caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ash-Shu'araa الشعراء

227 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 47

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ طسٓمٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ጣ፤ሲን፤ሚይም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْمُبِينِ

Amharic Translation - Africa Academy2. እነዚህ ግልጽ የሆነው መጽሀፍ አናቅጽ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَعَلَّكَ بَٰخِعٌ نَّفْسَكَ أَلَّا يَكُونُوا۟ مُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን አማኞች ባለ መሆናቸው በቁጭት ነፍስህን እንዳታጠፋ ይፈራልሃል (ያሰጋል)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن نَّشَأْ نُنَزِّلْ عَلَيْهِم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ ءَايَةً فَظَلَّتْ أَعْنَٰقُهُمْ لَهَا خَٰضِعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy4. ብንሻ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይ ተዓምርን እናወርድና አንገቶቻቸው (መሪዎቻቸው) ለእርሷ ተዋራጆች እናደርጋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يَأْتِيهِم مِّن ذِكْرٍ مِّنَ ٱلرَّحْمَٰنِ مُحْدَثٍ إِلَّا كَانُوا۟ عَنْهُ مُعْرِضِينَ

Amharic Translation - Africa Academy5. ከአር-ረህማን ዘንድ አዲስ የተወረደ ተግሳፅ አይመጣላቸዉም:: ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَدْ كَذَّبُوا۟ فَسَيَأْتِيهِمْ أَنۢبَٰٓؤُا۟ مَا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. በእርግጥም አስተባበሉ:: የዚያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ወሬዎች ፍጻሜ ይመጣባቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَرَوْا۟ إِلَى ٱلْأَرْضِ كَمْ أَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy7.ወደ ምድርም በውስጧ ከመልካም በቃይ ጎሳ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy8. በዚህ አስደናቂ ምልክት አለበት፤ አብዛኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በትክክል ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ نَادَىٰ رَبُّكَ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱئْتِ ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ሙሳን «ወደ እነዚያ በደለኛ ህዝቦች ሂድ።» በማለት በጠራው ጊዜ የሆነውን አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَوْمَ فِرْعَوْنَ أَلَا يَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. «ወደ ፈርዖን ህዝቦች አላህን አይፈሩምን?»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ إِنِّىٓ أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ

Amharic Translation - Africa Academy12. ሙሳም «ጌታዬ ሆይ! እኔ ያስተባብሉኛል ብዬ እፈራለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَضِيقُ صَدْرِى وَلَا يَنطَلِقُ لِسَانِى فَأَرْسِلْ إِلَىٰ هَٰرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. «ልቤም ይጠባል፤ ምላሴም ይንተባተባል። ስለዚህ ወደ ሃሩንም ላክ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُمْ عَلَىَّ ذَنۢبٌ فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُونِ

Amharic Translation - Africa Academy14. «በተጨማሪም ለእነርሱም በእኔ ላይ (የደም) ወንጀል አላቸው:: ስለዚህ እንዳይገድሉኝም እፈራለሁ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ كَلَّا فَٱذْهَبَا بِـَٔايَٰتِنَآ إِنَّا مَعَكُم مُّسْتَمِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. አላህ አለ: «ተው! አይነኩህም ሁለታችሁም በተአምሮታችን ታጅባችሁ ሂዱ። እኛ ከናንተ ጋር ሁነን ሰሚዎች ነንና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأْتِيَا فِرْعَوْنَ فَقُولَآ إِنَّا رَسُولُ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy16. «ወደ ፈርዖንም ሂዱና። በሉትም: ‹እኛ የዓለማት ጌታ መልዕክተኞች ነን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَنْ أَرْسِلْ مَعَنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy17. «‹የኢስራኢልን ልጆችም ከእኛ ጋር ልቀቅልን።›» (በሉት)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَلَمْ نُرَبِّكَ فِينَا وَلِيدًا وَلَبِثْتَ فِينَا مِنْ عُمُرِكَ سِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy18. ፈርዖንም አለ፡ «ልጅ ሆንህ በእኛ ውስጥ አላሳደግንህምን? በእኛ ውስጥም ከዕድሜህ ብዙ ዓመታትን አልተቀመጥክምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفَعَلْتَ فَعْلَتَكَ ٱلَّتِى فَعَلْتَ وَأَنتَ مِنَ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy19. «ያችን የሰራሃትን ስራስ አልሰራህምን? አንተ ከውለታ ቢሶች ነህ።» (አለ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ فَعَلْتُهَآ إِذًا وَأَنَا۠ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ

