ሱረቱ Al-Muzzammil المزمل
20 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 3
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْمُزَّمِّلُ
Amharic Translation - Africa Academy1. አንተ ተከናናቢው ሆይ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُمِ ٱلَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy2. ሌሊቱን (ሁሉ) ጥቂት ሲቀር ቁም (ስገድ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نِّصْفَهُۥٓ أَوِ ٱنقُصْ مِنْهُ قَلِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy3. ግማሹን (ቁም) ወይም ከእርሱ ጥቂትን ቀንስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ ٱلْقُرْءَانَ تَرْتِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy4. ወይም በእርሱ ላይ ጨምር:: ቁርኣንንም በዝግታ አንብብ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا سَنُلْقِى عَلَيْكَ قَوْلًا ثَقِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy5. እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እናወርዳለንና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ نَاشِئَةَ ٱلَّيْلِ هِىَ أَشَدُّ وَطْـًٔا وَأَقْوَمُ قِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy6. ሌሊት መነሳት (ህዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ነው:: ለማንበብም ትክክለኛ ሰዓት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ لَكَ فِى ٱلنَّهَارِ سَبْحًا طَوِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy7. ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም የመዘዋወርያ ሰዓት አለህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرِ ٱسْمَ رَبِّكَ وَتَبَتَّلْ إِلَيْهِ تَبْتِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy8. የጌታህን ስም አውሳ:: ወደ እርሱም (አምልኮ) መቋረጥን ተቋረጥ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَّبُّ ٱلْمَشْرِقِ وَٱلْمَغْرِبِ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَٱتَّخِذْهُ وَكِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy9. (እርሱም) የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: መጠጊያ አድርገህም ያዘው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱهْجُرْهُمْ هَجْرًا جَمِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy10. (ከሓዲያንም) በሚሉት ላይ ታገስ:: መልካምንም መተው ተዋቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَذَرْنِى وَٱلْمُكَذِّبِينَ أُو۟لِى ٱلنَّعْمَةِ وَمَهِّلْهُمْ قَلِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy11. የድሎት ባለቤቶችም ከሆኑት አስተባባዮች ጋር ተወኝ:: ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ لَدَيْنَآ أَنكَالًا وَجَحِيمًا
Amharic Translation - Africa Academy12. ከእኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎችና እሳት አሉንና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَطَعَامًا ذَا غُصَّةٍ وَعَذَابًا أَلِيمًا
Amharic Translation - Africa Academy13. (ጉሮሮን) የሚያንቅ ምግብና አሳማሚ ቅጣትም አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ تَرْجُفُ ٱلْأَرْضُ وَٱلْجِبَالُ وَكَانَتِ ٱلْجِبَالُ كَثِيبًا مَّهِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy14. በዚያ ምድርና ጋራዎች በሚርገፈገፉበት፤ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚሆኑበት ቀን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَرْسَلْنَآ إِلَيْكُمْ رَسُولًا شَٰهِدًا عَلَيْكُمْ كَمَآ أَرْسَلْنَآ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ رَسُولًا
Amharic Translation - Africa Academy15. እኛ ወደ ፊርዖን መልዕክተኛን እንደላክን ሁሉ በእናንተ ላይ መስካሪ መልዕክተኛንም ወደ እናንተ ላክን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَعَصَىٰ فِرْعَوْنُ ٱلرَّسُولَ فَأَخَذْنَٰهُ أَخْذًا وَبِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy16. ፊርዓውንም መልዕክተኛውን አመጸ:: ብርቱ መያዝንም ያዝነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَيْفَ تَتَّقُونَ إِن كَفَرْتُمْ يَوْمًا يَجْعَلُ ٱلْوِلْدَٰنَ شِيبًا
Amharic Translation - Africa Academy17. (በአላህ) ከካዳችሁ ያን ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን ቅጣት እንዴት ትጠነቀቃላችሁ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلسَّمَآءُ مُنفَطِرٌۢ بِهِۦ كَانَ وَعْدُهُۥ مَفْعُولًا
Amharic Translation - Africa Academy18. ሰማዩ በቀኑ ተሰንጣቂ ነው:: ቀጠሮዉም ተፈፃሚ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰذِهِۦ تَذْكِرَةٌ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ سَبِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy19. ይህች መገሰጫ ናት። መዳንንም የሻ (የፈለገ) ሰው ወደ ጌታው (የሚያደርሰዉን) መንገድ ይይዛል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ رَبَّكَ يَعْلَمُ أَنَّكَ تَقُومُ أَدْنَىٰ مِن ثُلُثَىِ ٱلَّيْلِ وَنِصْفَهُۥ وَثُلُثَهُۥ وَطَآئِفَةٌ مِّنَ ٱلَّذِينَ مَعَكَ وَٱللَّهُ يُقَدِّرُ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ عَلِمَ أَن لَّن تُحْصُوهُ فَتَابَ عَلَيْكُمْ فَٱقْرَءُوا۟ مَا تَيَسَّرَ مِنَ ٱلْقُرْءَانِ عَلِمَ أَن سَيَكُونُ مِنكُم مَّرْضَىٰ وَءَاخَرُونَ يَضْرِبُونَ فِى ٱلْأَرْضِ يَبْتَغُونَ مِن فَضْلِ ٱللَّهِ وَءَاخَرُونَ يُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَٱقْرَءُوا۟ مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَقْرِضُوا۟ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا وَمَا تُقَدِّمُوا۟ لِأَنفُسِكُم مِّنْ خَيْرٍ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيْرًا وَأَعْظَمَ أَجْرًا وَٱسْتَغْفِرُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌۢ
Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን፤ ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መሆንህን ጌታህ ያውቃል:: (ሙስሊሞች) ከእነዚያም አብረውህ ካሉ ከፊሎች የሚቆሙ መሆናቸውንም ያውቃል:: አላህ ሌሊትና ቀንን ይለካል:: ሌሊቱን በሙሉ የማትቆሙት መሆናችሁን አወቀ:: እናም በእናንተ ላይ ህጉን ወደ ማቃለል ተመለሰላችሁ:: ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን ያህል አንብቡ:: ከናንተ ውስጥ ሌሎችም በሽተኞች ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ ሌሎችም፤ በአላህ መንገድ ሃይማኖት ላይ የሚጋደሉ እንደሚኖሩ አወቀ:: አቃለለላቸዉም ከቁርኣን የቻላችሁትን አንብቡ:: ሶላትንም ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: ለአላህ መልካም ብድርንም አበድሩ:: ከመልካም ስራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህን ምህረት ለምኑት:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→