ سُلَّمٌ يَسْتَمِعُونَ فِيهِ فَلْيَأْتِ مُسْتَمِعُهُم بِسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy38. ወይስ ለእነርሱ በእርሱ ላይ ከሰማይ የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? (እንግዲያውስ) አድማጫቸዉ ሰማሁ የሚለውን ግልጽ አስረጂ ያምጣ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ لَهُ ٱلْبَنَٰتُ وَلَكُمُ ٱلْبَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. ወይስ ለእናንተ ወንዶች ልጆች እያሏችሁ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ تَسْـَٔلُهُمْ أَجْرًا فَهُم مِّن مَّغْرَمٍ مُّثْقَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy40. ወይስ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? በዚህም እነርሱ በእዳው የተከበዱ ናቸውን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ عِندَهُمُ ٱلْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy41. ወይስ ሩቁ ሚስጢር እነርሱ ዘንድ በመሆኑ እነርሱ ይጽፋሉን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يُرِيدُونَ كَيْدًا فَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ هُمُ ٱلْمَكِيدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያም የካዱት የተተነኮለባቸው ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ لَهُمْ إِلَٰهٌ غَيْرُ ٱللَّهِ سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. ወይስ ለእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن يَرَوْا۟ كِسْفًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ سَاقِطًا يَقُولُوا۟ سَحَابٌ مَّرْكُومٌ
Amharic Translation - Africa Academy44. ከሰማይም ቁራጭን በእነርሱ ላይ ወዳቂ ሆኖ ቢያዩ ኖሮ «ይህ የተደራረበ ደመና ነው» ይሉ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَذَرْهُمْ حَتَّىٰ يُلَٰقُوا۟ يَوْمَهُمُ ٱلَّذِى فِيهِ يُصْعَقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)ያንንም በእርሱ የሚገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ لَا يُغْنِى عَنْهُمْ كَيْدُهُمْ شَيْـًٔا وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy46. ተንኮላቸው ከእነርሱ ምንም የማይጠቅማቸውንና እነርሱም የማይረዱበትን ቀን እስከሚያገኙ ተዋቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ عَذَابًا دُونَ ذَٰلِكَ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy47. ለእነዚያም ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አለባቸው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ فَإِنَّكَ بِأَعْيُنِنَا وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ حِينَ تَقُومُ
Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: አንተ በጥበቃችን ስር ነህና:: ጌታህንም በምትቆም ጊዜ ከማመስገን ጋር አጥራው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَإِدْبَٰرَ ٱلنُّجُومِ
Amharic Translation - Africa Academy49. ከሌሊቱና በከዋክብት መደበቂያም ጊዜ (ንጋት ላይም) አጥራው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→