ሱረቱ Al-Mulk الملك
30 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 77
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ تَبَٰرَكَ ٱلَّذِى بِيَدِهِ ٱلْمُلْكُ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy1. ያ ንግስና በእጁ የሆነው አምላክ ችሮታው በዛ:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ
Amharic Translation - Africa Academy2. ያ የየትኛችሁ ስራ ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ህይወትን የፈጠረ ነው:: እርሱም አሸናፊና መሀሪ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِى خَلَقَ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍ طِبَاقًا مَّا تَرَىٰ فِى خَلْقِ ٱلرَّحْمَٰنِ مِن تَفَٰوُتٍ فَٱرْجِعِ ٱلْبَصَرَ هَلْ تَرَىٰ مِن فُطُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy3. ያ ሰባቱን ሰማያት የተነባበሩ ሆነው የፈጠረ ነው:: በአል ረህማን አፈጣጠርም ውስጥ ምንም ቅንጣት ያህል መዛነፍን (መቃረንና መበላሸት) አይታይም:: ዓይንህንም መልስ:: ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ ٱرْجِعِ ٱلْبَصَرَ كَرَّتَيْنِ يَنقَلِبْ إِلَيْكَ ٱلْبَصَرُ خَاسِئًا وَهُوَ حَسِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. ከዚያም ዓይንህን መላልስ:: ዓይንህ ተዋርዶ (ተናንሶ)፤ እርሱም የደከመ ሆኖ ወደ አንተ ይመለሳል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنْيَا بِمَصَٰبِيحَ وَجَعَلْنَٰهَا رُجُومًا لِّلشَّيَٰطِينِ وَأَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابَ ٱلسَّعِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy5. ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት:: ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፤ ለእነርሱም ተንቀልቃይ የእሳትን ቅጣት አዘጋጀንላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِرَبِّهِمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy6. ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አላቸው:: መመላሻይቱም ገሀነም ከፋች!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذَآ أُلْقُوا۟ فِيهَا سَمِعُوا۟ لَهَا شَهِيقًا وَهِىَ تَفُورُ
Amharic Translation - Africa Academy7. በውስጧ በተጣሉ ጊዜ እርሷ የምትፈላ ስትሆን ከእርሷ እንደ (አህያ) ማናፋትን ይሰማሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَكَادُ تَمَيَّزُ مِنَ ٱلْغَيْظِ كُلَّمَآ أُلْقِىَ فِيهَا فَوْجٌ سَأَلَهُمْ خَزَنَتُهَآ أَلَمْ يَأْتِكُمْ نَذِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy8. ከቁጭቷ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች:: በውስጧ ቡድኖች በተጣሉ ቁጥር «ዘበኞቿ (ስለዚህ ቀን) አስፈራሪ (ነብይ) አልመጣላችሁም ነበርን?» በማለት ይጠይቋቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ بَلَىٰ قَدْ جَآءَنَا نَذِيرٌ فَكَذَّبْنَا وَقُلْنَا مَا نَزَّلَ ٱللَّهُ مِن شَىْءٍ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا فِى ضَلَٰلٍ كَبِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy9. «አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶልናል:: አስተባበልንም:: አላህም ምንንም አላወረደም:: እናንተ አውርዷል ስትሉ፤ በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጂ አይደላችሁም አልን» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِىٓ أَصْحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy10. «የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርን ኖሮ የእሳት ጓዶች ባልሆን ነበር» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱعْتَرَفُوا۟ بِذَنۢبِهِمْ فَسُحْقًا لِّأَصْحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy11. በኃጢአታቸዉም ያምናሉ:: ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِٱلْغَيْبِ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy12. እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَسِرُّوا۟ قَوْلَكُمْ أَوِ ٱجْهَرُوا۟ بِهِۦٓ إِنَّهُۥ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy13. (ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ:: ወይም በእርሱ ጩሁ:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَا يَعْلَمُ مَنْ خَلَقَ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلْخَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy14. የፈጠረን አምላክ እርሱ እውቀተ ረቂቁ ውስጠ አዋቂው ሲሆን (ሚስጢርን) ሁሉ አያውቅምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَرْضَ ذَلُولًا فَٱمْشُوا۟ فِى مَنَاكِبِهَا وَكُلُوا۟ مِن رِّزْقِهِۦ وَإِلَيْهِ ٱلنُّشُورُ
Amharic Translation - Africa Academy15. እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው:: በጋራዎቿና በመንገዶቿም ሂዱ:: ከሲሳዮም ብሉ:: (ኋላ) መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ءَأَمِنتُم مَّن فِى ٱلسَّمَآءِ أَن يَخْسِفَ بِكُمُ ٱلْأَرْضَ فَإِذَا هِىَ تَمُورُ
