ሱረቱ Al-Muddaththir المدثر
56 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 4
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْمُدَّثِّرُ
Amharic Translation - Africa Academy1. አንተ (ልብስ) ደራቢው ሆይ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُمْ فَأَنذِرْ
Amharic Translation - Africa Academy2. ተነሳና (ህዝቦችህን) አስጠንቅቅ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَرَبَّكَ فَكَبِّرْ
Amharic Translation - Africa Academy3. ጌታህንም አክብር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَثِيَابَكَ فَطَهِّرْ
Amharic Translation - Africa Academy4. ልብስህንም አጥራ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلرُّجْزَ فَٱهْجُرْ
Amharic Translation - Africa Academy5. ጣዖትንም ራቅ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَمْنُن تَسْتَكْثِرُ
Amharic Translation - Africa Academy6. ማብዛትንም የምትፈልግ ሆነህ አትለግስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِرَبِّكَ فَٱصْبِرْ
Amharic Translation - Africa Academy7. (ብዙ ዒባዳን ከመስራት አትድከም):: ለጌታህም (ትዕዘዛዝ) ታገስ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا نُقِرَ فِى ٱلنَّاقُورِ
Amharic Translation - Africa Academy8. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَذَٰلِكَ يَوْمَئِذٍ يَوْمٌ عَسِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy9. ይህን ጊዜ ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ غَيْرُ يَسِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy10. (በተለይ) በከሓዲያን ላይ ገር ያልሆነ ቀን ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَرْنِى وَمَنْ خَلَقْتُ وَحِيدًا
Amharic Translation - Africa Academy11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በብቸኝነት ከፈጠርኩት ጋር ተወኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلْتُ لَهُۥ مَالًا مَّمْدُودًا
Amharic Translation - Africa Academy12. ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በዓይነቱ) አደረግኩለት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبَنِينَ شُهُودًا
Amharic Translation - Africa Academy13. በየአደባባዩ ተገኝ የሆኑ ወንዶች ልጆችንም ሰጠሁት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَهَّدتُّ لَهُۥ تَمْهِيدًا
Amharic Translation - Africa Academy14. ለእርሱም ኑሮውን መዘርጋትን ዘረጋሁለት፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ يَطْمَعُ أَنْ أَزِيدَ
Amharic Translation - Africa Academy15. ከዚያ ልጨምርለት ይከጅላል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّآ إِنَّهُۥ كَانَ لِـَٔايَٰتِنَا عَنِيدًا
Amharic Translation - Africa Academy16. ሰው ይከልከል! እርሱ ለአናቅጻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበርና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَأُرْهِقُهُۥ صَعُودًا
Amharic Translation - Africa Academy17. በእርግጥ (ገሀነም ውስጥ) ችግርን አስገድደዋለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُۥ فَكَّرَ وَقَدَّرَ
Amharic Translation - Africa Academy18. እርሱ (በቁርኣን ጉዳይ) አሰበ፤ ገመተም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ
Amharic Translation - Africa Academy19. እናም ተረገመ:: እንዴት ገመተ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ قُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ
Amharic Translation - Africa Academy20. ከዚያ ተረገመ። እንዴትስ ገመተ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ نَظَرَ
Amharic Translation - Africa Academy21. ከዚያም እንደገና (በቁርኣን ጉዳይ) ተመለከተ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ
Amharic Translation - Africa Academy22. ከዚያ ፊቱን አጨፈገገ አኮማተረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ أَدْبَرَ وَٱسْتَكْبَرَ
Amharic Translation - Africa Academy23. ከዚያ (በአላህ ከማመን) ዞረ:: ኮራም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقَالَ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ يُؤْثَرُ
Amharic Translation - Africa Academy24. «ይህ ከሌላ (ሰው) የሚቀዳ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنْ هَٰذَآ إِلَّا قَوْلُ ٱلْبَشَرِ
Amharic Translation - Africa Academy25. «ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَأُصْلِيهِ سَقَرَ
Amharic Translation - Africa Academy26. ሰቀር (በተባለ የገሀነም ዋሻ ውስጥ) በእርግጥ አስገባዋለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَدْرَىٰكَ مَا سَقَرُ
Amharic Translation - Africa Academy27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰቀር ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا تُبْقِى وَلَا تَذَرُ
Amharic Translation - Africa Academy28. (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም:: አትተዉምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَوَّاحَةٌ لِّلْبَشَرِ
Amharic Translation - Africa Academy29. የሰዎችን ቆዳ በጣም አክሳይ ናት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَلَيْهَا تِسْعَةَ عَشَرَ
Amharic Translation - Africa Academy30. በእርሷም ላይ አስራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا جَعَلْنَآ أَصْحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةً وَمَا جَعَلْنَا عِدَّتَهُمْ إِلَّا فِتْنَةً لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيَسْتَيْقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ وَيَزْدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِيمَٰنًا وَلَا يَرْتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمُؤْمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَٱلْكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًا كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِى مَن يَشَآءُ وَمَا يَعْلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَ وَمَا هِىَ إِلَّا ذِكْرَىٰ لِلْبَشَرِ