Amharic Translation - Africa Academy20. ሙሳም አለ፡ «ያን ጊዜ እኔም ከተሳሳቱት ሆኜ ሰራኋት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَفَرَرْتُ مِنكُمْ لَمَّا خِفْتُكُمْ فَوَهَبَ لِى رَبِّى حُكْمًا وَجَعَلَنِى مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy21. «በፈራኋችሁም ጊዜ ከናንተ ሸሸሁ። ጌታዬም ለእኔ ጥበብን ሰጠኝ:: ከመልዕክተኞችም አደረገኝ:።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتِلْكَ نِعْمَةٌ تَمُنُّهَا عَلَىَّ أَنْ عَبَّدتَّ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy22. «ይህችም የኢስራኢልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻድቅባት ጸጋ ናት።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ فِرْعَوْنُ وَمَا رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy23. ፈርዖን: «ሙሳ ሆይ! ላከኝ የምትለው የዓለማት ጌታ ምንድን ነው?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَآ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy24. ሙሳ፡- «የሰማያት የምድርና በመካከላቸዉም ያለው ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው። የምታረጋግጡ ብትሆኑ ነገሩ ይህ ነው።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لِمَنْ حَوْلَهُۥٓ أَلَا تَسْتَمِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. ፈርዖንም ዙሪያውን ላሉት ሰዎች: «አትሰሙምን?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبُّكُمْ وَرَبُّ ءَابَآئِكُمُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ሙሳ፡- «ጌታችሁና የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِنَّ رَسُولَكُمُ ٱلَّذِىٓ أُرْسِلَ إِلَيْكُمْ لَمَجْنُونٌ

Amharic Translation - Africa Academy27. ፈርዖን፡- «ያ ወደ እናንተ የተላከው መልዕክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبُّ ٱلْمَشْرِقِ وَٱلْمَغْرِبِ وَمَا بَيْنَهُمَآ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. ሙሳ፡- «(አላህ) የምስራቅና የምዕራብ በመካከላቸዉም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው:: ታውቁ እንደሆናችሁ (እመኑበት)።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَئِنِ ٱتَّخَذْتَ إِلَٰهًا غَيْرِى لَأَجْعَلَنَّكَ مِنَ ٱلْمَسْجُونِينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. ፈርዖን: «ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በእውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَوَلَوْ جِئْتُكَ بِشَىْءٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy30. ሙሳ፡- «ግልጽ የሆነ አስረጅ ባመጣም እንኳን?» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ فَأْتِ بِهِۦٓ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. ፊርዓውን «እንግዲያውስ ከእውነተኞች እንደሆንክ አስረጁን አምጣው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِىَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy32. በትሩንም ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَزَعَ يَدَهُۥ فَإِذَا هِىَ بَيْضَآءُ لِلنَّٰظِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy33 እጁንም አወጣ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ (የምታበራ) ሆነች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لِلْمَلَإِ حَوْلَهُۥٓ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy34. ፈርዖንም በዙሪያው ላሉት መማክርት አለ: «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُرِيدُ أَن يُخْرِجَكُم مِّنْ أَرْضِكُم بِسِحْرِهِۦ فَمَاذَا تَأْمُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. «ከምድራችሁ በድግምት ሊያወጣችሁ ይፈልጋልና ምንን ታዛላችሁ?» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ أَرْجِهْ وَأَخَاهُ وَٱبْعَثْ فِى ٱلْمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy36. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደየከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَأْتُوكَ بِكُلِّ سَحَّارٍ عَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy37. «በጣም አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَجُمِعَ ٱلسَّحَرَةُ لِمِيقَٰتِ يَوْمٍ مَّعْلُومٍ