Amharic Translation - Africa Academy16. በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ምድርን እንደማያሰምጥባችሁ ወዲያዉም እርሷም (እናንተኑ ውጣ) የምታረገርግ እንደማትሆን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ أَمِنتُم مَّن فِى ٱلسَّمَآءِ أَن يُرْسِلَ عَلَيْكُمْ حَاصِبًا فَسَتَعْلَمُونَ كَيْفَ نَذِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy17. ወይስ በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ንፋስን እንደማልክባችሁ ትተማመናላችሁ? (አትፈሩም?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy18. እነዚያ ከእነርሱ በስተፊት የነበሩትም አስተባበሉ:: ጥላቻየም እንዴት ነበር (አስተዉል)፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَرَوْا۟ إِلَى ٱلطَّيْرِ فَوْقَهُمْ صَٰٓفَّٰتٍ وَيَقْبِضْنَ مَا يُمْسِكُهُنَّ إِلَّا ٱلرَّحْمَٰنُ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَىْءٍۭ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy19. ከበላያቸው ሰልፍ ሰርተው ወዳሉ ወፎች አይመለከቱምን? ክንፎቻቸውን ያጥፋሉ:: ከአር-ረህማን ሌላ የሚይዛቸው የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمَّنْ هَٰذَا ٱلَّذِى هُوَ جُندٌ لَّكُمْ يَنصُرُكُم مِّن دُونِ ٱلرَّحْمَٰنِ إِنِ ٱلْكَٰفِرُونَ إِلَّا فِى غُرُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy20. በእውነት ያ እርሱ ከአር-ረህማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የሆነ ሰራዊት ማነው? ከሓዲያን በመታለል ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمَّنْ هَٰذَا ٱلَّذِى يَرْزُقُكُمْ إِنْ أَمْسَكَ رِزْقَهُۥ بَل لَّجُّوا۟ فِى عُتُوٍّ وَنُفُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy21. ወይም ሲሳዮን ቢይዝባችሁ ያ ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? በእውነት እነርሱ በሞገድና በመደንበር ውስጥ ጸኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَن يَمْشِى مُكِبًّا عَلَىٰ وَجْهِهِۦٓ أَهْدَىٰٓ أَمَّن يَمْشِى سَوِيًّا عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy22. በፊቱ ላይ ተደፍቶ የሚሄድ ሰው ይበልጥ የተቀና ነውን? ወይስ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ተስተካክሎ የሚሄድ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ هُوَ ٱلَّذِىٓ أَنشَأَكُمْ وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَٱلْأَفْـِٔدَةَ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. እርሱ! ያ አላህ የፈጠራችሁ፤ ለእናተም መስሚያና ማያዎች፤ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው:: ጥቂትንም አታመሰግኑምን በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ هُوَ ٱلَّذِى ذَرَأَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ وَإِلَيْهِ تُحْشَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. እርሱ ያ በምድር ላይ የበተናችሁ ነው:: ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy25. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው ተፈፃሚ የሚሆነው?» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّمَا ٱلْعِلْمُ عِندَ ٱللَّهِ وَإِنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy26. እውቀቱ ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا رَأَوْهُ زُلْفَةً سِيٓـَٔتْ وُجُوهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَقِيلَ هَٰذَا ٱلَّذِى كُنتُم بِهِۦ تَدَّعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. (ቅጣቱ) ቅርብ ሆኖ ባዩትም ጊዜ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ፊቶች ይከፋሉ:: ይህ ያ በእርሱ ትከራከሩበት የነበራችሁት ነው ይባላሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُمْ إِنْ أَهْلَكَنِىَ ٱللَّهُ وَمَن مَّعِىَ أَوْ رَحِمَنَا فَمَن يُجِيرُ ٱلْكَٰفِرِينَ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አያችሁን? እስኪ ንገሩኝ? አላህ ቢገድለኝ ከእኔ ጋር ያሉትንም (እንደዚሁ) ወይም በማቆየት ቢያዝንልን ከሓዲያንን ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድን ማን ነው? በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ هُوَ ٱلرَّحْمَٰنُ ءَامَنَّا بِهِۦ وَعَلَيْهِ تَوَكَّلْنَا فَسَتَعْلَمُونَ مَنْ هُوَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ያ (እመኑበት የምላችሁ) አር-ረህማን ነው:: እኛ በእርሱ አመንን:: በእርሱም ላይ ተጠጋን:: ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የሆነው እርሱ ማን እንደሆነ በእርግጥ ታውቃላችሁ በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُمْ إِنْ أَصْبَحَ مَآؤُكُمْ غَوْرًا فَمَن يَأْتِيكُم بِمَآءٍ مَّعِينٍۭ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አያችሁ (እስኪንገሩኝ?) ውሃችሁ ሰራጊ ቢሆን (ወደ መሬት ቢሰርግ) ፈሳሽን (ምንጭን) ውሃ የሚያመጣላችሁ ማን ነው? በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→