caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Furqaan الفرقان

77 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 42

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy1. ያ ፉርቃንን (እውነትን ከውሸት የሚለየውን) ቁርኣን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብሩ ላቀ (ጥራት ተገባው)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَلَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ شَرِيكٌ فِى ٱلْمُلْكِ وَخَلَقَ كُلَّ شَىْءٍ فَقَدَّرَهُۥ تَقْدِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ ያ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ የሆነ፤ ልጅንም ያልያዘ (ልጅም የሌለው)፤ በንግስናዉም ተጋሪ የሌለው፤ ሁሉንም ነገር የፈጠረና በትክክልም (በስርአት) የመጠነው አምላክ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً لَّا يَخْلُقُونَ شَيْـًٔا وَهُمْ يُخْلَقُونَ وَلَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ ضَرًّا وَلَا نَفْعًا وَلَا يَمْلِكُونَ مَوْتًا وَلَا حَيَوٰةً وَلَا نُشُورًا

Amharic Translation - Africa Academy3. ከሓዲያን ከእርሱ ከአላህ ሌላ ምንንም የማይፈጥሩንና እነርሱ ራሳቸው የሚፈጠሩ፤ ለነፍሶቻቸዉም (ከራሳቸው ላይ) ጉዳትን መከላከልም ሆነ ለራሳቸው ጥቅምን ማምጣት (ማስከበር) የማይችሉ፤ ለሞት ማብቃትም ሆነ ህይወትን መለገስና ከሞት መቀስቀስንም የማይችሉን አማልክትን አምላክ አድርገው ያዙ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّآ إِفْكٌ ٱفْتَرَىٰهُ وَأَعَانَهُۥ عَلَيْهِ قَوْمٌ ءَاخَرُونَ فَقَدْ جَآءُو ظُلْمًا وَزُورًا

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን እርሱ (ሙሐመድ) በራሱ የቀጠፈውና በእርሱም ላይ ሌሎች ህዝቦች ያገዙት ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ። በእርግጥም በደልንና እብለትን ፈጸሙ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوٓا۟ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ ٱكْتَتَبَهَا فَهِىَ تُمْلَىٰ عَلَيْهِ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy5. «እነዚህ የመጀመሪያ ሰዎች ተረቶች (አፈታሪክ) ናቸው። አስጽፎታል፤ እናም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ أَنزَلَهُ ٱلَّذِى يَعْلَمُ ٱلسِّرَّ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ إِنَّهُۥ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው:: እርሱ መሓሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ مَالِ هَٰذَا ٱلرَّسُولِ يَأْكُلُ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشِى فِى ٱلْأَسْوَاقِ لَوْلَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكٌ فَيَكُونَ مَعَهُۥ نَذِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy7. አሉም: «ይህ መልዕክተኛ ምን አይነት መልዕክተኛ ነው? ምግብ የሚመገብ ወደ ገበያ የሚመላለስ፤ ከእርሱ ጋር አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ወደ እርሱ መልአክ (በገሃድ) አይወረድም ኖሯልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يُلْقَىٰٓ إِلَيْهِ كَنزٌ أَوْ تَكُونُ لَهُۥ جَنَّةٌ يَأْكُلُ مِنْهَا وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًا مَّسْحُورًا

Amharic Translation - Africa Academy8. «ወይም ወደ እርሱ ድልብ አይሰጠዉምን? ወይም ከእርሷ የሚበላባት አትክልት ለእርሱ አትኖረዉምን?» አሉ። «በዳዮችም ላመኑት የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላን አትከተሉም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱنظُرْ كَيْفَ ضَرَبُوا۟ لَكَ ٱلْأَمْثَٰلَ فَضَلُّوا۟ فَلَا يَسْتَطِيعُونَ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy9.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና ከዚያም እንዴት እንደ ተሳሳቱ ተመልከት:: ወደ እውነት ለመድረስ መንገድንም አይችሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَبَارَكَ ٱلَّذِىٓ إِن شَآءَ جَعَلَ لَكَ خَيْرًا مِّن ذَٰلِكَ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ وَيَجْعَل لَّكَ قُصُورًۢا