Amharic Translation - Africa Academy38. ድግምተኞችም በታወቀ ቀን ቀጠሮ ተሰበሰቡ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقِيلَ لِلنَّاسِ هَلْ أَنتُم مُّجْتَمِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy39. ለሰዎቹም ተባለ: «እናንተ ተሰብስባችኋልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَعَلَّنَا نَتَّبِعُ ٱلسَّحَرَةَ إِن كَانُوا۟ هُمُ ٱلْغَٰلِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy40. «ድግምተኞቹን እነርሱ አሸናፊዎች ቢሆኑ እንከተል ዘንድ» ተባለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالُوا۟ لِفِرْعَوْنَ أَئِنَّ لَنَا لَأَجْرًا إِن كُنَّا نَحْنُ ٱلْغَٰلِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy41. ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን: «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ ዋጋ አለን?» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ نَعَمْ وَإِنَّكُمْ إِذًا لَّمِنَ ٱلْمُقَرَّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy42. እርሱም( ፈርዖን) «አዎን። እናንተ ያን ጊዜ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلْقُوا۟ مَآ أَنتُم مُّلْقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. ሙሳ ለእነርሱ: «የምትጥሉትን ጣሉ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَلْقَوْا۟ حِبَالَهُمْ وَعِصِيَّهُمْ وَقَالُوا۟ بِعِزَّةِ فِرْعَوْنَ إِنَّا لَنَحْنُ ٱلْغَٰلِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44. ገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ:: «በፈርዖንም ክብር ይሁንብን። እኛ በእርግጥ አሸናፊዎች ነን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَلْقَىٰ مُوسَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِىَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy45. ሙሳም ብትሩን ጣለ:: ወዲያዉም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأُلْقِىَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. ከዚያም ድግምተኞቹ ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ አደረጉ(ወረዱ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy47. እነርሱም አሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. «በሙሳና በሃሩን ጌታ (አመንን)።» (አሉ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ ءَامَنتُمْ لَهُۥ قَبْلَ أَنْ ءَاذَنَ لَكُمْ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِى عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحْرَ فَلَسَوْفَ تَعْلَمُونَ لَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَٰفٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy49. ፈርዖንም «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው። ወደፊትም በእርግጥ የሚያገኛችሁን ታውቃላችሁ:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን ቀኝና ግራን (በማናጋት) በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: ሁላችሁንም እሰቅላችኃለሁ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ لَا ضَيْرَ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50. እነርሱም አሉ፡- «ጉዳት የለብንም እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا نَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy51. «እኛ የምዕምናን መጀመሪያ በመሆናችን ጌታችን ኃጢአቶቻችንን ለኛ ሊምር እንከጅላለን።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنْ أَسْرِ بِعِبَادِىٓ إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy52. ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ሂድ እናንተ የሚከተሏችሁ ናችሁና።» ስንል ላክን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَرْسَلَ فِرْعَوْنُ فِى ٱلْمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy53. ፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَشِرْذِمَةٌ قَلِيلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy54. «እነዚህ ጥቂቶቹ ቡድኖች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُمْ لَنَا لَغَآئِظُونَ

Amharic Translation - Africa Academy55. «እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّا لَجَمِيعٌ حَٰذِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy56. «እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَخْرَجْنَٰهُم مِّن جَنَّٰتٍ وَعُيُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy57. አወጣናቸዉም፤ ከአትክልቶችና ከምንጮች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكُنُوزٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy58. ከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ وَأَوْرَثْنَٰهَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy59. ልክ እንደዚሁ ለኢስራኢል ልጆች አወረስናትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَتْبَعُوهُم مُّشْرِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy60. ጸሐይዋ ስትወጣም ተከተሏቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا تَرَٰٓءَا ٱلْجَمْعَانِ قَالَ أَصْحَٰبُ مُوسَىٰٓ إِنَّا لَمُدْرَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ (የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ كَلَّآ إِنَّ مَعِىَ رَبِّى سَيَهْدِينِ

Amharic Translation - Africa Academy62. ሙሳ «በፍፁም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱضْرِب بِّعَصَاكَ ٱلْبَحْرَ فَٱنفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرْقٍ كَٱلطَّوْدِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy63. ወደ ሙሳም «ባህሩን በበትርህ ምታው።» ስንል ላክንበት:: ከዚያ መታውና ተከፈለ፤ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ሆነ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَزْلَفْنَا ثَمَّ ٱلْـَٔاخَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy64. እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنجَيْنَا مُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy65. ሙሳንና ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَغْرَقْنَا ٱلْـَٔاخَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy66. ከዚያም ሌሎቹን አሰመጥን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy67. በዚህ ውስጥ ታላቅ ተዐምር አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ እርሱ አሸናፊና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ إِبْرَٰهِيمَ