Amharic Translation - Africa Academy31. የእሳትን ዘበኞች መላዕክት እንጂ ሌላ አላደረግንም:: ቁጥራቸውንም ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ሰዎች መፈተኛ እንጂ ለሌላ አላደረግንም:: እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች እንዲያረጋግጡ፤ እነዚያም በትክክል ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፤ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምዕመናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፤ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አስመሳዮችና ከሓዲያን «አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል?» እንዲሉ እንጂ (አላደረግንም):: ልክ እንደዚሁ አላህ የሚፈልገውን ያጠማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህንም ሰራዊት ልክ ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቅም:: የሰቀር እሳት ለሰዎች መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّا وَٱلْقَمَرِ
Amharic Translation - Africa Academy32. (ከክህደት) ይከልከሉ:: በጨረቃ (እምላለሁ)፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّيْلِ إِذْ أَدْبَرَ
Amharic Translation - Africa Academy33. በሌሊቱም በሄደ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلصُّبْحِ إِذَآ أَسْفَرَ
Amharic Translation - Africa Academy34. በንጋቱም ባበራ ጊዜ እምላለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهَا لَإِحْدَى ٱلْكُبَرِ
Amharic Translation - Africa Academy35. (ሰቀር) ከታላላቆች አደጋዎች አንዱ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نَذِيرًا لِّلْبَشَرِ
Amharic Translation - Africa Academy36. ለሰዎች አስፈራሪ ናት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِمَن شَآءَ مِنكُمْ أَن يَتَقَدَّمَ أَوْ يَتَأَخَّرَ
Amharic Translation - Africa Academy37. ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለፈለገ (ሰው) ሁሉ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُلُّ نَفْسٍۭ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy38. ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ተያዥ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّآ أَصْحَٰبَ ٱلْيَمِينِ
Amharic Translation - Africa Academy39. እነዚያ መዝገባቸውን በቀኝ እጃቸው የሚሰጡት ብቻ ሲቀሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِى جَنَّٰتٍ يَتَسَآءَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy40. (እነርሱማ) በገነቶች ውስጥ ሁነው እርስ በራሳቸው ይጠያየቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَنِ ٱلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy41. ከአመጸኞች ሁኔታ (ይጠያየቃሉ)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا سَلَكَكُمْ فِى سَقَرَ
Amharic Translation - Africa Academy42. (ከዚያ ለእነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል።) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ لَمْ نَكُ مِنَ ٱلْمُصَلِّينَ
Amharic Translation - Africa Academy43. «ከሰጋጆች አልነበርንም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ ٱلْمِسْكِينَ
Amharic Translation - Africa Academy44. «ለድሆችም የምናበላም አልነበርንም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلْخَآئِضِينَ
Amharic Translation - Africa Academy45. «ከዘባራቂዎችም ጋር እንዘባርቅ ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوْمِ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy46. «በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበር፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
حَتَّىٰٓ أَتَىٰنَا ٱلْيَقِينُ
Amharic Translation - Africa Academy47. «እርግጠኛው ነገር ሞት እስከመጣብን ድረስ።» ይላሉ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَا تَنفَعُهُمْ شَفَٰعَةُ ٱلشَّٰفِعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy48. እናም በዚያ ቀን የአማላጆች (ሁሉ) ምልጃ አትጠቅማቸዉም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَا لَهُمْ عَنِ ٱلتَّذْكِرَةِ مُعْرِضِينَ
Amharic Translation - Africa Academy49. ከ(ቁርኣን) ከግሳጼም የሚያፈገፍጉበት ምን ምክኒያት አላቸው?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَأَنَّهُمْ حُمُرٌ مُّسْتَنفِرَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy50. እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዩች ይመስላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَرَّتْ مِن قَسْوَرَةٍۭ
Amharic Translation - Africa Academy51. ከአንበሳ የሸሹ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ يُرِيدُ كُلُّ ٱمْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُؤْتَىٰ صُحُفًا مُّنَشَّرَةً
Amharic Translation - Africa Academy52. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል ለእያንዳንዱ ሰው የተዘረጉ ጹሑፎችን በእጁ እንዲሰጥ ይፈልጋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّا بَل لَّا يَخَافُونَ ٱلْـَٔاخِرَةَ
Amharic Translation - Africa Academy53. ከዚህ መሰል ተግባራቸው ይከልከሉ:: ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት አይፈሩም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّآ إِنَّهُۥ تَذْكِرَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy54. ይከልከሉ፤እርሱ(ቁርአን) መገሰጫ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy55. ስለዚህ የፈለገ ሰው ቁርኣንን ይገሰጽበታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَذْكُرُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ هُوَ أَهْلُ ٱلتَّقْوَىٰ وَأَهْلُ ٱلْمَغْفِرَةِ
Amharic Translation - Africa Academy56. ሆኖም (ሰዎች) አላህ ካልፈለገ በስተቀር አይገሰጹም:: አላህ የመፈራት ባለቤት ነው:: (ለፈሩትም) የምህረት ባለቤት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→