caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Naml النمل

93 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 48

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ طسٓ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْقُرْءَانِ وَكِتَابٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy1. ጣ፤ ሲን፤ ይህ ከቁርኣኑና ከገላጩ መጽሐፍ አናቅጽ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy2. ለምዕምናን መሪና ብስራት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلْـَٔاخِرَةِ هُمْ يُوقِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. ለእነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት፤ ዘካንም ለሚሰጡ፤ እነርሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነርሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ زَيَّنَّا لَهُمْ أَعْمَٰلَهُمْ فَهُمْ يَعْمَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ ክፉ ሥራዎቻቸውን ሸለምንላቸው:: ስለዚህ እነርሱ ይዋልላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَهُمْ سُوٓءُ ٱلْعَذَابِ وَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ هُمُ ٱلْأَخْسَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. እነርሱ እነዚያ ክፉ ቅጣት ያላባቸው ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ በጣም ከከሳሪዎቹ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّكَ لَتُلَقَّى ٱلْقُرْءَانَ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ عَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቁርኣንን ጥበበኛና አዋቂ ከሆነው ጌታህ ዘንድ በእርግጥ ትስሰጣለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِأَهْلِهِۦٓ إِنِّىٓ ءَانَسْتُ نَارًا سَـَٔاتِيكُم مِّنْهَا بِخَبَرٍ أَوْ ءَاتِيكُم بِشِهَابٍ قَبَسٍ لَّعَلَّكُمْ تَصْطَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለቤተሰቦቹ «እኔ እሳትን አየሁ ከእርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ፤ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኮሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ» ባለ ጊዜ የሆነውን አውሳላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَهَا نُودِىَ أَنۢ بُورِكَ مَن فِى ٱلنَّارِ وَمَنْ حَوْلَهَا وَسُبْحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy8. በመጣትም ጊዜ እንዲህ በማለት ተጠራ፡- «በእሳቲቱ ያለው ሰውና በዙሪያዋ ያሉም ሰዎች ሁሉ ተባረኩ:: የዓለማትም ጌታ አላህ ጥራት ይገባው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّهُۥٓ أَنَا ٱللَّهُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy9. «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊዉና ጥበበኛው (አምላክህ) አላህ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَلْقِ عَصَاكَ فَلَمَّا رَءَاهَا تَهْتَزُّ كَأَنَّهَا جَآنٌّ وَلَّىٰ مُدْبِرًا وَلَمْ يُعَقِّبْ يَٰمُوسَىٰ لَا تَخَفْ إِنِّى لَا يَخَافُ لَدَىَّ ٱلْمُرْسَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. «በትርህንም ጣል» (ተባለና ጣለም):: እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ፊቱን አዙሮ ሸሸ:: አልተመለሰምም:: «ሙሳ ሆይ! አትፍራ:: መልዕክተኞች እኔ ዘንድ ፈጽሞ አይፈሩምና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا مَن ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسْنًۢا بَعْدَ سُوٓءٍ فَإِنِّى غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy11. «ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ፤ አዛኝ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَدْخِلْ يَدَكَ فِى جَيْبِكَ تَخْرُجْ بَيْضَآءَ مِنْ غَيْرِ سُوٓءٍ فِى تِسْعِ ءَايَٰتٍ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَقَوْمِهِۦٓ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمًا فَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy12. «እጅህንም በአንገትየህ ውስጥ አስገባ ያለ ነውር (ወይም ያለ ለምጽ) ነጭ ሆና ትወጣለችና በዘጠኝ ታዐምራት ወደ ፈርዖንና ወደ ሕዝቦቹ ሂድ እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ናቸውና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَتْهُمْ ءَايَٰتُنَا مُبْصِرَةً قَالُوا۟ هَٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy13. ተዓምራታችንም ግልጽ ሆና በመጣቻቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَحَدُوا۟ بِهَا وَٱسْتَيْقَنَتْهَآ أَنفُسُهُمْ ظُلْمًا وَعُلُوًّا فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُفْسِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy14. ነፍሶቻቸዉም ያረጋገጧት ሲሆኑ ለበደልና ለኩራት በእርሷ ካዱ:: የአበላሾችም ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا دَاوُۥدَ وَسُلَيْمَٰنَ عِلْمًا وَقَالَا ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى فَضَّلَنَا عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّنْ عِبَادِهِ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy15. ለዳውድና ለሱለይማንም እውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው:: «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ለዚያ ከአማኞች ባሮቹ በብዙዎቹ ላይ ላበለጠን ይገባው።» አሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَوَرِثَ سُلَيْمَٰنُ دَاوُۥدَ وَقَالَ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ عُلِّمْنَا مَنطِقَ ٱلطَّيْرِ وَأُوتِينَا مِن كُلِّ شَىْءٍ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْفَضْلُ ٱلْمُبِينُ

Amharic Translation - Africa Academy16. ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ:: አለም «ሰዎች ሆይ የበራሪን ንግግር (የወፍን ቋንቋ) ተስተማርን ከነገሩም ሁሉ ተሰጠን ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የሆነ ችሮታ ነው።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَحُشِرَ لِسُلَيْمَٰنَ جُنُودُهُۥ مِنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ وَٱلطَّيْرِ فَهُمْ يُوزَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. ለሱለይማንም ከአጋንንት ከሰዉም ከበራሪም የሆኑት ሰራዊቶቹ ተሰበሰቡ:: እነርሱም ይከመከማሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَآ أَتَوْا۟ عَلَىٰ وَادِ ٱلنَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّمْلُ ٱدْخُلُوا۟ مَسَٰكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَٰنُ وَجُنُودُهُۥ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን፡- «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ:: ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ እንዳይሰባብሯችሁ።» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَبَسَّمَ ضَاحِكًا مِّن قَوْلِهَا وَقَالَ رَبِّ أَوْزِعْنِىٓ أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ ٱلَّتِىٓ أَنْعَمْتَ عَلَىَّ وَعَلَىٰ وَٰلِدَىَّ وَأَنْ أَعْمَلَ صَٰلِحًا تَرْضَىٰهُ وَأَدْخِلْنِى بِرَحْمَتِكَ فِى عِبَادِكَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy19. ከንግግርዋም እየሳቀ ጥርሱን ፈገግ አደረገ። «ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፤ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አስገባኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَفَقَّدَ ٱلطَّيْرَ فَقَالَ مَا لِىَ لَآ أَرَى ٱلْهُدْهُدَ أَمْ كَانَ مِنَ ٱلْغَآئِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy20. በራሪዎቹንም ተመለከተ:: ከዚያ «ሁድሁድን ለምን አላየሁትም! በእውነት ከራቁት ነበርን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَأُعَذِّبَنَّهُۥ عَذَابًا شَدِيدًا أَوْ لَأَا۟ذْبَحَنَّهُۥٓ أَوْ لَيَأْتِيَنِّى بِسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy21. «ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እቀጣዋለሁ:: ወይም በእርግጥ አርደዋለሁ:: ወይም ግልጽ የሆነ አስረጅን ያቀርብልኛል።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَكَثَ غَيْرَ بَعِيدٍ فَقَالَ أَحَطتُ بِمَا لَمْ تُحِطْ بِهِۦ وَجِئْتُكَ مِن سَبَإٍۭ بِنَبَإٍ يَقِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy22. (ሁድሁድ የተባለው ወፍ) እሩቅ ያልሆነንም ጊዜ ቆየ:: ከዚያም አለ «ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّى وَجَدتُّ ٱمْرَأَةً تَمْلِكُهُمْ وَأُوتِيَتْ مِن كُلِّ شَىْءٍ وَلَهَا عَرْشٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy23. «እኔ የምትገዛቸው የሆነችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ:: ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አላት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَدتُّهَا وَقَوْمَهَا يَسْجُدُونَ لِلشَّمْسِ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ أَعْمَٰلَهُمْ فَصَدَّهُمْ عَنِ ٱلسَّبِيلِ فَهُمْ لَا يَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy24. «እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለጸሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው። ሰይጣንም ለእነርሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል። ከእውነተኛዉም መንገድ አግዷቸዋል:: ስለዚህ እነርሱ ወደ እውነት አይመሩም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَّا يَسْجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِى يُخْرِجُ ٱلْخَبْءَ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُخْفُونَ وَمَا تُعْلِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. «ለዚያም በሰማያትና በምድር ዉስጥ የተደበቀውን ለሚያወጣው የምትሸሽጉትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ ሰይጣን አግዷቸዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلْعَرْشِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy26. «አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» (አለ) {1}