Amharic Translation - Africa Academy69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም (በህዝቦችህ) ላይ የኢብራሂምን ወሬ አንብብላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. ለአባቱና ለህዝቦቹ «ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy71. «ጣኦታትን እንገዛለን:: እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ هَلْ يَسْمَعُونَكُمْ إِذْ تَدْعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. ኢብራሂም አለ፡- «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يَنفَعُونَكُمْ أَوْ يَضُرُّونَ

Amharic Translation - Africa Academy73. «ወይስ ይጠቅሟችኋልን? ወይስ ይጎዷችኋልን?»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ بَلْ وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا كَذَٰلِكَ يَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy74. «የለም! ነገር ግን አባቶቻችን ልክ እንደዚሁ ሲሰሩ አገኘን(ና እኛም እነርሱን እንከተላለን።») አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَفَرَءَيْتُم مَّا كُنتُمْ تَعْبُدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy75. እርሱም አለ: «ትገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَنتُمْ وَءَابَآؤُكُمُ ٱلْأَقْدَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy76. «እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም እየተገዛችሁት ያለውን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّىٓ إِلَّا رَبَّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy77. «እነርሱም ጣኦቶቹ ለእኔ ጠላቶች ናቸው:: የዓለማት ጌታ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ወዳጄ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى خَلَقَنِى فَهُوَ يَهْدِينِ

Amharic Translation - Africa Academy78. «እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው:: እርሱም ይመራኛል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِى هُوَ يُطْعِمُنِى وَيَسْقِينِ

Amharic Translation - Africa Academy79. «ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝም ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

Amharic Translation - Africa Academy80. «በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِى يُمِيتُنِى ثُمَّ يُحْيِينِ

Amharic Translation - Africa Academy81. «ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደርገኝ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِىٓ أَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لِى خَطِيٓـَٔتِى يَوْمَ ٱلدِّينِ

Amharic Translation - Africa Academy82. «ያም በፍርዱ ቀን ኃጢአቴን ሊምርልኝ የምከጅለው ነው።» (አለ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبِّ هَبْ لِى حُكْمًا وَأَلْحِقْنِى بِٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy83. (ኢብራሂምም) «ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ስጠኝ በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱجْعَل لِّى لِسَانَ صِدْقٍ فِى ٱلْـَٔاخِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy84. «በኋለኞቹም ህዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱجْعَلْنِى مِن وَرَثَةِ جَنَّةِ ٱلنَّعِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy85. «የጸጋይቱን ገነት ከሚወርሱትም ሰዎች አድርገኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱغْفِرْ لِأَبِىٓ إِنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ

Amharic Translation - Africa Academy86. «ለአባቴም ኃጢያቱን ማር። እርሱ ከተሳሳቱት ነበርና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُخْزِنِى يَوْمَ يُبْعَثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy87. «በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy88. «ገንዘብም ሆነ ልጆች በማይጠቅሙበት ቀን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا مَنْ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy89. «ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ቢሆን አንጂ።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأُزْلِفَتِ ٱلْجَنَّةُ لِلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy90. ገነትም ለጥንቁቆቹ በምትቀረብበት ቀን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبُرِّزَتِ ٱلْجَحِيمُ لِلْغَاوِينَ

Amharic Translation - Africa Academy91. ገሀነምም ለጠማሞቹ በምትገለጽበት ቀን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقِيلَ لَهُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَعْبُدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy92. ለእነርሱም «እነዚያ ትገዟቸው የነበራችሁት የት ናቸው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِن دُونِ ٱللَّهِ هَلْ يَنصُرُونَكُمْ أَوْ يَنتَصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy93. « ከአላህ ሌላ ሲሆኑ (ትገዟቸው የነበራችሁ) ይረዱዋችኋልን? ወይስ ለራሳቸው ይረዳሉን?» በሚባል ቀን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكُبْكِبُوا۟ فِيهَا هُمْ وَٱلْغَاوُۥنَ

