قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَسْتُمْ عَلَىٰ شَىْءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُوا۟ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ طُغْيَٰنًا وَكُفْرًا فَلَا تَأْسَ عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትን፤ ኢንጂልን እና ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ቁርኣንን እስከምትሰሩባቸው ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም።» በላቸው:: ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነርሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል:: በካሐዲያን ህዝቦች ላይ አትዘን።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደእናንተ የተወረደውን እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው፡፡ ከጌታህም ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል፡፡ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ አትዘን፡፡