ሱረቱ Al-Infitaar الإنفطار
19 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 82
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنفَطَرَتْ
Amharic Translation - Africa Academy1. ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا ٱلْكَوَاكِبُ ٱنتَثَرَتْ
Amharic Translation - Africa Academy2. ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا ٱلْبِحَارُ فُجِّرَتْ
Amharic Translation - Africa Academy3. ባህሮችም በተከፈቱና በተደባለቁ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا ٱلْقُبُورُ بُعْثِرَتْ
Amharic Translation - Africa Academy4. መቃብሮችም በተገለባበጡና ሙታን በተነሱ ጊዜ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ وَأَخَّرَتْ
Amharic Translation - Africa Academy5. (ያኔ) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያዘገየችውን ታውቃለች።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلْإِنسَٰنُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ ٱلْكَرِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy6. አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِى خَلَقَكَ فَسَوَّىٰكَ فَعَدَلَكَ
Amharic Translation - Africa Academy7. በዚያ በፈጠረህ፤ አካለ ሙሉም ባደረገህ፤ ባስተካከለህም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِىٓ أَىِّ صُورَةٍ مَّا شَآءَ رَكَّبَكَ
Amharic Translation - Africa Academy8. በማንኛውም (እርሱ) በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ ጌታህ ምን አታለለህ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّا بَلْ تُكَذِّبُونَ بِٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy9 (ሰዎች ሆይ!) ተከልከሉ፤ በእውነት በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَٰفِظِينَ
Amharic Translation - Africa Academy10. በእናንተ ላይ ጠባቂዎች ያሉባችሁ ስትሆኑ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كِرَامًا كَٰتِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy11. የተከበሩ ጸሐፊዎች የሆኑ (ተጠባባቂዎች)፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. የምትሰሩትን (ሁሉ) ያውቃሉ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلْأَبْرَارَ لَفِى نَعِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy13. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ ٱلْفُجَّارَ لَفِى جَحِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy14.ከሓዲያንም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَصْلَوْنَهَا يَوْمَ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy15.በፍርዱ ቀን ይገቧታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا هُمْ عَنْهَا بِغَآئِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy16.እነርሱም (ምን ጊዜም) ከእርሷ ራቂዎች አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَدْرَىٰكَ مَا يَوْمُ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ مَآ أَدْرَىٰكَ مَا يَوْمُ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy18. ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቅህ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ لَا تَمْلِكُ نَفْسٌ لِّنَفْسٍ شَيْـًٔا وَٱلْأَمْرُ يَوْمَئِذٍ لِّلَّهِ
Amharic Translation - Africa Academy19. (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግ የማትችልበት ቀን ነው:: ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→