Amharic Translation - Africa Academy94. በውስጧም እነርሱና ጠማሞች በፊቶቻቸው ተጥለው ይንከባለላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجُنُودُ إِبْلِيسَ أَجْمَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy95 የሰይጣንም ሰራዊቶች መላዉም ይጣላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ وَهُمْ فِيهَا يَخْتَصِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy96. እነርሱም በርሷ ውስጥ የሚከራከሩ ሆነው ይላሉ:

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَٱللَّهِ إِن كُنَّا لَفِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy97. «በአላህ እንምላለን፤ እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነብርን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ نُسَوِّيكُم بِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy98. «በዓለማት ጌታ ባስተካከልናችሁ ጊዜ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَضَلَّنَآ إِلَّا ٱلْمُجْرِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy99. «አመጸኞቹም እንጅ ሌላ አላሳሳተንም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَا لَنَا مِن شَٰفِعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy100. «ከአማላጆችም ለኛ ምንም የለንም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا صَدِيقٍ حَمِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy101. «አዛኝ ወዳጅም የለንም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَوْ أَنَّ لَنَا كَرَّةً فَنَكُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy102 «ለእኛም አንዲት ጊዜ እንኳን የመመለስ እድል በኖረንና ከትክክለኛ አማኞች በሆን እንመኛለን።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy103. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ግሣጼ አለበት:: አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ قَوْمُ نُوحٍ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy105. የኑህ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ نُوحٌ أَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy106. ወንድማቸው ኑህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ፡ «አትጠነቀቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy107. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy108. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy109. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም:: ዋጋዬ ከዓለማት ጌታ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy110. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ أَنُؤْمِنُ لَكَ وَٱتَّبَعَكَ ٱلْأَرْذَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy111. እነርሱም «ወራዶቹ ብቻ የተከተሉህ ሆነህ ላንተ እናምናለን?» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ وَمَا عِلْمِى بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy112. እርሱም አላቸው፡- «ይሰሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝና?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ حِسَابُهُمْ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّى لَوْ تَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy113. «ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም:: ብታውቁ ኖሮ ይህንን ትረዱት ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy114. «እኔ አማኞችን አባራሪ አይደለሁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy115. «እኔም እኮ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» (አለ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ يَٰنُوحُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمَرْجُومِينَ

Amharic Translation - Africa Academy116. «ኑህ ሆይ! ከምትለው ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትሆናለህ።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوْمِى كَذَّبُونِ

Amharic Translation - Africa Academy117. እርሱም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ አስተባበሉኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱفْتَحْ بَيْنِى وَبَيْنَهُمْ فَتْحًا وَنَجِّنِى وَمَن مَّعِىَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy118. «በእኔና በእነርሱም መካከል ተገቢ ፍርድን ፍረድ:: ከእነርሱ አድነኝም:: ከእኔ ጋር ያሉትን አማኞችም አድን።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَنجَيْنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِى ٱلْفُلْكِ ٱلْمَشْحُونِ

Amharic Translation - Africa Academy119. እርሱንም ሆነ ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ በተሞላው መርከብ ውስጥ አዳንን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَغْرَقْنَا بَعْدُ ٱلْبَاقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy120. ከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰመጥን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy121. በዚህ ውስጥ ታላቅ ግሣጼ አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy122. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ عَادٌ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy123. ዓድ መልዕክተኞችን አስተባበለች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ هُودٌ أَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy124. ወንድማቸው ሁድ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy125. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy126. «አላህን ብቻ ፍሩ ታዘዙኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy127. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَتَبْنُونَ بِكُلِّ رِيعٍ ءَايَةً تَعْبَثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy128. «የምትጫወቱ ሆናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክት ትገነባላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَتَّخِذُونَ مَصَانِعَ لَعَلَّكُمْ تَخْلُدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy129. «የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ህንፃዎችንም ለዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ሆናችሁ ትሰራላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا بَطَشْتُم بَطَشْتُمْ جَبَّارِينَ

Amharic Translation - Africa Academy130. «በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ሆናችሁ ትቀጣላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy131. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّقُوا۟ ٱلَّذِىٓ أَمَدَّكُم بِمَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy132. «ያንንም በምታውቁት ጸጋ ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَدَّكُم بِأَنْعَٰمٍ وَبَنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy133. «በእንስሳዎችና በልጆችም ያጣቀማችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَنَّٰتٍ وَعُيُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy134. «በአትክልቶችና በምንጮችም ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy135. «እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ سَوَآءٌ عَلَيْنَآ أَوَعَظْتَ أَمْ لَمْ تَكُن مِّنَ ٱلْوَٰعِظِينَ

