لَا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغْوِ فِىٓ أَيْمَٰنِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ ٱلْأَيْمَٰنَ فَكَفَّٰرَتُهُۥٓ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَٰكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٍ ذَٰلِكَ كَفَّٰرَةُ أَيْمَٰنِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ وَٱحْفَظُوٓا۟ أَيْمَٰنَكُمْ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy89. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከመሀሎቻችሁ መካከል በውድቁ አይዛችሁም:: ባሰባችሁበት መሀላ ግን ይይዛችኋል:: እናም መሀላዎችን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ለአስር ሚስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይም የአንዲትን ባሪያ ጫንቃን ነፃ ማውጣት ነው:: ከተባሉት አንዱንም ያለገኘ ሶስት ቀናትን መፆም ብቻ ነው:: ይህ በማላችሁና መሀላዎቻችሁን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ነው:: መሀላዎቻችሁንም ጠብቁ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አናቅጽን ያብራራል:: እናንተም ልታመሰግኑት ይከጀላልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፡፡ ግን መሐላዎችን (ባሰባችሁት) ይይዛችኋል፡፡ ማስተሰሪያውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው (ምግብ) ዐስርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነሱን ማልበስ ወይም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፤ (ከተባሉት አንዱን) ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፡፡ መሐላዎቻችሁንም ጠብቁ፡፡ እንደዚሁ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ያብራራል፡፡ እናንተ ልታመሰግኑ ይከጀላልና፡፡