Amharic Translation - Africa Academy10. ያ ቢሻ ከዚህ ካሉት የተሻለን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አትክልት ስፍራዎችን ላንተ የሚያደርግልህ ህንጻ ቤቶችንም የሚያደርግልህ የሆነው ጌታ ችሮታው በዛ:: (ክብሩ ላቀ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ كَذَّبُوا۟ بِٱلسَّاعَةِ وَأَعْتَدْنَا لِمَن كَذَّبَ بِٱلسَّاعَةِ سَعِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy11. ይልቁንም እነርሱ በትንሳኤ አስተባበሉ:: በትንሳኤ ላስተባበለም ሁሉ አቃጣይ እሳት አዘጋጅተናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذَا رَأَتْهُم مِّن مَّكَانٍۭ بَعِيدٍ سَمِعُوا۟ لَهَا تَغَيُّظًا وَزَفِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy12. ከሩቅ ስፍራ ባየቻቸው ጊዜ የእርሷን የቁጭት መገንፈልንና ማናፋትን ይሰማሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَآ أُلْقُوا۟ مِنْهَا مَكَانًا ضَيِّقًا مُّقَرَّنِينَ دَعَوْا۟ هُنَالِكَ ثُبُورًا

Amharic Translation - Africa Academy13. ከጓደኞቻቸው ጋር (ከሰይጣኖቻቸው ጋር) በአንድ የታሰሩ ሆነዉም ከእርሷ በጠባብ ስፍራ በተጣሉ ጊዜ በዚያ ስፍራ ጥፋትን ይጠራሉ:: (ዋ ጥፋታችን! ይላሉ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا تَدْعُوا۟ ٱلْيَوْمَ ثُبُورًا وَٰحِدًا وَٱدْعُوا۟ ثُبُورًا كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy14. ዛሬማ አንድን ጥፋት ብቻ አትጥሩ:: ይልቁንም ብዙን ጥፋት ጥሩ ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ أَذَٰلِكَ خَيْرٌ أَمْ جَنَّةُ ٱلْخُلْدِ ٱلَّتِى وُعِدَ ٱلْمُتَّقُونَ كَانَتْ لَهُمْ جَزَآءً وَمَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «ይህ የተሻለ ነውን? ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጡት የዘልዓለሟ ገነት?» ገነት ለእነርሱ ምንዳና መመለሻ ሆነች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّهُمْ فِيهَا مَا يَشَآءُونَ خَٰلِدِينَ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ وَعْدًا مَّسْـُٔولًا

Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ተስፋ ከጌታህ ሊለመን የሚገባው ተስፋ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَقُولُ ءَأَنتُمْ أَضْلَلْتُمْ عِبَادِى هَٰٓؤُلَآءِ أَمْ هُمْ ضَلُّوا۟ ٱلسَّبِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy17. እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን የሚሰበስብበትንና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን? ወይስ እነርሱው እራሳቸው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ سُبْحَٰنَكَ مَا كَانَ يَنۢبَغِى لَنَآ أَن نَّتَّخِذَ مِن دُونِكَ مِنْ أَوْلِيَآءَ وَلَٰكِن مَّتَّعْتَهُمْ وَءَابَآءَهُمْ حَتَّىٰ نَسُوا۟ ٱلذِّكْرَ وَكَانُوا۟ قَوْمًۢا بُورًا

