caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Qalam القلم

52 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 2

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ نٓ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy1. ኑን፤ በብዕር እና በዚያም በሱ በሚጽፉት ሁሉ እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَآ أَنتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِمَجْنُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በጌታህ ጸጋ ምክኒያት ዕብድ አይደለህም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ لَكَ لَأَجْرًا غَيْرَ مَمْنُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy3. ላንተም ከጌታህ የማይቋረጥ ምንዳ (የልፋት ዋጋ) በእርግጥ አለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy4. አንተም በታላቅ ጸባይ ላይ ነህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسَتُبْصِرُ وَيُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. ወደ ፊት አንተም ታያለህ፤ እነርሱም ያያሉ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِأَييِّكُمُ ٱلْمَفْتُونُ

Amharic Translation - Africa Academy6. ዕብደት በማንኛችሁ እንዳለ (እብዱ ማን እንደሆነ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy7. ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው። ወደ ቀናው መንገድ ተመሪዎችንም አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا تُطِعِ ٱلْمُكَذِّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy8. ስለዚህ ለአስተባባዩች (ሁሉ) አትታዘዝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدُّوا۟ لَوْ تُدْهِنُ فَيُدْهِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9. (አስተባባዩች) ብትመሳሰላቸውና እነርሱም ቢመሳሰሉህ ተመኙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُطِعْ كُلَّ حَلَّافٍ مَّهِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy10. መሓለኛን ወራዳን ሁሉ አትታዘዝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَمَّازٍ مَّشَّآءٍۭ بِنَمِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy11. ሰውን አነዋሪን፤ ነገር አሳባቂን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّنَّاعٍ لِّلْخَيْرِ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy12.ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፤ ወሰን አላፊን፤ ኃጢአተኛንም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عُتُلٍّۭ بَعْدَ ذَٰلِكَ زَنِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy13. ልበ ደረቅን ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የዝሙት ልጅ ዲቃላን (አትታዘዝ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَن كَانَ ذَا مَالٍ وَبَنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy14. የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመሆኑ (ያስተባብላል)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy15. በእርሱ ላይ እንቀፆቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَنَسِمُهُۥ عَلَى ٱلْخُرْطُومِ

Amharic Translation - Africa Academy16. በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክትን እናደርግበታለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا بَلَوْنَٰهُمْ كَمَا بَلَوْنَآ أَصْحَٰبَ ٱلْجَنَّةِ إِذْ أَقْسَمُوا۟ لَيَصْرِمُنَّهَا مُصْبِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy17. እኛ እነዚያን የአትክልቲቱን ባለቤቶች ማልደው ፍሬዋን ሊለቅሟት (አላህ ቢሻ ሳይሉ) በማሉ ጊዜ እንደሞከርን ሁሉ የመካ ሰዎችንም ሞከርናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَسْتَثْنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. (በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَطَافَ عَلَيْهَا طَآئِفٌ مِّن رَّبِّكَ وَهُمْ نَآئِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19.እነርሱ የተኙ ሆነዉም ሳሉ ከጌታህ የሆነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَصْبَحَتْ كَٱلصَّرِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy20. እንደ ሌሊት ጨለማ የከሰለች ሆና አነጋች (አደረች)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَنَادَوْا۟ مُصْبِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy21.ያነጉም ሆነው ተጠራሩ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَنِ ٱغْدُوا۟ عَلَىٰ حَرْثِكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy22. "ቆራጮች እንደ ሆናችሁ ወደ እርሻችሁ ለመሄድ ማልዱ በማለት" (ተጠራሩ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنطَلَقُوا۟ وَهُمْ يَتَخَٰفَتُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. እነርሱ የሚያሾካሾኩ ሆነው ሄዱም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَن لَّا يَدْخُلَنَّهَا ٱلْيَوْمَ عَلَيْكُم مِّسْكِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy24. ዛሬ በእናንተ ላይ አንድም ድሃ እንዳይገባት በማለትና

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَغَدَوْا۟ عَلَىٰ حَرْدٍ قَٰدِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy25. ድሆችን በመከልከልም ላይ በሀሳባቸው ቻዮች ሆነው ማለዱ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا رَأَوْهَا قَالُوٓا۟ إِنَّا لَضَآلُّونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ከዚያ ተቃጥላ ባዩዋት ጊዜ (እንዲህ) አሉ: «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ نَحْنُ مَحْرُومُونَ