Amharic Translation - Africa Academy136. እነርሱም አሉ: «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮች ባትሆንም በእኛ ላይ እኩል ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ هَٰذَآ إِلَّا خُلُقُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy137. «(ያለንበትን አንለቅም)። ይህ የፊተኞቹ ሰዎች መንገድ እንጂ ሌላ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy138. «እኛም የምንቀጣ አይደለንም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَذَّبُوهُ فَأَهْلَكْنَٰهُمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy139. አስተባበሉትም፤ አጠፋናቸዉም፤ በዚህም ውስጥ እርግጠኛ ግሣጼም አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy140. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊውና አዛኙ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ ثَمُودُ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy141. የሰሙድ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ صَٰلِحٌ أَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy142. ወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy143. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy144. «አላህን ፍሩ ታዘዙኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy145. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَتُتْرَكُونَ فِى مَا هَٰهُنَآ ءَامِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy146. «በዚያ እዚህ ባለው ጸጋ ውስጥ የረካችሁ ሆናችሁ ትቀራላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى جَنَّٰتٍ وَعُيُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy147. «በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَزُرُوعٍ وَنَخْلٍ طَلْعُهَا هَضِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy148. «በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በሆነች ዘንባባም ውስጥ ትቀራላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَنْحِتُونَ مِنَ ٱلْجِبَالِ بُيُوتًا فَٰرِهِينَ

Amharic Translation - Africa Academy149. «ብልሆች ሆናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy150. «አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُطِيعُوٓا۟ أَمْرَ ٱلْمُسْرِفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy151. «የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُفْسِدُونَ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا يُصْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy152. «የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን (ትዕዛዝ አትከተሉ)።» (አለ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلْمُسَحَّرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy153. እነርሱም አሉ: «አንተ በብዙ ከተደገመባቸው ሰዎች ብቻ ነህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُنَا فَأْتِ بِـَٔايَةٍ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy154. «አንተ ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም። ከእውነተኞችም ከሆንክ ተዐምርን አምጣ።» (አሉ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ هَٰذِهِۦ نَاقَةٌ لَّهَا شِرْبٌ وَلَكُمْ شِرْبُ يَوْمٍ مَّعْلُومٍ

Amharic Translation - Africa Academy155. እርሱም አለ: «ይህች ግመል ናት:: ለእርሷ የመጠጥ ፋንታ አላት:: ለእናንተም የታወቀ ቀን ፋንታ አላችሁ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابُ يَوْمٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy156. «በክፉም አትንኳት የታላቅ ቀን ቅጣት ይይዛችኋልና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَعَقَرُوهَا فَأَصْبَحُوا۟ نَٰدِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy157. ወጓትም:: ወዲያው ተጸፃቾች ሆነው አነጉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَخَذَهُمُ ٱلْعَذَابُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy158. ቅጣትም ያዛቸው በዚህም ውስጥ አያሌ ግሣጼ አለበት:: አብዛኞቻቸዉም አማኞች አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy159. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊውና አዛኙ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ قَوْمُ لُوطٍ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy160. የሉጥ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ لُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy161. ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy162. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy163. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy164. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَتَأْتُونَ ٱلذُّكْرَانَ مِنَ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy165. «ከዓለማት ሰዎች መካከል የተለየ ወንዶችን ትገናኛላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمْ رَبُّكُم مِّنْ أَزْوَٰجِكُم بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ عَادُونَ

Amharic Translation - Africa Academy166. «ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነት እናንተ ወሰን አላፊዎች ህዝቦች ናችሁ።» (አለ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ يَٰلُوطُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُخْرَجِينَ

Amharic Translation - Africa Academy167. እነርሱም አሉ: «ሉጥ ሆይ! ከዚህ ነገርህ ባትከለከል በእርግጥ በሀይል ከአገር ከሚወጡት ትሆናለህ።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِنِّى لِعَمَلِكُم مِّنَ ٱلْقَالِينَ

