caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 2

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:2

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُحِلُّوا۟ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ وَلَا ٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَلَا ٱلْهَدْىَ وَلَا ٱلْقَلَٰٓئِدَ وَلَآ ءَآمِّينَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّن رَّبِّهِمْ وَرِضْوَٰنًا وَإِذَا حَلَلْتُمْ فَٱصْطَادُوا۟ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَـَٔانُ قَوْمٍ أَن صَدُّوكُمْ عَنِ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ أَن تَعْتَدُوا۟ وَتَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْبِرِّ وَٱلتَّقْوَىٰ وَلَا تَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ምልክቶች ይሆኑ ዘንድ የከለከላቸውን ነገሮች የተፈቀዱ አታድርጉ። የተከበረውንም ወር በውስጡ ጦርነትን በማካሄድ አትድፈሩት:: ወደ መካ የሚነዱትን የመስዋዕት እንስሳትና የሚታበቱባቸውን ገመዶች፤ ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው ወደ ተከበረው ቤት አሳቢዎችንም በክፉ አትንኳቸው:: የሐጅን ስራ ፈጽማችሁ ባጠናቀቃችሁ ጊዜ የዱር አውሬዎችን እንደልባችሁ አድኑ:: ከተከበረው መስጊድ ስለከለከሏችሁ ሰዎችን መጥላታችሁ በእነርሱ ላይ ወሰንን እንድታልፉና ፍትህን እንድታዛቡ አይገፋፉችሁ:: በበጎ ተግባርና አላህን በመፍራት እርስ በእርስ ተባበሩ:: ኃጢአትና ወሰንን በማለፍ ግን አትተባበሩ:: አላህን በትክክል ፍሩ:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህ (ክልክል ያደረጋቸውን) ምልክቶች የተፈቀዱ አታድርጉ፡፡ የተከበረውንም ወር በመጋደል አትድፈሩ፡፡ ወደ መካ የሚነዱትን መስዋዕትና የሚታበቱባቸውንም ገመዶች ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው ወደ ተከበረው ቤት አሳቢዎችንም ሰዎች (አትንኩ)፡፡ ከሐጅም ሥራ በወጣችሁ ጊዜ ዐድኑ፡፡ ከተከበረው መስጊድ ስለከለከሉዋችሁ ሰዎችን መጥላትም (በነሱ ላይ) ወሰን እንድታልፉ አይገፋፋችሁ፡፡ በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70