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ سَنَنظُرُ أَصَدَقْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْكَٰذِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy27. ሱለይማንም አለ፡- «እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደሆንክ ወደ ፊት እናያለን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱذْهَب بِّكِتَٰبِى هَٰذَا فَأَلْقِهْ إِلَيْهِمْ ثُمَّ تَوَلَّ عَنْهُمْ فَٱنظُرْ مَاذَا يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. «ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ሂድ:: ወደ እነርሱም ጣለው ከዚያ ከእነርሱ ዘወር በልና ምን እንደሚመልሱም ተመልከት።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَتْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْمَلَؤُا۟ إِنِّىٓ أُلْقِىَ إِلَىَّ كِتَٰبٌ كَرِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy29. እርሷም በደረሳት ጊዜ አለች፡- «እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሑፍ ወደ እኔ ተጣለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ مِن سُلَيْمَٰنَ وَإِنَّهُۥ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy30. «እርሱ ከሱለይማን ነው። እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَّا تَعْلُوا۟ عَلَىَّ وَأْتُونِى مُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. «‹በእኔ ላይ አትኩሩ:: ታዛዦችም ሆናችሁ ወደ እኔ ኑ› የሚል ነው።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَتْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْمَلَؤُا۟ أَفْتُونِى فِىٓ أَمْرِى مَا كُنتُ قَاطِعَةً أَمْرًا حَتَّىٰ تَشْهَدُونِ

Amharic Translation - Africa Academy32. «እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ የሚበጀውን ንገሩኝ እስከምትነግሩኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ نَحْنُ أُو۟لُوا۟ قُوَّةٍ وَأُو۟لُوا۟ بَأْسٍ شَدِيدٍ وَٱلْأَمْرُ إِلَيْكِ فَٱنظُرِى مَاذَا تَأْمُرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy33. «እኛ የሃይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን:: ግን ትዕዛዙ ከወደ አንቺ ብቻ ነው። ምን እንደምታዝዢንም አስተውይ» አሏት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَتْ إِنَّ ٱلْمُلُوكَ إِذَا دَخَلُوا۟ قَرْيَةً أَفْسَدُوهَا وَجَعَلُوٓا۟ أَعِزَّةَ أَهْلِهَآ أَذِلَّةً وَكَذَٰلِكَ يَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. እርሷም አለች፡- «ንጉሶች ከተማን በሃይል በገቡባት ጊዜ ያበላሿታል የተከበሩ ሰዎቿንም ወራዶች ያደርጋሉ:: ልክ እንደዚሁ ነው የሚያደርጉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنِّى مُرْسِلَةٌ إِلَيْهِم بِهَدِيَّةٍ فَنَاظِرَةٌۢ بِمَ يَرْجِعُ ٱلْمُرْسَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. «እኔም ወደ እነርሱ ገጸበረከትን የምልክና መልዕክተኞቹ በምን እንደሚመልሱ የምጠባበቅ ነኝ።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَ سُلَيْمَٰنَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٍ فَمَآ ءَاتَىٰنِۦَ ٱللَّهُ خَيْرٌ مِّمَّآ ءَاتَىٰكُم بَلْ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمْ تَفْرَحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. መልዕክተኛው ሱለይማንን በመጣውም ጊዜ አለ፡- «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን? አላህም የሰጠን ከሰጣችሁ የበለጠ ነው:: ይልቁንም እናንተ በገጸበረከታችሁ ትደሰታላችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱرْجِعْ إِلَيْهِمْ فَلَنَأْتِيَنَّهُم بِجُنُودٍ لَّا قِبَلَ لَهُم بِهَا وَلَنُخْرِجَنَّهُم مِّنْهَآ أَذِلَّةً وَهُمْ صَٰغِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy37. «ወደ እነርሱ ተመለስ:: ለእነርሱም በእርሷ ችሎታ በሌላቸው ሰራዊት እንመጣባቸዋለን:: ከእርሷም እነርሱ የተዋረዱ ሆነው በእርግጥ እናወጣቸዋለን።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْمَلَؤُا۟ أَيُّكُمْ يَأْتِينِى بِعَرْشِهَا قَبْلَ أَن يَأْتُونِى مُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy38. «እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ሙስሊሞች ሆነው ወደ እኔ ሳይመጡ በፊት ዙፋኗን የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው?» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ عِفْرِيتٌ مِّنَ ٱلْجِنِّ أَنَا۠ ءَاتِيكَ بِهِۦ قَبْلَ أَن تَقُومَ مِن مَّقَامِكَ وَإِنِّى عَلَيْهِ لَقَوِىٌّ أَمِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy39. ከጋኔን ሃይለኛው «ከችሎትህ ከመነሳትህ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ:: እኔም በእርሱ ላይ ብርቱ ታማኝ ነኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ ٱلَّذِى عِندَهُۥ عِلْمٌ مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ أَنَا۠ ءَاتِيكَ بِهِۦ قَبْلَ أَن يَرْتَدَّ إِلَيْكَ طَرْفُكَ فَلَمَّا رَءَاهُ مُسْتَقِرًّا عِندَهُۥ قَالَ هَٰذَا مِن فَضْلِ رَبِّى لِيَبْلُوَنِىٓ ءَأَشْكُرُ أَمْ أَكْفُرُ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِۦ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّى غَنِىٌّ كَرِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy40. ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው «የተገለጸው ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ።» አለ:: እንደዚሁም አደረገ:: እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየዉም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው። የማመሰግን ወይም የምክድ መሆኔን ሊሞክረኝ ቸረልኝ:: አላህን ያመሰገነ ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ነው:: አላህን የካደም ሰው ሁሉ ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ፤ ቸር ነው።» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ نَكِّرُوا۟ لَهَا عَرْشَهَا نَنظُرْ أَتَهْتَدِىٓ أَمْ تَكُونُ مِنَ ٱلَّذِينَ لَا يَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy41. «ዙፋኗን ለእርሷ አሳስቱ ታውቀው እንደሆነ ወይም ከእነዚያ ከማያውቁት ትሆን እንደሆነ እናያለን።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَتْ قِيلَ أَهَٰكَذَا عَرْشُكِ قَالَتْ كَأَنَّهُۥ هُوَ وَأُوتِينَا ٱلْعِلْمَ مِن قَبْلِهَا وَكُنَّا مُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy42. በመጣችም ጊዜ፡- «ዙፋንሽ እንደዚህ ነውን?» ተባለች «እርሱ ልክ እርሱን ነው የመሰለኝ።» አለች። ሱለይማንም አለ: «ከእርሷ በፊትም እውቀትን ተሰጠን:: ሙስሊሞችም ነበርን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَصَدَّهَا مَا كَانَت تَّعْبُدُ مِن دُونِ ٱللَّهِ إِنَّهَا كَانَتْ مِن قَوْمٍ كَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy43. «ከአላህ ሌላ ትገዛው የነበረችውንም ከለከላት:: እርሷ ከከሓዲያን ሕዝቦች ነበረችና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قِيلَ لَهَا ٱدْخُلِى ٱلصَّرْحَ فَلَمَّا رَأَتْهُ حَسِبَتْهُ لُجَّةً وَكَشَفَتْ عَن سَاقَيْهَا قَالَ إِنَّهُۥ صَرْحٌ مُّمَرَّدٌ مِّن قَوَارِيرَ قَالَتْ رَبِّ إِنِّى ظَلَمْتُ نَفْسِى وَأَسْلَمْتُ مَعَ سُلَيْمَٰنَ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy44. «ሕንጻውን ግቢ።» ተባለች:: ባየችዉም ጊዜ ባህር ነው ብላ ጠረጠረችው:: ከባቶቿም ገለጠች:: «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ህንጻ ነው።» አሏት:: «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩኝ።» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَآ إِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَٰلِحًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ فَإِذَا هُمْ فَرِيقَانِ يَخْتَصِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy45. ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን አላህን ተገዙ በማለት በእርግጥ ላክነው:: ወዲያዉም እነርሱ የሚነታረኩ ሁለት ቡድኖች ሆኑ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ يَٰقَوْمِ لِمَ تَسْتَعْجِلُونَ بِٱلسَّيِّئَةِ قَبْلَ ٱلْحَسَنَةِ لَوْلَا تَسْتَغْفِرُونَ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy46. «ሕዝቦቼ ሆይ! ከመልካሙ በፊት በክፉው ቅጣትን አምጣብን በማለት ለምን ታስቸኩላላችሁ ይታዘንላችሁ ዘንድ አላህን ምህረትን አትለምኑምን?» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ ٱطَّيَّرْنَا بِكَ وَبِمَن مَّعَكَ قَالَ طَٰٓئِرُكُمْ عِندَ ٱللَّهِ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ تُفْتَنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy47. «ባንተና ካንተም ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደ ቢሶች ሆንን።» አሉት:: «ገደ ቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው:: ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَانَ فِى ٱلْمَدِينَةِ تِسْعَةُ رَهْطٍ يُفْسِدُونَ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا يُصْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. በከተማይቱም ውስጥ ምድርን የሚያበላሹና የማያሳምሩ ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ تَقَاسَمُوا۟ بِٱللَّهِ لَنُبَيِّتَنَّهُۥ وَأَهْلَهُۥ ثُمَّ لَنَقُولَنَّ لِوَلِيِّهِۦ مَا شَهِدْنَا مَهْلِكَ أَهْلِهِۦ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. ዘጠኞቹም «እርሱንና ቤተሰቦቹን ሌሊት እንግደልና ከዚያም ለዘመዱ የቤተሰቦቹን መገደል አላየንም:: እኛም እውነተኞች ነን ልንል በአላህ እንማማል።