قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ غَيْرَ ٱلْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوٓا۟ أَهْوَآءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا۟ مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا۟ كَثِيرًا وَضَلُّوا۟ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ
Amharic Translation - Africa Academy77. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ውጭ ወሰንን አትለፉ:: ፊትም የተሳሳቱትንና ብዙዎቹን ህዝቦች ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም አሁን የተሳሳቱትን ህዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች (ስሜቶች) አትከተሉ።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን (ማለፍ) ወሰንን አትለፉ፡፡ በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትንና ብዙዎችን ያሳሳቱና ከቀጥተኛው መንገድም (አሁን) የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