ٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلْمَغْفِرَةِ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ وَإِذْ أَنتُمْ أَجِنَّةٌ فِى بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمْ فَلَا تُزَكُّوٓا۟ أَنفُسَكُمْ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy32. እነርሱም ከጥቃቅን ጥፋቶች በቀር ከባባድ ወንጀሎችንና አጸያፊ ተግባሮችን የራቁ ናቸው:: ጌታህ ምህረተ ሰፊ ነው:: እርሱ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜም ሆነ በእናቶቻችሁ ማሕጸን ውስጥ ጽንሶች በሁናችሁበት ጊዜ ያውቃችኋል:: ስለዚህ እራሳችሁን አታሞግሱ:: እርሱ በትክክል የሚፈራውን ሰው ከሁሉም ይበልጥ አዋቂ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ (የሚማሩ) ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