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَكَرُوا۟ مَكْرًا وَمَكَرْنَا مَكْرًا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50. ተንኮልንም መከሩ:: እነርሱም የማያውቁ ሲሆኑ በተንኮላቸው ምክኒያት አጠፋናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ مَكْرِهِمْ أَنَّا دَمَّرْنَٰهُمْ وَقَوْمَهُمْ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተንኮላቸዉም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ እኛ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም በሙሉ እንዴት እንዳጠፋናቸው ተመልከት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتِلْكَ بُيُوتُهُمْ خَاوِيَةًۢ بِمَا ظَلَمُوٓا۟ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy52. እንዚህም በበደላቸው ምክንያት ባዶዎች ሲሆኑ እነዚህም ቤቶቻቸው ናቸው:: በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አስደናቂ ተዐምር አለበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنجَيْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ يَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. እነዚያንም ያመኑትንና ከክህደት ይጠነቀቁ የነበሩትን አዳንን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَٰحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥንም ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ):: «እናንተ የምታዩ ስትሆኑ መጥፎን ነገር ትሠራላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy55. «እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን? በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓا۟ أَخْرِجُوٓا۟ ءَالَ لُوطٍ مِّن قَرْيَتِكُمْ إِنَّهُمْ أُنَاسٌ يَتَطَهَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy56. የህዝቦቹም መልስ «የሉጥን ቤተሰቦች ከከተማችሁ አውጡ:: እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَنجَيْنَٰهُ وَأَهْلَهُۥٓ إِلَّا ٱمْرَأَتَهُۥ قَدَّرْنَٰهَا مِنَ ٱلْغَٰبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy57. እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንን:: ሚስቱ ብቻ ስትቀር:: እርሷማ በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ አደረግናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا فَسَآءَ مَطَرُ ٱلْمُنذَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy58. በእነርሱም ላይ የድንጋይ ዝናብን አዘነብንባቸው:: የተስፈራሪዎቹም የቅጣት ዝናብ ከፋ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ وَسَلَٰمٌ عَلَىٰ عِبَادِهِ ٱلَّذِينَ ٱصْطَفَىٰٓ ءَآللَّهُ خَيْرٌ أَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሁልጊዜም ሰላም ይውረድ:: አላህ በላጭ ነውን? ወይስ ያ በእርሱ የሚያጋሩት ጣዖት?» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَنۢبَتْنَا بِهِۦ حَدَآئِقَ ذَاتَ بَهْجَةٍ مَّا كَانَ لَكُمْ أَن تُنۢبِتُوا۟ شَجَرَهَآ أَءِلَٰهٌ مَّعَ ٱللَّهِ بَلْ هُمْ قَوْمٌ يَعْدِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy60. ወይስ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው ማን ሆነና? በእርሱም ባለ ውበት የሆኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለእናንተ ችሎታ ሳይኖራችሁ እኛ ብቻችንን አበቀልን:: ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም) ግን እነርሱ ከእውነት የሚያዘነብሉ ህዝቦች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَّن جَعَلَ ٱلْأَرْضَ قَرَارًا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنْهَٰرًا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِىَ وَجَعَلَ بَيْنَ ٱلْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا أَءِلَٰهٌ مَّعَ ٱللَّهِ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. ወይስ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ ለእርሷም ጋራዎችን ያደረገ በጣፋጩና በጨዋማው በሁለቱ ባህሮችም መካከል ግርዶን ያደረገ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَّن يُجِيبُ ٱلْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ ٱلسُّوٓءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَآءَ ٱلْأَرْضِ أَءِلَٰهٌ مَّعَ ٱللَّهِ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy62. ወይስ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚደርጋችሁ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሰጹም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَّن يَهْدِيكُمْ فِى ظُلُمَٰتِ ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ وَمَن يُرْسِلُ ٱلرِّيَٰحَ بُشْرًۢا بَيْنَ يَدَىْ رَحْمَتِهِۦٓ أَءِلَٰهٌ مَّعَ ٱللَّهِ تَعَٰلَى ٱللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy63. ወይስ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ንፋሶችንም ከዝናቡ በፊት አብሳሪ ሆነው የሚልክ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? አላህ በእርሱ ከሚያጋሯቸው ነገሮች ሁሉ ላቀ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَّن يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَمَن يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ أَءِلَٰهٌ مَّعَ ٱللَّهِ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy64. ወይስ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው፤ ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣቸሁ አምላክ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? እውነተኞች እንደሆናችሁ አስረጃችሁን አምጡ በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ٱلْغَيْبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም:: አላህ ግን ያውቀዋል:: መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلِ ٱدَّٰرَكَ عِلْمُهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ بَلْ هُمْ فِى شَكٍّ مِّنْهَا بَلْ هُم مِّنْهَا عَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy66. በእውነት የመጨረሻይቱን ዓለም ሁኔታ ማወቃቸው ተሟላን? አይደለም። እነርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእውነትም እነርሱ ከእርሷ እውሮች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَءِذَا كُنَّا تُرَٰبًا وَءَابَآؤُنَآ أَئِنَّا لَمُخْرَجُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ፡- «እኛም አባቶቻችንም ዐፈር በሆንን ጊዜ እንደ ገና ከመቃብር የምንወጣ ነን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ وُعِدْنَا هَٰذَا نَحْنُ وَءَابَآؤُنَا مِن قَبْلُ إِنْ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy68. «ይህንን እኛም ሆነ ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረንበታል:: ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ سِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُجْرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ የአመጸኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልክቱ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَحْزَنْ عَلَيْهِمْ وَلَا تَكُن فِى ضَيْقٍ مِّمَّا يَمْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም ላይ አትዘን:: ከሚመክሩብህም ነገር በጭንቀት ውስጥ አትሁን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy71. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ رَدِفَ لَكُم بَعْضُ ٱلَّذِى تَسْتَعْجِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የዚያ የምትቻኮሉበት ከፊሉ ለእናንተ የቀረበ መሆኑ ተረጋግጧል።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነው:: ግን አብዛኛዎቻቸው አያመሰግኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَعْلَمُ مَا تُكِنُّ صُدُورُهُمْ وَمَا يُعْلِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ያውቃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا مِنْ غَآئِبَةٍ فِى ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ إِلَّا فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy75. በሰማይም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም:: ገላጭ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانَ يَقُصُّ عَلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ أَكْثَرَ ٱلَّذِى هُمْ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy76. ይህ ቁርኣን እነዚያ የኢስራኢል ልጆች እነርሱ በእርሱ ላይ የሚለያዩበትን ጉዳይ አብዛኛውን ይነግራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُۥ لَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy77. እርሱም ለአማኞች ብቸኛ መምሪያና እዝነት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِى بَيْنَهُم بِحُكْمِهِۦ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy78. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፤ እርሱም ሁሉን አሸናፊዉና አዋቂው ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ إِنَّكَ عَلَى ٱلْحَقِّ ٱلْمُبِينِ

Amharic Translation - Africa Academy79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህም ላይ ተጠጋ:: አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّكَ لَا تُسْمِعُ ٱلْمَوْتَىٰ وَلَا تُسْمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوْا۟ مُدْبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ሙታንን አታሰማም። ደንቆሮዎችንም የሚተው ሆነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَنتَ بِهَٰدِى ٱلْعُمْىِ عَن ضَلَٰلَتِهِمْ إِن تُسْمِعُ إِلَّا مَن يُؤْمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُم مُّسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy81.