Amharic Translation - Africa Academy18. (ተመላኪዎቹም): «አላህ ሆይ! ጥራት ይገባህ:: ከአንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ አይገባንም:: ግን እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን መገንዘብን እስከ ተውና ጠፊ ህዝቦችም እስከሚሆኑ ድረስ አጣቀምካቸው።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَدْ كَذَّبُوكُم بِمَا تَقُولُونَ فَمَا تَسْتَطِيعُونَ صَرْفًا وَلَا نَصْرًا وَمَن يَظْلِم مِّنكُمْ نُذِقْهُ عَذَابًا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy19. በምትሉትም አማልክቶቻችሁ አስዋሹዋችሁ:: ቅጣቴን መገፍተርንም ሆነ እራሳችሁን መርዳት አትችሉም:: ከናንተም የሚበድልን ሰው ታላቅን ቅጣት እናቀምሰዋለን:: (ይባላሉ።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّآ إِنَّهُمْ لَيَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشُونَ فِى ٱلْأَسْوَاقِ وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም ከመልዕክተኞች እነርሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚሄዱ ሆነው እንጂ አላክንም:: ከፊላችሁንም ለከፊሉ ፈተና አድርገናል:: ትታገሳላችሁን? ጌታህም ተመልካች ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ نَرَىٰ رَبَّنَا لَقَدِ ٱسْتَكْبَرُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ وَعَتَوْ عُتُوًّا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy21. እነዚያ መገናኘታችንን የማይጠብቁ ሰዎች «በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም ወይም ጌታችንን ለምን አናይም?» አሉ። በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ። ታላቅንም አመጽ አመጹ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يَرَوْنَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ لَا بُشْرَىٰ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُجْرِمِينَ وَيَقُولُونَ حِجْرًا مَّحْجُورًا

Amharic Translation - Africa Academy22. መላዕክትን በሚያዩበት ቀን በዚያ ጊዜ ለአመጸኞች የምስራች የላቸዉም። (መላዕክቱም) «የተከለከለ ክልክል» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَدِمْنَآ إِلَىٰ مَا عَمِلُوا۟ مِنْ عَمَلٍ فَجَعَلْنَٰهُ هَبَآءً مَّنثُورًا

Amharic Translation - Africa Academy23. ወደ ሰሩት ስራም እናስባለን:: ከዚያም እንደ ተበተነ ትቢያ እናደርገዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ يَوْمَئِذٍ خَيْرٌ مُّسْتَقَرًّا وَأَحْسَنُ مَقِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy24. የገነት ሰዎች በዚያ ቀን በመርጊያ የተሻሉ በማረፊያም በጣም ያማሩ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ تَشَقَّقُ ٱلسَّمَآءُ بِٱلْغَمَٰمِ وَنُزِّلَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ تَنزِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማይ በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መውረድን የሚወርዱበትን ቀን አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ ٱلْحَقُّ لِلرَّحْمَٰنِ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ عَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy26. እውነተኛው ንግስና በዚያ ቀን ለአር-ረህማን ብቻ ነው:: በከሓዲያን ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ يَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ يَدَيْهِ يَقُولُ يَٰلَيْتَنِى ٱتَّخَذْتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዳይም «ዋ ምኞቴ! ከመልዕክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ምነው ይዤ በሆነ፤ እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆችን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy28. «ዋ ጥፋቴ! እገሌን በወዳጅነት ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ أَضَلَّنِى عَنِ ٱلذِّكْرِ بَعْدَ إِذْ جَآءَنِى وَكَانَ ٱلشَّيْطَٰنُ لِلْإِنسَٰنِ خَذُولًا

Amharic Translation - Africa Academy29. (የእምነት ቃል የሆነው) «ቁርኣን ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ።» ይላል:: ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلرَّسُولُ يَٰرَبِّ إِنَّ قَوْمِى ٱتَّخَذُوا۟ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانَ مَهْجُورًا

Amharic Translation - Africa Academy30. መልዕክተኛዉም (ሙሐመድ) «ጌታዬ ሆይ! ህዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አደረጉት።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِىٍّ عَدُوًّا مِّنَ ٱلْمُجْرِمِينَ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ هَادِيًا وَنَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy31. ልክ እንደዚሁም ለነብያቱ ሁሉ ከአመጸኞች የሆነ ጠላትን አድርገናል:: መሪነትና ረዳትነት በጌታህ በቃ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ ٱلْقُرْءَانُ جُمْلَةً وَٰحِدَةً كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِۦ فُؤَادَكَ وَرَتَّلْنَٰهُ تَرْتِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy32. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችም «ቁርኣንን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ በአንድ ጊዜ አልተወረደለትም።» አሉ። ልክ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ (ከፋፍለን በተለያየ አወረድነው):: ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየትኛዉም ጥያቄ አይመጡብህም እውነተኛውን መልስና መልካም ፍቹንም የምናመጣልህ ብንሆን እንጅ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُحْشَرُونَ عَلَىٰ وُجُوهِهِمْ إِلَىٰ جَهَنَّمَ أُو۟لَٰٓئِكَ شَرٌّ مَّكَانًا وَأَضَلُّ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy34. እነዚያ በፊቶቻቻው ላይ እየተጎተቱ ወደ ገሀነም የሚሰበሰቡት እነዚያ ስፍራቸው የከፋ መንገዳቸዉም የጠመመ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ وَجَعَلْنَا مَعَهُۥٓ أَخَاهُ هَٰرُونَ وَزِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy35. በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው:: ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقُلْنَا ٱذْهَبَآ إِلَى ٱلْقَوْمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَدَمَّرْنَٰهُمْ تَدْمِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy36. «ወደ እነዚያም በተዓምራታችን ወደ አስተባበሉት ህዝቦች ሂዱ።» አልናቸው። (አስዋሿቸዉም) ማጥፋትንም አጠፋናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَوْمَ نُوحٍ لَّمَّا كَذَّبُوا۟ ٱلرُّسُلَ أَغْرَقْنَٰهُمْ وَجَعَلْنَٰهُمْ لِلنَّاسِ ءَايَةً وَأَعْتَدْنَا لِلظَّٰلِمِينَ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy37. የኑህን ሰዎችም መልዕክተኞችን ባስተባበሉ ጊዜ አሰመጥናቸው:: ለሰዎችም መገሰጫ አደረግናቸው፤ ለበደለኞችም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَادًا وَثَمُودَا۟ وَأَصْحَٰبَ ٱلرَّسِّ وَقُرُونًۢا بَيْنَ ذَٰلِكَ كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy38. ዓድንም፤ሰሙድንም፤ የረስ ሰዎችንና በዚህ መካከል የነበሩትንም ብዙ የክፍለ ዘመናት ህዝቦችንም አጠፋን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكُلًّا ضَرَبْنَا لَهُ ٱلْأَمْثَٰلَ وَكُلًّا تَبَّرْنَا تَتْبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy39. ሁሉንም (ገሠጽን):: ለእነርሱ ምሳሌዎችን ገለጽን:: ሁሉንም ማጥፋትን አጠፋናቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَتَوْا۟ عَلَى ٱلْقَرْيَةِ ٱلَّتِىٓ أُمْطِرَتْ مَطَرَ ٱلسَّوْءِ أَفَلَمْ يَكُونُوا۟ يَرَوْنَهَا بَلْ كَانُوا۟ لَا يَرْجُونَ نُشُورًا

Amharic Translation - Africa Academy40. በዚያችም ክፉ ዝናብን በተዘነበችው ከተማ ላይ (የመካ ከሓዲያን) በእርግጥ መጥተዋል:: የሚያዩዋት አልነበሩምን? በእውነቱ መቀስቀስን የማይፈሩ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا رَأَوْكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِى بَعَثَ ٱللَّهُ رَسُولًا

Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባዩህም ጊዜ (እንዲህ) እያሉ መሳለቂያ እንጅ ሌላ አያደርጉህም: «ያ አላህ መልዕክተኛ እድርጎ የላከው ይህ ነውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن كَادَ لَيُضِلُّنَا عَنْ ءَالِهَتِنَا لَوْلَآ أَن صَبَرْنَا عَلَيْهَا وَسَوْفَ يَعْلَمُونَ حِينَ يَرَوْنَ ٱلْعَذَابَ مَنْ أَضَلُّ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy42. «እነሆ በእርሷ ላይ መታገሳችን (ጽናታችን) ባልነበረ ኖሮ ከአማልክቶቻችን ሊያሳስተን ቀርቦ ነበር።» ሲሉም ይሳለቃሉ:: ወደ ፊትም ቅጣትን በሚያዩ ጊዜ መንገድን በጣም የተሳሳተው ማን እንደ ሆነ በእርግጥ ያኔ ያውቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَرَءَيْتَ مَنِ ٱتَّخَذَ إِلَٰهَهُۥ هَوَىٰهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘን ሰው አየህን? አንተም በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ تَحْسَبُ أَنَّ أَكْثَرَهُمْ يَسْمَعُونَ أَوْ يَعْقِلُونَ إِنْ هُمْ إِلَّا كَٱلْأَنْعَٰمِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy44. ይልቁንም አብዛኛዎቻቸው የሚሰሙ ወይም የሚያውቁ መሆናቸውን ታስባለህን? እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከቶውንም እነርሱ ከእንስሳዎች በባሰ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَىٰ رَبِّكَ كَيْفَ مَدَّ ٱلظِّلَّ وَلَوْ شَآءَ لَجَعَلَهُۥ سَاكِنًا ثُمَّ جَعَلْنَا ٱلشَّمْسَ عَلَيْهِ دَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥላን እንዴት እንደ ዘረጋ አላየህምን? በሻም ኖሮ የረጋ ባደረገው ነበር:: ከዚያ ጸሐይን በእርሱ ላይ ምልክት አደረግን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ قَبَضْنَٰهُ إِلَيْنَا قَبْضًا يَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy46. ከዚያም ቀስ በቀስ ወደ እኛ ሰበሰብነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِبَاسًا وَٱلنَّوْمَ سُبَاتًا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورًا

Amharic Translation - Africa Academy47. እርሱም ያ ለእናንተ ሌሊትን ልብስ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ:: ቀንንም መተኛ ያደረገላችሁ አምላክ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ ٱلرِّيَٰحَ بُشْرًۢا بَيْنَ يَدَىْ رَحْمَتِهِۦ وَأَنزَلْنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً طَهُورًا

Amharic Translation - Africa Academy48. እርሱ (አላህ) ያ ንፋሶችን አብሳሪዎች ሲሆኑ ከዝናቡ በስተፊት የላከ ነው:: ከሰማይም አጥሪ ውሃን አወረድን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّنُحْـِۧىَ بِهِۦ بَلْدَةً مَّيْتًا وَنُسْقِيَهُۥ مِمَّا خَلَقْنَآ أَنْعَٰمًا وَأَنَاسِىَّ كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy49. በእርሱ የሞተችን ሀገር ህያው ልናደርግበት፤ ከፈጠርነዉም ፍጡር እንስሳዎችንና ብዙ ሰዎችንም ልናጠጣበት አወረድነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ صَرَّفْنَٰهُ بَيْنَهُمْ لِيَذَّكَّرُوا۟ فَأَبَىٰٓ أَكْثَرُ ٱلنَّاسِ إِلَّا كُفُورًا

Amharic Translation - Africa Academy50. ጸጋችንን ይገነዘቡም ዘንድ በመካከላቸው ከፋፈልነው አበላለጥነዉም:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ክህደትን እንጂ እንቢ አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ شِئْنَا لَبَعَثْنَا فِى كُلِّ قَرْيَةٍ نَّذِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy51. በሻንም ኖሮ በየከተማይቱ አስፈራሪን በላክን ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا تُطِعِ ٱلْكَٰفِرِينَ وَجَٰهِدْهُم بِهِۦ جِهَادًا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy52. ከሓዲያንን አትታዘዛቸው:: በእርሱም (በቁርኣን) ታላቅን ትግል ታገላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى مَرَجَ ٱلْبَحْرَيْنِ هَٰذَا عَذْبٌ فُرَاتٌ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌ وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا بَرْزَخًا وَحِجْرًا مَّحْجُورًا