Amharic Translation - Africa Academy27. «ይልቁንም እኛ ከአላህ የተከለከልን እደለ ቢሶች ነን» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَوْسَطُهُمْ أَلَمْ أَقُل لَّكُمْ لَوْلَا تُسَبِّحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. (ከመካከላቸው) ትክክለኛቸው (አስተዋያቸው)፡- «እናንተ አላህን ለምን አታጠሩም (አታወሱም) አላልኳችሁም ነበርን?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ سُبْحَٰنَ رَبِّنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. «(ሁላቸዉም) ጌታችን ጥራት ይገባው፤ እኛ በዳዩች ነበርን» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَلَٰوَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy30. እርስ በራሳቸው የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰوَيْلَنَآ إِنَّا كُنَّا طَٰغِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. «ዋ፤ጥፋታችን፤ እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَسَىٰ رَبُّنَآ أَن يُبْدِلَنَا خَيْرًا مِّنْهَآ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا رَٰغِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. «ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል:: እኛ ወደ ጌታችን ከጃዩች ነን» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ ٱلْعَذَابُ وَلَعَذَابُ ٱلْـَٔاخِرَةِ أَكْبَرُ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. (የአላህ) ቅጣቱ ልክ እንደዚሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ከዚህ የበለጠ ከባድ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ (ከዚህ ቅጣት በተጠነቀቁ ነበር)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy34. ለጥንቁቆች በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَنَجْعَلُ ٱلْمُسْلِمِينَ كَٱلْمُجْرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy35. ሙስሊሞችን እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን? (አናደርግም)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. ለእናንተ ምን (አስረጂ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ( ምን ነካችሁ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ لَكُمْ كِتَٰبٌ فِيهِ تَدْرُسُونَ

Amharic Translation - Africa Academy37. በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ لَكُمْ فِيهِ لَمَا تَخَيَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy38. በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁን? (የሚል)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ لَكُمْ أَيْمَٰنٌ عَلَيْنَا بَٰلِغَةٌ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّ لَكُمْ لَمَا تَحْكُمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy39. ወይስ «ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ» በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሳኤ ቀን ደራሽ የሆኑ መሐላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَلْهُمْ أَيُّهُم بِذَٰلِكَ زَعِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy40. በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ لَهُمْ شُرَكَآءُ فَلْيَأْتُوا۟ بِشُرَكَآئِهِمْ إِن كَانُوا۟ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy41. ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) ተጋሪዎች አሏቸውን? እውነተኞችም እንደሆኑ ተጋሪዎቻቸውን ያምጡ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يُكْشَفُ عَن سَاقٍ وَيُدْعَوْنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ فَلَا يَسْتَطِيعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ባት የሚገለጥበትን፤ (ከሓዲያን) ወደ መስገድ የሚጠሩበትና የማይችሉበትን ቀን (አስታውስ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَٰشِعَةً أَبْصَٰرُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ وَقَدْ كَانُوا۟ يُدْعَوْنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ وَهُمْ سَٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. ዓይኖቻቸው የፈሩ፤ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲሆኑ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን):: እነርሱ (በምድረ ዓለም) ደህና ሆነው ሳሉ ወደ ስግድት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَذَرْنِى وَمَن يُكَذِّبُ بِهَٰذَا ٱلْحَدِيثِ سَنَسْتَدْرِجُهُم مِّنْ حَيْثُ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመሆኑም እኔን በዚህ ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተወኝ፤ (ለእነርሱ እኔ እበቃሃለሁ):: ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأُمْلِى لَهُمْ إِنَّ كَيْدِى مَتِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy45. እነርሱንም አዘገያቸዋለሁ:: (ዘዴዬ) ብቀላየ ብርቱ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ تَسْـَٔلُهُمْ أَجْرًا فَهُم مِّن مَّغْرَمٍ مُّثْقَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይንስ በእውነቱ (በማስተማርህ) ዋጋን እንዲከፍሉህ ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ عِندَهُمُ ٱلْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy47. ወይስ ከእነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር እውቀት አለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ ٱلْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌ

Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ ለጌታህ (ዉሳኔ) ፍርድ ታገስ:: (በመበሳጨትና ባለ መታገስ) እንደ ዓሳው ባለቤት እንደ (ነብዩ ዩኑስ) አትሁን:: እርሱ በጭንቀት የተሞላ ሆኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّوْلَآ أَن تَدَٰرَكَهُۥ نِعْمَةٌ مِّن رَّبِّهِۦ لَنُبِذَ بِٱلْعَرَآءِ وَهُوَ مَذْمُومٌ

Amharic Translation - Africa Academy49. ከጌታው የሆነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ሆኖ በተጣለ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱجْتَبَٰهُ رَبُّهُۥ فَجَعَلَهُۥ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy50. ጌታዉም (በነብይነት) መረጠው:: ከደጋጎችም አደረገው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن يَكَادُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَيُزْلِقُونَكَ بِأَبْصَٰرِهِمْ لَمَّا سَمِعُوا۟ ٱلذِّكْرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُۥ لَمَجْنُونٌ

Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ «እርሱም በእርግጥ እብድ ነዉም» ይላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy52.እርሱ ግን ለዓለማት መገሰጫ (ገሳጭ) እንጂ ሌላ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70