Amharic Translation - Africa Academy168. እርሱም አለ: «እኔ ስራችሁን ከሚጠሉት ሰዎች አንዱ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبِّ نَجِّنِى وَأَهْلِى مِمَّا يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy169. «ጌታዬ ሆይ! እኔንም ሆነ ቤተሰቦቼን እኒህ ህዝቦች ከሚሰሩት ስራ ቅጣት አድነን።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَنَجَّيْنَٰهُ وَأَهْلَهُۥٓ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy170. እርሱንም ሆነ ቤተሰቦቹንም በጠቅላላ አዳንናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا عَجُوزًا فِى ٱلْغَٰبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy171. በቀሪዎቹ ውስጥ የሆነች አሮጊት ስተቀር (እርሷ ግን ጠፋች)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ دَمَّرْنَا ٱلْـَٔاخَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy172. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا فَسَآءَ مَطَرُ ٱلْمُنذَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy173. በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናብን አዘነብንባቸው:: የተስፋራሪዎችም ዝናብ ከፋ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy174. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy175. ጌታህ እርሱ አሸናፊውና አዛኙ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَ أَصْحَٰبُ لْـَٔيْكَةِ ٱلْمُرْسَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy176. የአይካ ሰዎች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لَهُمْ شُعَيْبٌ أَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy177. ወንድማቸው ሹዐይብ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy178. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy179. «አላህን ፍሩ፤ ታዘዙኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy180. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْفُوا۟ ٱلْكَيْلَ وَلَا تَكُونُوا۟ مِنَ ٱلْمُخْسِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy181. «ስፍርንም ሙሉ:: ከአጎዳዮችም አትሁኑ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَزِنُوا۟ بِٱلْقِسْطَاسِ ٱلْمُسْتَقِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy182. «በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَبْخَسُوا۟ ٱلنَّاسَ أَشْيَآءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ مُفْسِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy183. «ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው:: በምድርም ላይ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّقُوا۟ ٱلَّذِى خَلَقَكُمْ وَٱلْجِبِلَّةَ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy184. «ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች የፈጠረውን ፍሩ።» (ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلْمُسَحَّرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy185. እነርሱም አሉ: «ሹዓይብ ሆይ! አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች አንዱ ነህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُنَا وَإِن نَّظُنُّكَ لَمِنَ ٱلْكَٰذِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy186. «አንተም ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም:: እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَسْقِطْ عَلَيْنَا كِسَفًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy187. «ከእውነተኞችም እንደሆንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን።» (አሉ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّىٓ أَعْلَمُ بِمَا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy188. «ጌታዬ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمْ عَذَابُ يَوْمِ ٱلظُّلَّةِ إِنَّهُۥ كَانَ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy189. አስተባበሉትም የጥላይቱ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፤ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት ነበርና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً وَمَا كَانَ أَكْثَرُهُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy190. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛዛቻቸዉም አማኞች አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy191. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊዉንና አዛኙ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُۥ لَتَنزِيلُ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy192. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلْأَمِينُ

Amharic Translation - Africa Academy193. እርሱን ታማኙ መንፈስ ጂብሪል አወረደው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلْمُنذِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy194. ከአስፈራሪዎች ነብያት ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ አወረደው፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِلِسَانٍ عَرَبِىٍّ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy195. ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ፤ (አወረደው)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُۥ لَفِى زُبُرِ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy196. እርሱም (ቁርኣን) በቀድሞዎቹ መጽሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَكُن لَّهُمْ ءَايَةً أَن يَعْلَمَهُۥ عُلَمَٰٓؤُا۟ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy197. የኢስራኢል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መሆኑ ለእነርሱ (ለመካ ከሓዲያን) ምልክት አይሆናቸዉም?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ نَزَّلْنَٰهُ عَلَىٰ بَعْضِ ٱلْأَعْجَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy198. ከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነዉም ኖሮ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَرَأَهُۥ عَلَيْهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ مُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy199. በእነርሱ ላይ ቢያነበዉም በእርሱ አማኞች አይሆኑም ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ سَلَكْنَٰهُ فِى قُلُوبِ ٱلْمُجْرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy200. እንድዚሁ ማስተባበልን በተንኮለኞች ልቦች ውስጥ አስገባነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يُؤْمِنُونَ بِهِۦ حَتَّىٰ يَرَوُا۟ ٱلْعَذَابَ ٱلْأَلِيمَ

