ሱረቱ Al-Qiyaama القيامة
40 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 31
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ لَآ أُقْسِمُ بِيَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ
Amharic Translation - Africa Academy1. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በትንሳኤ ቀን እምላለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَآ أُقْسِمُ بِٱلنَّفْسِ ٱللَّوَّامَةِ
Amharic Translation - Africa Academy2. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ራሷን ወቃሽ በሆነች ነፍስም እምላለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَيَحْسَبُ ٱلْإِنسَٰنُ أَلَّن نَّجْمَعَ عِظَامَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy3. (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ።) ሰው አጥንቶችን ለመሰብሰባችን ይጠራጠራልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلَىٰ قَٰدِرِينَ عَلَىٰٓ أَن نُّسَوِّىَ بَنَانَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy4. እንዴታ ጣቶቹንም ፊት እንደነበሩት በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንሆን (እንሰበስባቸዋለን)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ يُرِيدُ ٱلْإِنسَٰنُ لِيَفْجُرَ أَمَامَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy5. ይልቁን ሰው በፊቱ ባለ ነገር በትንሳኤ ቀን ሊያስተባብል ይፈልጋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْـَٔلُ أَيَّانَ يَوْمُ ٱلْقِيَٰمَةِ
Amharic Translation - Africa Academy6. «የትንሳኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا بَرِقَ ٱلْبَصَرُ
Amharic Translation - Africa Academy7. ዓይንም በዋለለ ጊዜ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَخَسَفَ ٱلْقَمَرُ
Amharic Translation - Africa Academy8. ጨረቃም በጨለመ ጊዜ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجُمِعَ ٱلشَّمْسُ وَٱلْقَمَرُ
Amharic Translation - Africa Academy9. ጸሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَقُولُ ٱلْإِنسَٰنُ يَوْمَئِذٍ أَيْنَ ٱلْمَفَرُّ
Amharic Translation - Africa Academy10. ሰው በዚያን ቀን «መሸሻው የት ነው?» ይላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّا لَا وَزَرَ
Amharic Translation - Africa Academy11. «ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ ٱلْمُسْتَقَرُّ
Amharic Translation - Africa Academy12. በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።» ይባላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُنَبَّؤُا۟ ٱلْإِنسَٰنُ يَوْمَئِذٍۭ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ
Amharic Translation - Africa Academy13. ሰው በዚያን ቀን ያስቀደመውም ያስቆየውም ሁሉ ይነገረዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلِ ٱلْإِنسَٰنُ عَلَىٰ نَفْسِهِۦ بَصِيرَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy14. በእርግጥ ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَلْقَىٰ مَعَاذِيرَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy15. ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣ እንኳን (አይሰማም)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا تُحَرِّكْ بِهِۦ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِۦٓ
Amharic Translation - Africa Academy16. በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ብለህ ምላስህን አታላውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُۥ وَقُرْءَانَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy17. በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማስነበቡ በኛ ላይ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا قَرَأْنَٰهُ فَٱتَّبِعْ قُرْءَانَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy18. ባነበብነው ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy19. ከዚያም (ላንተ) ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّا بَلْ تُحِبُّونَ ٱلْعَاجِلَةَ
Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመጣደፍ ተከልከል፤ ይልቁንም (ሰዎች ስትባሉ) ፈጣኒቱን ዓለም ትወዳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَذَرُونَ ٱلْـَٔاخِرَةَ
Amharic Translation - Africa Academy21. የመጨረሻይቱን ዓለም (ግን) ትተዋላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy22. (የተወሰኑ) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. ወደ ጌታቸው ተመልካቾችም ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍۭ بَاسِرَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy24. (ሌሎች) ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን አጨፍጋጊዎች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَظُنُّ أَن يُفْعَلَ بِهَا فَاقِرَةٌ
Amharic Translation - Africa Academy25. በእነርሱም ላይ አደጋ እንደሚሰራባቸው ያረጋገጣሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلتَّرَاقِىَ
Amharic Translation - Africa Academy26. (ሙስሊሞች አስተውሉ።) (ነፍስ) ወደ ጉሮሮ በደረሰች፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقِيلَ مَنْ رَاقٍ
Amharic Translation - Africa Academy27. «አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَظَنَّ أَنَّهُ ٱلْفِرَاقُ
Amharic Translation - Africa Academy28. (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መለየት መሆኑን ባረጋገጠ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْتَفَّتِ ٱلسَّاقُ بِٱلسَّاقِ
Amharic Translation - Africa Academy29. ባትም ከባት በተጣበቀች ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ ٱلْمَسَاقُ
Amharic Translation - Africa Academy30. በዚያ ቀን መነዳት ወደ ጌታህ (ፍርድ) ብቻ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy31. እናም (ከሀዲው) አላመነምም፤ አልሰገደምም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy32. ግን በአላህ አስተባበለ፤ ከእምነት ዞረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰٓ أَهْلِهِۦ يَتَمَطَّىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy33. ከዚያም እየተንጎማለለ ወደ ቤተሰቡ ሄደ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy34. (የምትጠላውን ነገር) ላንተው ይሁን፤ ላንተ ተገቢህም ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy35. ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ላንተ የተገባህም ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَيَحْسَبُ ٱلْإِنسَٰنُ أَن يُتْرَكَ سُدًى
Amharic Translation - Africa Academy36. ሰው እንደፈለገ እንዲኖር ልቅ ሆኖ የሚተው ይመስለዋልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِىٍّ يُمْنَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy37. የሚፈስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy38. ከዚያ የረጋ ደም ሆነ:: ከዚያ አላህ ሰው አድርጎ ፈጠረው፤ አስተካከለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَجَعَلَ مِنْهُ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy39. ከእርሱም ሁለት ዓይነቶች ወንድና ሴትን አደረገ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَيْسَ ذَٰلِكَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحْـِۧىَ ٱلْمَوْتَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy40. (ታዲያ) ይህ ሀያል (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→