Amharic Translation - Africa Academy53. እርሱ ያ ሁለትን ባህሮች አጎራብቶ የለቀቀ ነው:: አንዱ ጥም የሚቆርጥና ጣፋጭ ነው:: ሌላኛው ደግሞ የሚመረግግ ጨው ነው:: በመካከላቸዉም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን ክልል ያደረገ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ مِنَ ٱلْمَآءِ بَشَرًا فَجَعَلَهُۥ نَسَبًا وَصِهْرًا وَكَانَ رَبُّكَ قَدِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy54. እርሱም ያ ከውሃ ሰውን የፈጠረ የዝምድናና የአማችም ባለቤት ያደረገው ነው:: ጌታህም ሁሉን ነገር ቻይ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُهُمْ وَلَا يَضُرُّهُمْ وَكَانَ ٱلْكَافِرُ عَلَىٰ رَبِّهِۦ ظَهِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy55. ከአላህ ሌላ የማይጠቅማቸውንና የማይጎዳቸውን አካል ይገዛሉ:: ከሓዲ በጌታው ላይ (በማመጽ ለሰይጣን) ረዳት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ إِلَّا مُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጂ አላክንህም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِلَّا مَن شَآءَ أَن يَتَّخِذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይ ዋጋን በፍጹም አልጠይቃችሁም። ወደ ጌታው መልካም መንገድን ለመያዝ የሻ ሰው ይስራ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy58. በዚያም በማይሞተው ህያው አምላክ ላይ ተመካ፤ ከማመስገንም ጋር አጥራው:: የባሮቹን ኃጢአቶች ውስጥ በማወቅ በእርሱ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ ٱلرَّحْمَٰنُ فَسْـَٔلْ بِهِۦ خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy59. ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ የፈጠረ ነው። ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ አለ:: አር-ረህማን ነው:: ከእርሱም አዋቂን ጠይቅ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱسْجُدُوا۟ لِلرَّحْمَٰنِ قَالُوا۟ وَمَا ٱلرَّحْمَٰنُ أَنَسْجُدُ لِمَا تَأْمُرُنَا وَزَادَهُمْ نُفُورًا

Amharic Translation - Africa Academy60. ለእነርሱም «ለአር-ረህማን ስገዱ።» በተባሉ ጊዜ «አር-ረህማን ማን ነው? ለምታዘንና ለማናውቀው እንሰግዳለን እንዴ?» ይላሉ። ይህም መራቅን ጨመራቸው። {1}

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَبَارَكَ ٱلَّذِى جَعَلَ فِى ٱلسَّمَآءِ بُرُوجًا وَجَعَلَ فِيهَا سِرَٰجًا وَقَمَرًا مُّنِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy61. ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገና በእርሷም አንጸባራቂን ጸሐይ አብሪ ጨረቃንም የፈጠረ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ خِلْفَةً لِّمَنْ أَرَادَ أَن يَذَّكَّرَ أَوْ أَرَادَ شُكُورًا

Amharic Translation - Africa Academy62. እርሱም ያ ያመለጠውን ስራ ማስታወስን ለሚፈልግ ወይም ማመስገንን ለሚፈልግ ሌሊትንና ቀንን ተተካኪ ያደረገ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلْجَٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَٰمًا

Amharic Translation - Africa Academy63. የአር-ረህማን ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚሄዱት፤ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሯቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَٰمًا

Amharic Translation - Africa Academy64. እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች (ሰጋጆች) ሆነው የሚያድሩት ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا ٱصْرِفْ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا

Amharic Translation - Africa Academy65. እነዚያም (እንዲህ) የሚሉት ናቸው: «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ መልስልን ቅጣቷ የማይለይለቅ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهَا سَآءَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا

Amharic Translation - Africa Academy66. «እርሷ መርጊያና መቀመጫ ለመሆን ከፋች!» የሚሉት ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ إِذَآ أَنفَقُوا۟ لَمْ يُسْرِفُوا۟ وَلَمْ يَقْتُرُوا۟ وَكَانَ بَيْنَ ذَٰلِكَ قَوَامًا

Amharic Translation - Africa Academy67. እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑት የማይቆጥቡትም ናቸው:: በዚህም መካከል ልግስናቸው ትክክለኛ የሆነ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ ٱلنَّفْسَ ٱلَّتِى حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

Amharic Translation - Africa Academy68. እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደርጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉ እና የማያመነዝሩት ናቸው:: ይህንን የሚፈጽም ሰው ወንጀለኛ ይሆናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُضَٰعَفْ لَهُ ٱلْعَذَابُ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِۦ مُهَانًا

Amharic Translation - Africa Academy69. በትንሳኤ ቀን ቅጣት ይደራረብበታል:: በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ዘልአለሙን ይኖራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَٰلِحًا فَأُو۟لَٰٓئِكَ يُبَدِّلُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِهِمْ حَسَنَٰتٍ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy70. ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም የሰራ ሰው ብቻ ሲቀር እነዚያም አላህ መጥፎ ስራዎቻቸውን በመልካም ስራዎች ይለውጣል:: አላህም እጅግ መሓሪና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن تَابَ وَعَمِلَ صَٰلِحًا فَإِنَّهُۥ يَتُوبُ إِلَى ٱللَّهِ مَتَابًا

Amharic Translation - Africa Academy71. ተጸጽቶ የተመለሰና መልካምን ተግባር የሰራ እርሱ በአላህ ዘንድ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ ٱلزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا۟ بِٱللَّغْوِ مَرُّوا۟ كِرَامًا

Amharic Translation - Africa Academy72. እነዚያ በሐሰት የማይጣዱ፤ በውድቅ ቃል (ተናጋሪ) አጠገብም ባለፉ ጊዜ የተከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُوا۟ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمْ لَمْ يَخِرُّوا۟ عَلَيْهَا صُمًّا وَعُمْيَانًا

Amharic Translation - Africa Academy73. እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ በተገሠጹ ጊዜ (የተረዱ ተቀባዮች ሆነው እንጂ) ደንቆሮዎችና እውሮች ሆነው በእርሷ ላይ የማይደፉት ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَٰجِنَا وَذُرِّيَّٰتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَٱجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا

Amharic Translation - Africa Academy74. እነዚያ «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፤ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን።» የሚሉ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ يُجْزَوْنَ ٱلْغُرْفَةَ بِمَا صَبَرُوا۟ وَيُلَقَّوْنَ فِيهَا تَحِيَّةً وَسَلَٰمًا

Amharic Translation - Africa Academy75. እነዚያ በመታገሳቸው የገነትን ሰገነቶች ይመነዳሉ:: በእርሷም ውስጥ ውዳሴንና ሰላምታን ይሰጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَٰلِدِينَ فِيهَا حَسُنَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا

Amharic Translation - Africa Academy76. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሆነው (ይሰጣሉ):: መርጊያና መኖሪያይቱ ገነት አማረች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَا يَعْبَؤُا۟ بِكُمْ رَبِّى لَوْلَا دُعَآؤُكُمْ فَقَدْ كَذَّبْتُمْ فَسَوْفَ يَكُونُ لِزَامًۢا

Amharic Translation - Africa Academy77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ) «ጸሎታችሁ ባልነበረ ኖሮ ጌታዬ እናንተን ከምንም አይቆጥራችሁም ነበር:: አስተባበላችሁ:: እናም ወደ ፊት ቅጣት ያዣችሁ ይሆናል።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70