Amharic Translation - Africa Academy201. አሳማሚ ቅጣትን እስከሚያዩ ድረስ በእርሱ አያምኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَيَأْتِيَهُم بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy202. እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ ቅጣቱ ድንገት እስከሚመጣባቸዉም ድረስ (አያምኑም)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَيَقُولُوا۟ هَلْ نَحْنُ مُنظَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy203. በመጣባቸው ጊዜ: «እኛ የምንቆይ ነን?» እስከሚሉም (አያምኑም)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَبِعَذَابِنَا يَسْتَعْجِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy204. በቅጣታችን ያቻኩላሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَرَءَيْتَ إِن مَّتَّعْنَٰهُمْ سِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አየህን? ብዙ ዓመታትን ብናጣቅማቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ جَآءَهُم مَّا كَانُوا۟ يُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy206. ከዚያም ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቢመጣባቸው

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَآ أَغْنَىٰ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يُمَتَّعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy207. ይጣቀሙበት የነበሩት ሁሉ ከእነርሱ ምንም አያብቃቃቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy208. አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስፈራሪዎች ያሏት (እና ያስተባበለች) ሆና እንጂ አላጠፋንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذِكْرَىٰ وَمَا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy209. ይህች ግሣጼ ናት:: በዳዮችም አልነበርንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا تَنَزَّلَتْ بِهِ ٱلشَّيَٰطِينُ

Amharic Translation - Africa Academy210. ሰይጣናትም እርሱን ቁርኣንን አላወረዱትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يَنۢبَغِى لَهُمْ وَمَا يَسْتَطِيعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy211. ለእነርሱም አይገባቸዉም፤ አይችሉምም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُمْ عَنِ ٱلسَّمْعِ لَمَعْزُولُونَ

Amharic Translation - Africa Academy212. እነርሱ የመላዕክትን ንግግር ከመስማት የተከለከሉ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلْمُعَذَّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy213. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከሚቀጡት ትሆናለህና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنذِرْ عَشِيرَتَكَ ٱلْأَقْرَبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy214. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱخْفِضْ جَنَاحَكَ لِمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy215. (ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ ልዝብ ሁን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنْ عَصَوْكَ فَقُلْ إِنِّى بَرِىٓءٌ مِّمَّا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy216. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንቢ ካሉህ «እኔ ከምትሰሩት ወንጀል ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy217. (ሙሐመድ ሆይ!) አሸናፊና አዛኝ በሆነው ጌታህ ላይም ተጠጋ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى يَرَىٰكَ حِينَ تَقُومُ

Amharic Translation - Africa Academy218. በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَقَلُّبَكَ فِى ٱلسَّٰجِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy219. በሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ ላይ ተጠጋ::)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy220. እነሆ እርሱ (አላህ) ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ أُنَبِّئُكُمْ عَلَىٰ مَن تَنَزَّلُ ٱلشَّيَٰطِينُ

Amharic Translation - Africa Academy221. ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَنَزَّلُ عَلَىٰ كُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy222. በውሸታም ኃጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُلْقُونَ ٱلسَّمْعَ وَأَكْثَرُهُمْ كَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy223. የሰሙትን ወደ ጠንቋዮች ይጥላሉ:: አብዛኞቻቸዉም ውሸታሞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلشُّعَرَآءُ يَتَّبِعُهُمُ ٱلْغَاوُۥنَ

Amharic Translation - Africa Academy224. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎች ይከተሏቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ أَنَّهُمْ فِى كُلِّ وَادٍ يَهِيمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy225. እነርሱ (በንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መሆናቸውን አታይምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنَّهُمْ يَقُولُونَ مَا لَا يَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy226. እነርሱም የማይሰሩትን ነገር የሚናገሩ መሆናቸውን አታይምን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَذَكَرُوا۟ ٱللَّهَ كَثِيرًا وَٱنتَصَرُوا۟ مِنۢ بَعْدِ مَا ظُلِمُوا۟ وَسَيَعْلَمُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ أَىَّ مُنقَلَبٍ يَنقَلِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy227. እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ አላህን በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)። እነዚያም የበደሉ ከሞቱ በኋላ እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70