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ልበ ዕውሮችን ከጥመታቸው አቅኚ አይደለህም:: እነዚያን በአናቅጻችን በትክክል የሚያምኑትን እንጂ አታሰማም:: እነርሱ ፍጹም ታዛዦች (ሙስሊሞች) ናቸውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا وَقَعَ ٱلْقَوْلُ عَلَيْهِمْ أَخْرَجْنَا لَهُمْ دَآبَّةً مِّنَ ٱلْأَرْضِ تُكَلِّمُهُمْ أَنَّ ٱلنَّاسَ كَانُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا لَا يُوقِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. በእነርሱም ላይ የቅጣት ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአናቅጻችን የማያረጋግጡ እንደነበሩ የምትነግራቸውን እንስሳ ለእነርሱ ከምድር እናወጣላቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ نَحْشُرُ مِن كُلِّ أُمَّةٍ فَوْجًا مِّمَّن يُكَذِّبُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُمْ يُوزَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦቹም ሁሉ በአናቅጽ የሚያስተባብሉትን ቡድኖች የምንሰበስብበትን ቀን አስታውስ:: እነርሱም ይከመከማሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُو قَالَ أَكَذَّبْتُم بِـَٔايَٰتِى وَلَمْ تُحِيطُوا۟ بِهَا عِلْمًا أَمَّاذَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy84. በመጡም ጊዜ (አላህ) ይላቸዋል፡ «በአንቀጾቼ እርሷን በማወቅ ያላዳረሳችሁ ስትሆኑ አስተባበላችሁን? ወይስ ምንን ትሰሩ ነበራችሁ?»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَوَقَعَ ٱلْقَوْلُ عَلَيْهِم بِمَا ظَلَمُوا۟ فَهُمْ لَا يَنطِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy85. በመበደላቸዉም ምክኒያት በእነርሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል:: እነርሱም አይናገሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا جَعَلْنَا ٱلَّيْلَ لِيَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy86. እኛ ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንደሚያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን? ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ አያሌ ተዓምራት አሉበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ يُنفَخُ فِى ٱلصُّورِ فَفَزِعَ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا مَن شَآءَ ٱللَّهُ وَكُلٌّ أَتَوْهُ دَٰخِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉትና በምድርም ውስጥ ያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። ሁሉም የተናነሱ ሆነዉም ወደ እርሱ ይመጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَرَى ٱلْجِبَالَ تَحْسَبُهَا جَامِدَةً وَهِىَ تَمُرُّ مَرَّ ٱلسَّحَابِ صُنْعَ ٱللَّهِ ٱلَّذِىٓ أَتْقَنَ كُلَّ شَىْءٍ إِنَّهُۥ خَبِيرٌۢ بِمَا تَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy88. ጋራዎችንም እርሷ እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትሆን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያለህ፤ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት:: እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَن جَآءَ بِٱلْحَسَنَةِ فَلَهُۥ خَيْرٌ مِّنْهَا وَهُم مِّن فَزَعٍ يَوْمَئِذٍ ءَامِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy89. መልካም ሥራን የሰራ ለእርሱ ከእርሷ የበለጠ ምንዳ አለው:: እነርሱም በዚያ ቀን ከድንጋጤ ነፃ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَكُبَّتْ وُجُوهُهُمْ فِى ٱلنَّارِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy90. መጥፎንም የሰሩ ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ። «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጂ አትመነዱም» ይበላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَآ أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ رَبَّ هَٰذِهِ ٱلْبَلْدَةِ ٱلَّذِى حَرَّمَهَا وَلَهُۥ كُلُّ شَىْءٍ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy91. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! በላቸው:) «የታዘዝኩት የዚህችን አገር የመካን ጌታ ያንን ክልክል ያደረጋትንም አላህን እንድገዛ ብቻ ነው:: ነገሩም ሁሉ የእርሱ ነው:: ከሙስሊሞችም እንድሆን ታዝዣለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنْ أَتْلُوَا۟ ٱلْقُرْءَانَ فَمَنِ ٱهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِى لِنَفْسِهِۦ وَمَن ضَلَّ فَقُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلْمُنذِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy92. «ቁርኣንንም እንዳነብ ታዝዣለሁ:: በቀጥተኛው መንገድ የተመራ ሁሉ የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው:: የተሳሳተም እኔ ከአስፈራሪዎች ነኝ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقُلِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ ءَايَٰتِهِۦ فَتَعْرِفُونَهَا وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው:: ተአምራቱን ወደ ፊት ያሳያችኋል:: ታውቋታላችሁም።» በላቸው:: ጌታህ ከምትሠሩት ነገር ሁሉ ዘንጊ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70