caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Mutaffifin المطففين

36 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 86

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَيْلٌ لِّلْمُطَفِّفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy1. ለቀሻቢዎች ወዮላቸው፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ إِذَا ٱكْتَالُوا۟ عَلَى ٱلنَّاسِ يَسْتَوْفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy2. ለእነዚያ ከሰዎች ለመግዛት ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا كَالُوهُمْ أَو وَّزَنُوهُمْ يُخْسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. እነርሱም (ለሰዎች) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎሉ (ለሆኑት)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَا يَظُنُّ أُو۟لَٰٓئِكَ أَنَّهُم مَّبْعُوثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መሆናቸውን (በትክክል) አያውቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيَوْمٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy5. ለታላቁ ቀን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يَقُومُ ٱلنَّاسُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy6. ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸውን)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلْفُجَّارِ لَفِى سِجِّينٍ

Amharic Translation - Africa Academy7. በእውነት የከሓዲያን መዝገብ በእርግጥ በ"ሲጂን" ውስጥ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَدْرَىٰكَ مَا سِجِّينٌ

Amharic Translation - Africa Academy8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ሲጂን" ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كِتَٰبٌ مَّرْقُومٌ

Amharic Translation - Africa Academy9. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy10. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوْمِ ٱلدِّينِ

Amharic Translation - Africa Academy11. ለእነዚያ በፍርድ ቀን ለሚያስተባብሉት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يُكَذِّبُ بِهِۦٓ إِلَّا كُلُّ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy12. በእርሱም ወሰን አላፊ ኃጢአተኛ ሁሉ እንጂ ሌላ አያስተባብልም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy13. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ እኒህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው ይላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّا بَلْ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. ይከልከሉ፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሰሩት የነበሩት ኃጢአት ደገደገባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّآ إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. ይከልከሉ:: እነርሱ በዚያ ቀን ጌታቸውን ከማየት ተጋራጆች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِنَّهُمْ لَصَالُوا۟ ٱلْجَحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy16. ከዚያ እነርሱ በእርግጥ ገሀነም ገቢዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا ٱلَّذِى كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. ከዚያ ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلْأَبْرَارِ لَفِى عِلِّيِّينَ

Amharic Translation - Africa Academy18. የ(እውነተኞቹ) ደጋጎች መጽሐፍ በ"ዒሊዩን" ውስጥ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَدْرَىٰكَ مَا عِلِّيُّونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ዒሊዩን"ም ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كِتَٰبٌ مَّرْقُومٌ

Amharic Translation - Africa Academy20. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَشْهَدُهُ ٱلْمُقَرَّبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. (የአላህ) ባለሟሎቹ ይጠብቁታል (ይጣዱታል)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْأَبْرَارَ لَفِى نَعِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy22. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَى ٱلْأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. በተዋቡ ዙፋኖች ላይ የተደገፉ ሆነው ይመለከታሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَعْرِفُ فِى وُجُوهِهِمْ نَضْرَةَ ٱلنَّعِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy24. ከፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ትረዳለህ (ታውቃለህ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُسْقَوْنَ مِن رَّحِيقٍ مَّخْتُومٍ

Amharic Translation - Africa Academy25. ተጣርቶ ከታተመ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خِتَٰمُهُۥ مِسْكٌ وَفِى ذَٰلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ ٱلْمُتَنَٰفِسُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. መደምደሚያው ሚስክ ከሆነ (መጠጥ ይጠጣሉ)። ተሽቀዳዳሚዎች በዚህ ይሽቀዳደሙ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِزَاجُهُۥ مِن تَسْنِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy27. መበረዣዉም ከተስኒም ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَيْنًا يَشْرَبُ بِهَا ٱلْمُقَرَّبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. (የአላህ) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ كَانُوا۟ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ يَضْحَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy29. እነዚያ (በአላህ ላይ) ያመጹት በእነዚያ (በአላህ) ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا مَرُّوا۟ بِهِمْ يَتَغَامَزُونَ

Amharic Translation - Africa Academy30. በእነርሱም አጠገብ ባለፉ ጊዜ ይጠቋቆሙባቸው (ይጠቃቀሱባቸው) ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱنقَلَبُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَهْلِهِمُ ٱنقَلَبُوا۟ فَكِهِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. ወደ ቤተሰቦቻቸዉም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ሆነው ይመለሱ ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا رَأَوْهُمْ قَالُوٓا۟ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. ባዩዋቸዉም ጊዜ፡- "እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው።" ይሉ ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أُرْسِلُوا۟ عَلَيْهِمْ حَٰفِظِينَ

Amharic Translation - Africa Academy33. በእነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲሆኑ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلْيَوْمَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنَ ٱلْكُفَّارِ يَضْحَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. ዛሬ (በትንሳኤ ቀን) ግን እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑት ሰዎች በከሓዲያን ላይ ይስቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَى ٱلْأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. በተዋበ ዙፋን ላይ ሆነው የሚመለከቱ ሲሆኑ (ይስቃሉ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ ثُوِّبَ ٱلْكُفَّارُ مَا كَانُوا۟ يَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. ከሓዲያን ይሰሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70